2022-10-13 11:15:46
ለ 13000 ቁጥር የተጠጋ ተማሪ በሙሉ ኮራጅ ነው ብሎ ብይን ሰጥቶ እነኚህን ተማሪዎች በሙሉ በ slanders and insult ከዚያ አለፍ ሲልም ከማህበረሰብ ስነ ልቦና ጋ ለማማያዝ የሚደረገው ጥረት በጣም የሚያሳዝን ነው።
ተማሪዎቹ ፈተና አንወስድም ብለው ማቋረጣቸው ስህተት የመሆኑን ያክል ወደዚህ ውሳኔ የገፋቸውን ሰበብ ከመርመርና ከማጥናት ይልቅ ለምን ፈተናውን አልኮረጅንም በሚል ሰበብ ነው ፈተና ያቋረጡት በሚል ስላቅ፣ስድብና ዘለፋ ጉዳዩን ከማጣጣል ይልቅ መንስኤውን ለማወቅ መጣርም ግዴታ ነበር።
በዚህ መካከል ፈተናውን ባቋረጡ ተማሪዎች ዙሪያ ችግሩን ከመውቀስና ልክ እንዳልሆነ ከመግለፅና ከመገሰፅ ባሻገር ዘለፋ፣ስድብ፣ማበሻቀጥና ራስን መስደብ የተስተዋለው በኛው ወገን መሆኑ በጣም አሳሳቢ ነው። ተማሪዎቹ ፈተናውን ላለመውሰድ ጥለው መውጣታቸውን መውቀስ የሞራል ልእልና ተደርጎ ሊወሰድ ቢችልም ከዚያ ባለፈ በተማሪዎች የማህበራዊ ስብእና ላይ ለመቀለድና ለመዝለፍ ይሄን ያክል መቁነጥነጥ የሞራል ልእልናን ማሳያ ልክም አይደለም።
በዚህ መካካል የአማራ ምሁራን ይሄን አጋጣሚ ተጠቅመው በአማራ ክልል የተጠቂነት ፖለቲካ (victimhood politics) ሰለባ
መሆንና ይህም አዋጪ አለመሆኑን ለማጉላት አንዱ በአንዱ ላይ ሆኖ ነጥብ ለማስቆጠር እየተላፉ ነው። ለነኚህ ሰዎች የምንጠይቀው ጥያቄ:–
> ይሄን ጉዳይ በመገንዘብ ለህዝብ የሚሆን ፖለቲካዊ መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ በአማራ ህዝብ ላይ መከራ እያደረሱ ያሉ አካላቶችን የልብ ልብ እየሠጠ ያለው የብልፅግና መንግስት ስር አድራችሁ እናንተ ራሳችሁ ለአማራ ህዝብ መከራ መሳሪያ እያቀበላችሁ አይደለም ወይ?
> ህዝባችን የ victimhood politics ሰለባ ሆኗል ካላችሁ መፍትሄው ለህዝባችን የ victimhood politics ሰለባ መሆን አስተዋፅኦ እያደረገ ካለው መንግስት ስር መርመጥመጥ ነው መፍትሄው ወይስ የጠራ የፖለቲካ ሪፎርም ይዞ ህዝብን ማታገል?
> ልትነግሩን የፈለጋችሁት ከብልፅግና ጋ ወንድማማች በመሆን የአማራ ህዝብን መሰረታዊ የፖለቲካ ችግር መቅረፍና መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ከሆነ ብአዴን 27 አመት፣ አዴፓ በአምስት አመት ውስጥ ምንም የቀየሩት ነገር የለም። We can't count on you for the reason that you won't be any different than #ADP.
@BruhDailyNews
2.3K viewsedited 08:15