Get Mystery Box with random crypto!

ብሩህ ወቅታዊ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ bruhdailynews — ብሩህ ወቅታዊ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ bruhdailynews — ብሩህ ወቅታዊ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @bruhdailynews
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.10K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-11-10 10:53:03
2.9K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 10:38:34 ጀኔራሉ ተፈራ ማሞ

የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞ ትላንት ጥቅምት 30/2015 ዓም ምሽት አምስት ሰዓት ለነበራቸው በረራ  ቀደም ብለው ሁለት ሰዓት ለህክምና ወደ አሜሪካ ሊሄዱ  ሲሉ ከኤርፖርት መመለሳቸው እና ከሀገር እንዳይወጡ ታግደዋል።
ምክንያቱ ለጊዜው አልታወቀም።

https://www.youtube.com/channel/UC2DGN4BCp6bID3zZUfTMoAw?sub_confirmation=1
3.1K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 21:04:25 ኬኒያ  ናይሮቢ

የኢትዮጵያ መንግሥትና የሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች ናይሮቢ ላይ በዝግ እያካሄዱት ያለው ውይይት ነገ ሀሙስ እንደሚጠናቀቅ ከኬኒያ ከዲፕሎማቲክ አካላት የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ስለውይይቱ መጠናቀቂያ ቀን ፍንጭ ሰጥተዋል።ዛሬ ወይም ነገ ይጠናቀቃል ብለው ነበር።

አሁን ምሽት ከኬኒያ እየወጡ ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የጦር መሪዎቹ ንግግር ዋና ዋና ጉዳዮች ዛሬ ተጠናቀዋል።ነገ በቀሪ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረው መግለጫ ያወጣሉ ተብሏል።
ፕሪቶሪያ ስምምነት የተፈፀመበትን አጀንዳ ለመተግበርምየሚያስችሉ የአፈፃፀም መርሃ ግብሮች መዘጋጀታቸው ታውቋል።
1.2K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 12:02:25 #አሸባሪው ህወሃት ዳግም ጦርነት ቀሰቀሰ፦ ትግራይ ክልል ውስጥ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ትናንትና ዛሬ  በአበይ አዲ ተንቤን እና ማይጨዉ አካባቢ የአሸባሪው ህወሀት ታጣቂዎች ጦርነት እያካሄዱ መሆኑ ታውቋል። በVideo ለማየት፦ https://www.youtube.com/channel/UC2DGN4BCp6bID3zZUfTMoAw?sub_confirmation=1
3.0K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 08:26:51 ቶሌ ቀበሌ በሸኔ ጥቃት ሊፈጸምብ ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገለጹ!

ባለፈው ዓመት ሰኔ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች የተገደሉባት ቶሌ ቀበሌ ነዋሪዎች ዳግም ተመሳሳይ ጥቃት ሊፈፀምብን ይችላል በሚል ስጋት አካባቢያቸውን ለቀው መውጣታቸውን ገለጹ።

ባለፈው ዓመት ሰኔ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች የተገደሉባት ቶሌ ቀበሌ ነዋሪዎች ዳግም ተመሳሳይ ጥቃት ሊፈፀምብን ይችላል በሚል ስጋት አካባቢያቸውን ለቀው መውጣታቸውን ገለጹ።

ከአራት ወራት በፊት ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት ሰይሞ ሸኔ በሚል የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 400 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጾ ነበር።

በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ ነዋሪዎችን ኢላማ አድርጎ በነበረው ጥቃት በርካታ ሴቶችና ህጻናት ሰለባ በሆኑበት በዚያ ጥቃት የተገደሉት ነዋሪዎች ቁጥር 338 መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ መግለጹ ይታወሳል። 
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ይህ ጥቃት ከተፈጸመ ከጥቂት ወራት በኋላ የአማር ብሔር ተወላጅ የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተመሳሳይ ጥቃት ሊፈጸም ይችላል በሚል የደኅንነት ስጋት ከቶሌ ቀበሌ ተፈናቅለው መውጣታቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቀበሌው ነዋሪዎች በአካባቢው የነበረው የፌደራል መንግሥቱ የፀጥታ ኃይሎች እንዲወጡ እንደነገሯቸውና አርብ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ተነስተው ለሰዓታት በመጓዝ በምሥራቅ ወለጋ በሚገኘው አርጆ ጉደቱ ወደተባለ አካባቢ መሸሻቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የሁለት ልጆች እናት የሆነች ሴት ከዚህ ቀደም ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በስፍራው የፌደራል ፖሊስ ተሰማርቶ እንደነበረ ገልጻ፣ ባለፈው ዓርብ ጥቅምት 25/2015 ዓ.ም. ከቦታው እንደሚለቁ ነግረውን “ሕይወታችሁን ለማትረፍ ውጡ እንሸኛችሁ” አሉን ስትል ትናገራለች።

ሌላኛው የቶሌ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው እና የአራት ልጆች አባት የሆነው ግለሰብ እንደገለጸው፣ በስፍራው ሰፍረው የነበሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት ከእኩለ ለሊት በኋላ 9 ሰዓት ላይ መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመምጣት አካባቢውን ጥለው እንዲወጡ እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግሯል።

“ከእንቅልፍ ቀስቅሰው ተነሱ አሉን። የምናውቀው ነገር የለም በእግር ተጉዘን አምስት ሰዓት አርጆ ደረሰን” የሚለው ነዋሪው ከቀያቸው በድንገት በመውጣታቸው ምንም ነገር ሳይዙ መውጣታቸውን ያስረዳሉ።

ከስድስት የቤተሰብ አባላቷ ጋር ከቶሌ ቀበሌ የወጣች ሌላ እናት ደግሞ “ከዚህ በፊት ብዙዎች እዚያው ከፊታችን ታርደውም፣ ተቃጥለውም ሲገደሉ ስላየን ሕይወታችንን ለማዳን ስንል ወጣን” ስትል ትናገራለች።

ከዚህ በፊት በቶሌ ቀበሌ በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ የተፈጸመው የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጥበቃ ባለማደረጋቸው ነው ተብሎ ነበር።

     ( ቢቢሲ አማርኛ ) 
3.3K views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 14:00:01 ህወሓት ትላንትም ዛሬም ነገም #አሸባሪ ነው። ትጥቅ ፈታ አልፈታ ያው በአማራ ህዝብ ላይ ጀኖሳይድ የፈጸመ #አሸባሪ ነው። ህልውናው ማክተም ያለበት ሰው በላ ድርጅት ነው። @BruhDailyNews
1.7K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 13:13:24 ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የተፈፀመ " የድሮን  " የለም

" ... ከጌታቸው ጨምሮ ከራሳቸው ከTPLF ሰዎች አጣርቻለሁ ያ የተነገረው የድሮን ጥቃት የሚባለው ውሸት ነው "  አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የተፈፀመ " የድሮን " የለም ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።

ይህን የተናገሩት " የኢትዮጵያ ሚዲያ ሰርቪስ (ኢ ኤም ኤስ) " ለተባለና በኢንተርኔት ላይ ለሚሰራጭ ሚዲያ ነው።

" በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ አንዳንድ ክስተቶች ተፈጠሩ ሲባል መረጃ እንለዋወጣለን። ስምምነት ተፈራርመናል ስለዚህ የስልክ ችግር የለብንም። " ያሉት አምባሳደር ሬድዋን በኬንያ ናይሮቢ ፤ ከእነ አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከወታደራዊ አዛዦቹም ጋር መነጋገራቸውን እና የድሮን ጥቃት ተፈፀመ የተባለው ውሸት መሆኑን  ገልፀዋል።

" #ስምምነት_ከመፈረሙ_በፊት የነበረ (incident) ክስተትን ከስምምነት በኃላም ለማምጣት የሚሞክሩ አሉ። በዚህ ግጭት ውስጥ ገንዘብ ይከፈላቸው የነበሩ ጥሩ ሃብት ያፈሩበት ሰዎች አሁንም ግጭት እንዲቀጥል የማቀጣጠል ፍላጎት ያላቸው እንዳሉ እናያለን ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ፤ ከውስጥም በተለያየ መንገድ ስሜታዊ የሆነ ሰው ሊያራግበው ይችላል የትግራይ ሚዲያም ፤ የወያኔ ቴሌቪዥንም ሰርተውት ነበር" ብለዋል።

" በእኛ በኩል #ንግግሮችን ለማስተካከል ሞክረናል " ያሉት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን " አሁን ሰው ተስፋ እንዳያድርበት ወደፊትም ይሄን ነገር እንዲያመጣ ነው እንጂ ቁርሾውን በ 'Transitional Justice' በሂደት ይሄዳል ፣ በምህረት የሚታለፈው ይታለፋል መፀፀቱ ከታየ እውነት ከተናገረ ፤ የግድ በፍርድ ቤት ማለቅ ያለበት ከባድ ወንጀል የሆነ ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳል፣ ተጠያቂነትንም የማህበራዊ ህክምናንም ትስስርንም እኩል የሚያማክል መንገድ አለን እሱ ይደረሳል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ያልነበረ ነገር እያጋጋሉ የውሸት ሚፅፉ አሉ ከራሳቸው ከTPLF ሰዎች አጣርቻለሁ ጌታቸውን ጨምሮ ያ የወጣው መግለጫ (የGSTS መግለጫ ማለታቸው ነው) የጋራቸው አቋም እንዳልሆነ፣  የተባለው የድሮን ጥቃትም ውሸት እንደሆነ አጣርቻለሁ " ብለዋል።

በስናይፐር ፣ በድሽቃ አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ ሊያጋጥም እንደሚችል የጠቆሙት አምባሳደሩ " ይሄ የተለመደ ነው፤ የሰላም ፊርማ ሲፈረም የተወሰኑ ቀናት እየሞተ እስከሚሄድ ድረስ የሰማም በስሜት ተውጦ እምቢ ብሎ ሊያደርገው ይችላል፣ ሳይሰማ የሚቀርም ያደርገዋል፤ ነገር ፈልጎ ነገሩ እንዲበላሽ  የሚፈልግም ሊያደርገው ይችላል በታንክ እና በመድፍ እንድካልሆነ ድረስ በድሽቃ እና በስናይፐሮች የሚደረግ አንዳንድ የተኩስ ምልልሶች እዚህም እዚያም ያጋጥማሉ " ሲሉ አስረድተዋል።

" ሰው ይሄንን (አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚያጋጥሙትን የተኩስ ልውውጦችን ማለታቸው ነው) ለመዘገብ የሚቸኩለውን ያህል ከTPLF ካምፕ ወደኛ ወታደር መጥቶ አብሮ በልቶ ፣ ... ፣ ተጫውቶ ፣ ፎቶ ተነስቶ የሚመለሰውን ለመዘገብ ፍላጎት የላቸውም እኛ ነን መግፋት ያለብን የሚል ነገር በሁለቱም በኩል አለ ካማንደሮቹ ይሄን ጉዳይ መልክ ካስያዙት በኃላ ሁሉ። የራሳቸውን Discipline ያሲዛሉ " ሲሉ ተደምጠዋል።(ቲክቫህ)
1.9K views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 20:09:12 ናይሮቢ-ኬኒያ አሸባሪው ህወሃት እና መንግስት

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ናይሮቢ ላይ የተናገሩት ፦

"የቴሌኮም የኢነርጂ እና የባንክ አገልግሎቶችን መልሰን ማገናኘት አለብን።ከዚያ በፊት ግን ሰዎቻችን በቅድሚያ ምግብ እና መድኃኒት ይፈልጋሉ። ይህን ለማፋጠን እየሞከርን ነው።ክልሎችን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች በባለፉ ጉዳዮች ከመዘፈቅ ይልቅ ተስፋ እንዲፈነጥቁ እና መጪውን ጊዜ በጸጋ እንዲቀበሉ መንግስት እያበረታታ ነው። "

አቶ ጌታቸው ረዳ (ከህወሓት) ፦

" በስምምነታችን የተካተቱ ብዙ መደረግ ያለባቸው ነገሮች አሉ።ከእነዚህ ተግባራት መካከል የአገልግሎቶች መጀመር አንዱ ነው።የአገልግሎቶቹ ቁጥር ከፍ ሲልም በተደራዳሪ ወገኖች መካከል የሚኖረው መተማመን እና ግንኙነት አብሮ ይጨምራል፤ በሰዎች አዕምሮ ውስጥም ተስፋ ይዘራል ፤ ለማስፈን እየሞከርን ያለውን ሰላም የበለጠ ያጠናክራል። ... እኛ የገባነውን ቃል ለማክበር ቁርጠኛ ነን። "

ኡሁሩ ኬንያታ ፦

<<በፕሪቶሪያ ጀመርን፣ መንገዳችን እየተጠጋ ፤ አሁን ናይሮቢ ነን ፣ በሚቀጥለው ጊዜ ስብሰባችን መቐለ እንደሚሆን ተስፋ አድርጋለሁ ፤ በመጨረሻም አዲስ አበባ ላይ አብረን እናከብራለን። ይህ ጸሎታችን ፣ ተስፋ የምናደርገው እና የምንፈልገው ነው።>>

Tikvah
1.6K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 17:58:32 ህወሓት ትላንትም ዛሬም ነገም #አሸባሪ ነው።
ትጥቅ ፈታ አልፈታ ያው በአማራ ህዝብ ላይ ጀኖሳይድ የፈጸመ #አሸባሪ ነው።

ህልውናው ማክተም ያለበት ሰው በላ ድርጅት ነው።

@BruhDailyNews
2.3K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 14:39:42
#አሸባሪው ህወሃት እና የኢትዮጵያ መንግስት በናይሮቢ!

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የህወሓት ከፍተኛ የጦር አመራሮች ለዉይይት በኬንያ መዲና ናይሮቢ ተገናኝተዋል፡፡

የፌደራል መንግሥቱ መከላከያ ኃይል ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ከህወሓት በኩል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ረፋድ ላይ በናይሮቢ ንግግር መጀመራቸው ታወቋል።

የጦር አመራሮቹ የተገናኙት ከቀናት በፊት በሁለቱ አካላት መካከል በፕሪቶርያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት የማስፈጸም አንዱ አካል በሆነው የትጥቅ ማስፈታት ሂደት ላይ ለመነጋገር ነው።

የንግግሩን መጀመር ይፋ በተደረገበት መድረክ በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር ድርድሩን ሲያስተባብሩ ከነበሩት መካከል የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሱንጉን ኦባሳንጆ እና የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ተገኝተዋል።

ይህ ውይይት በቀጣይ ቀናት ቀጥሎ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
(EthioFM)

በVideo ለማየት፦

https://www.youtube.com/channel/UC2DGN4BCp6bID3zZUfTMoAw?sub_confirmation=1
2.8K viewsedited  11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ