Get Mystery Box with random crypto!

ብሩህ ወቅታዊ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ bruhdailynews — ብሩህ ወቅታዊ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ bruhdailynews — ብሩህ ወቅታዊ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @bruhdailynews
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.10K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 27

2022-08-29 21:46:35 አሁን በሮቢት ደቡብ አቅጣጫ "ቃሊም" ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ከባድ ውጊያ እየተካሄ መሆኑ ተሰምቷል።

@BruhdailyNews
5.5K viewsedited  18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:56:40 ሮቢት፣ጎብዬ፣ጎርባ

ጥምር ጦሩ በሮቢትና ጎብዬ አቅጣጫ ጎርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከውሃት ኃይል ጋር አሁንም ውጊያ ላይ እንደሆነ ታውቋል።ይህ በዚህ እንዳለ የህውሃት ወራሪ ኃይል ከጎብዬ ደቡብ አቅጣጫ ፣ዱርለበስ፣አላውሃ እና ማመጫ ተብለው የሚጠሩትን አካባቢዎች ተጠቅሞ ወደ ወልዲያ ለመምጣት ዕቅድ እንዳለው ታውቋል።ይህንን የተረዳው ጥምር ጦሩ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተሰምቷል።

በህዝባዊ ማዕበል ልክ እንደከዚህ በፊቱ ወልዲያን ድጋሜ ለመውረር ያስቀመጠውን ዕቅድ መክቶ ለማክሸፍ ወሳኝ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ በመሆኑ ይሄው እየተፈፀመ እንዳለ ታውቋል።
በየትኛውም ሂደት መዘናጋት አያስፈልግም።ነቅቶ ጥምር ጦሩን ማገዝ ይገባል።

@BruhdailyNews
@BruhdailyNews
5.5K views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:31:40 Channel photo updated
15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:52:05
ሕወሓት በአፍሪካ ሕብረት ወደሚመራው የሰላም ድርድር እንዲመጣ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ተጠየቀ

ሕወሓት በአፍሪካ ሕብረት ወደሚመራው የሰላም ድርድር እንዲመጣ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ በአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት ጠየቀ፡፡

ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ሕወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የከፈተውን ጦርነት እንዲያቆም ግፊት ማድረግ ይገባዋል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለሰላም ስምምነት ያለማቋረጥ ጥሪ ያደርጋል ሲልም ጽሕፈት ቤቱ በትውተር ገጹ አስፍሯል፡፡

ይሁን እንጂ ሕወሓት ሌላ ግጭት ለመፍጠር በመምረጥ ወደ ጦርነት መግባቱን በመልዕክቱ ጠቁሟል፡፡

@BruhDailyNews
@BruhDailyNews
5.2K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:17:44
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ባደረባቸው በስጋት ምክንያት ግቢያቸውን ለቀው የወጡ ተማሪዎችን በሚመለከት ውሳኔ አሳለፈ።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በ22/12/2014 ዓ.ም ባደረባቸው ስጋት ምክንያት የተነሳ ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።

በዚህ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1ኛ. የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ #በቀጣይ_ዓመት ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ ይሆናል።

2ኛ. የክረምት መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ የተጀመረውን ትምህርትና ፈተና ለማጠናቀቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ መስከረም 03/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@BruhdailyNews
@BruhdailyNews
5.0K views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:40:44
አስደንጋጭ መረጃ ቆቦ

የህወሓት ታጣቂዎች በቆቦ ከተማ ንጹሃንን መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ!

ቆቦ ከተማን የተቆጣጠሩት የህወሓት ታጣቂዎች ንጹሃንን መግደላቸውን የራያ ቆቦ ወረዳ ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ገለጹ።መንግስት የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን መልቀቁን መግለጹን ተከትሎ የህወሃት ታጣቂዎች በራያ ቆቦ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን መገደላቸውን ነዋሪዎቹ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል።

ለደህንነታቸውን ሲባል ድምጻቸውን ቀንሰው በስልክ ያነጋገሩን ግለሰብ፤ በከተማዋ ወጣቶች መገደላቸውን ተናግረዋል።በቆቦ ከተማ ስልክ ይዞ መገኘት እንደሚስገድል የተናገሩት አስተያየት ሰጭዋ፤ የተገደሉ ወጣቶች አስክሬን አሁንም አለመነሳቱን ተናግረዋል።አሁን ላይ በቆቦ ከተማ በተለያዩ መንገዶች ላይ የተገደሉ ወጣቶች አስክሬን እንዳለ የተናገሩት ደግሞ ሌላ አስተያየት ሰጭ ናቸው። አሁን ባለው ሁኔታ አስክሬን ማንሳት እንዳልተቻለ የተገለጸ ሲሆን አሁንም ውጊያ እንዳለ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ እና አርሶ አደሮቹ “ፋኖ ናችሁ፤ የብልጽግና አባል ናችሁ፤ ሚሊሻ ናችሁ” በሚል ግድያ እየተፈጸመ እንደሆነ ገልጸዋል።በሮቢት ከተማ ብቻ ሁለት ወጣቶች መገደላቸውን ከስፍራው ወደ ወልዲያ የመጣ አንድ አስተያየት ሰጭ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግሯል።

Via Al Ain
@BruhDailyNews
@BruhDailyNews
2.1K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:08:22
የአማራ ክልል የ2014 ዓ.ም. የ8ኛ ክፍል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።በዚህ መሠረት በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ማለፊያ ውጤት ለወንዶች 39%፣ ለሴቶች ደግሞ 38% እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች 37% እንዲሆን ተወስኗል።

፨ዝርዝሩን ከፎቶው ይመልከቱ

ምንጭ፡የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ

@bruhdailynews
@bruhdailynews
5.6K views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:03:07 የአየር ኃይል አካዳሚ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመረቀ

የኢፌድሪ አየር ኃይል አካዳሚ በኤሌክትሮኒክስ፣ በአውሮፕላን አካል እና ሞተር ጥገና እንዲሁም በመሰረታዊ የአቪዬሽን ሙያ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ "አየር ኃይሉ መክፈል የሚገባውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍሎ ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ለማድረግ በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል።" ብለዋል።

አየር ኃይሉ ከሀገራዊ ለውጡና ከተቋማዊ ሪፎርሙ በኋላ የዝግጁነት አቅሙን ለማሳዳግ በሰው ኃይል ግንባታ፣ በዘመናዊ ትጥቆች እና ቴክኖሎጂ ብሎም ሰፋፊ የውጊያ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት በትኩረት መስራት መቻሉንም ገልፀዋል።

ዋና አዛዡ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎች ወቅቱን በመረዳትና የተማሩትን ሙያ ወደ ተግባር በመቀየር ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

አየር ኃይሉ መክፈል የሚገባውን መስዋዕትነት ሁሉ በመክፈል ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ለማድረግ በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል ሲሉም አረጋግጠዋል ።

ከተመራቂ ሙያተኞች መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት ዘመኑ የሚጠይቀውን የአቪዬሽን እውቀት መቅሰማቸውን ጠቁመው በዚህም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ በማድረግ ሀገራዊ ግዳጃቸውን በብቃት ለመወጣት ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@BruhDailyNews
@BruhDailyNews
1.9K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:57:17
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጄሪያ ዋና ከተማ በሚገኘው የሰማዕታት ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ ስርዓት አከናውነዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጄሪያ ዋና ከተማ በሚገኘው የሰማዕታት ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ ስርዓት አከናውነዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጀሪያ እያደረጉት ባለው ይፋዊ የስራ ጉብኝት በርዕሰ መዲናዋ አልጀርስ የሚገኘውን የሰማዓታት መታሰቢያ ሙዚየም ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስፍራው የአበባ ጉንጉንም አኑረዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትናነትናው እለት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አልጀሪያ መግባታቸው ይታወሳል።

@BruhDailyNews
@BruhDailyNews
1.9K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:13:55
የወልድያ ከተማ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እንደቀጠለ ነው።

#ወልድያ

ወልድያ ከተማ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እንደቀጠለ መሆኑን የወልድያ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የተለያዩ ሚዲያዎች እና የፖለቲካ ተንታኝ ነን የሚሉ የውጭ አካላት በማህበራዊ ሚዲያው ወልድያን በተመለከተ ሀሰተኛ ዜና እያሰራጩ ይገኛሉ።

" ከወልድያ አመራሩ ወጥቷል፣ ወልድያንም ህወሓት ይዟል " የሚሉ መረጃዎችን ቢያሰራጩም ሁሉም ሀሰት መሆኑና ህዝቡን ለማሸበር የሚሰራ ስራ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ግጭት በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ አይነት በሀሰት ህዝብን የማሸበር ስራ ሲሰራ፣ ህዝብን ለማስደንገጥ ብዙ ጥረቶች ሲደረጉና በዚህ ሳቢያ ብዙ መመሰቃቀል ሲፈጠር እንደነበር አይዘነጋም።

እስካሁን ድረስ በወልድያና በቀጠናው ባለው ሁኔታ ከወልድያ ከተማም ይሁን ከጅቡቲ ወደብ የሚነሱ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን ከተለመደው የዕለት ተዕለት ጉዟቸው ያስተጓጎላቸው ሁኔታ እንዳልተከሰተ ከወልድያ ከተማ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፤ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከሚማሩ ተማሪዎች ከወቅቱ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ስጋት አድሮባቸው ግቢያቸውን ለቀው የወጡ፤ የትራንስፖርት አጥተውም በእግር የተጓዙ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።

አንዳንድ መልዕክት የላኩ የግቢው ተማሪዎች ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ " ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ እንዲደረግ ፤ አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ እነሱም ቤተሰብም ጭምር ጭንቀት ላይ በመሆኑና በዚህ ሁኔታ ትምህርትን በንቃት መከታተል ስለሚያስቸግር ተቋማቸው መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል።

በተማሪዎቹ ስጋት ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ ለማግኘት እንጥራለን።

#ወልድያ_ከተማ_ኮሙኒኬሽን
@BruhDailyNews
@BruhDailyNews
1.7K views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ