2022-11-10 10:53:16
ጥቅምት 30 ማይካድራ ሁለት ዓመት ሞላው። ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በማይካድራ፣ ሁመራ፣ አብደራፊ፣ አብርሃጅራ እና ዳንሻ ከተሞች በዐማሮች ላይ የተፈጸመው ጥቃት ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት ነበር። ጥቃቱ ከመከሰቱ ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የዐማራ ተወላጆችን መታወቂያ ልንሰጣችሁ ነው በማለት መጀመሪያ እንዲመዘገቡ አደረጉ፤ በየቦታው እየተንቀሳቀሱ የማጣራት ስራ ተሰራ፤ ቤት ለቤት ፍተሻ አደረጉ፤ ወደየትም እንዳይንቀሳቀሱ ሁሉም መውጫ መንገዶች በትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት ተዘጉ፤ የትግራይ ተወላጆች እየተለዩ መሳሪያ እንዲታጠቁና የመሳሪያ አጠቃቀም ስልጠና እንዲወስዱ ተደረገ፤ ሊገደሉ ለታሰቡት ዐማሮች መቀበሪያ የሚሆን በሎደር የተቆፈሩ ጉድጓዶችንም አዘጋጁ።
እነዚህ ሁሉ ቅድመ ዝግጅቶች ከተደረጉ በኋላ ጥቅምት 30 ቀን የትግራይ ክልል የፖሊስና የልዩ ኃይል አባላት እንዲሁም በልዩ ስሙ "ሣምሪ" ማንም ሰው ከቤት እንዳይወጣ ትዕዛዝ አስተላለፉ። ከቀኑ 5፡00 ጀምሮ በአብዛኛው የዐማራ ብሔር ተወላጆች የሚኖሩበት ልዩ ስሙ "ግምብ ሰፈር" በሚባለው አካባቢ ደግሞ ከ 9፡ዐዐ ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2፡00 ስዓት አካባቢ የትግራይ ተወላጅ የሆኑና ያልሆኑ ሰዎችን ለመለየት መታወቂያ በማየት እና በትግረኛ ሲያናግሯቸው መልስ መስጠት የማይችሉ ዐማሮችን ለይተው ጭፍጨፋውን
በገጀራ፣ ጩቤ፣ ፈራድ (ጥረቢያ) እና በገመድ በማነቅ ጀመሩ።
ዐማሮችን በጉልበታቸው እንዲንበረከኩና አንገታቸውን ወደ መሬት እንዲያቀረቅሩ በማድረግ አንገትና ጭንቅላታቸውን እጅግ አሰቀቂ በሆነ መንገድ በመቀጥቀጥ የጅምላ ግድያ
ፈጸሙባቸው። የሟቾችን አስከሬን በትራክተር በመጫን ከከተማው ውጭ ባሉ ገደላማ ቦታዎች እየወሰዱ በጅምላ ደፏቸው።
በወልቃይት ማይካድራ ከተማ ዐማራን መሰረት ያደረገ በተፈፀመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ 1 ሺህ 600 በላይ ዐማሮች ተገድለዋል። አንዲት ሴት በአማካኝ ከ8 እስከ 10 በሆኑ የትግራይ ሰዎች አሰቃቂና አረመኒያዊ በሆነ መንገድ ተደፍራለች፤ ሕጻናትም ያለ ወላጅ ቀርተዋል።
ይህ ቀን መቼም የሚዘነጋ አይደለም!
3.3K viewsedited 07:53