2022-09-07 10:02:16
የፌደራሉ መንግሥት ‘ሸኔ’ ብሎ የሚጠራው እና በሽብርተኝነት የፈረጀው ቡድን በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኘው አርጆ ደዴሳ ስኳር ፋብሪካ ላይ ጥቃት ማድረሱ ተገለጸ።
ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን በምስራቅ ወለጋ ዞን የሚገኘውን ፋብሪካ ለሰዓታት ተቆጣጥሮ ከቆየ በኋላ ንብረት ማውደሙን እና ዘረፋ መፈጸሙን የስኳር ኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊ ረታ ደመቀ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በዚህ ጥቃት ስምንት መኪኖች በእሳት የጋዩ ሲሆን፣ ስድስቱ የአርጆ ደዴሳ ተሸከርካሪዎች ሲሆኑ፤ አንዱ ደግሞ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣ ሌላኛው ተሸከርካሪ ደግሞ በፋብሪካው የነበረ የኮንስትራክሽን ድርጅት መሆኑን አቶ ረታ ጨምረው ተናግረዋል።
ታጣቂ ቡድኑ ካደረሰው ጉዳት በተጨማሪ ዘረፋ መፈጸሙን አቶ ረታ ጨምረው ተናግረዋል።
“የሠራተኞችን ሞባይል፣ ጫማ ይዘው ሄደዋል። ቁጥሩ ገና እየተጣራ ያለ ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ወስደዋል። ከወሰዷቸው ዕቃዎች መካከል ሃርድ ዲስክ እና ፕሪንተር እንዳለበት ከፋብሪካው ሪፖርት ደርሶናል” ብለዋል።
(ቢቢሲ አማርኛ)
@BruhDailyNEWS
@BruhDailyNEWS
1.2K viewsedited 07:02