Get Mystery Box with random crypto!

ብሩህ ወቅታዊ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ bruhdailynews — ብሩህ ወቅታዊ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ bruhdailynews — ብሩህ ወቅታዊ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @bruhdailynews
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.10K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-11-02 20:10:40
ሰላም ለኢትዮጵያ ፣ሰላም ለሰፊው ህዝብ

@BruhDailyNews
3.3K viewsedited  17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 20:05:31 ሰበር መረጃ-የሰላም ስምምነት

በመንግስትና በህወሃት መካከል የተደረሰዉን የሰላም ስምምነት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የህወሓቱ ተወካይ አቶ ጌታቸዉ ረዳ በፊርማቸዉ አረጋግጠዋል፡፡

አምባሳደር ሬድዋንና አቶ ጌታቸዉ ረዳ ስምምነት ላይ የተደረሱባቸዉን ነጥቦች በጋራ አቅርበዋል፡፡

ሁለቱ ተወካዮች ፊርማቸዉን ካኖሩ በኋላ እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል።

ቁልፍ የስምምነት አጀንዳዎች፦

ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን፤ በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ፤
- ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ 24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር እንደሚያደርጉ፤

- ስምምነቱ በተፈረመ 5 ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ፤
- የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ ህወሓት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል፤
- ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል፤
-በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል።
- በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል፤
- የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል።
- መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል።
- ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።
- የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፤
- ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል።
- እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈጹ ግለሰቦች ካሉ በሀገሪቱ ሕግ የሚጠየቁ ይሆናል።
3.3K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 17:50:23 መረጃ

አድዋ ከተማ ከአንድ የእምነት ተቋም በመውጣት ተኩስ በመክፈት ነዋሪውን ለመረበሽ የሞከሩ የህውሃት ታጣቂዎች በሀገር መከላከያ ሰራዊቱ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተስምቷል።

የህውሃት ታጣቂዎች መቀሌ የሚገኘውን የአሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ከሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ለማስለቀቅ ውጊያ ሲያደርጉ መዋላቸው ታውቋል።

ዛሬ ጠዋት ህውሃቶች መደበቂያ ዋሻ ለማግኘት ከአቢአዲ ወደ ተንቤ አቅጣጫ ውጊያ ሞክረው ነበር ከሰዓት በኋላ ግን ጦርነቱ መቆሙ ተሰምቷል።

በኮረም ግንባር የማይጨው አካባቢ ውጊያ ከከተማው አቅራቢ ወደ ፊት መሄዱን ለማወቅ ተችሏል።ጥምር ጦር ማይጨው ከተማ ለመግባት አካባቢውን ማጥራት ብቻ እንደሚቀረው ተጠቁሟል።

@BruhDailyNews
6.0K views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 17:09:54
አሉላ አባነጋ ኤርፖርት

ህወሃት የአሉላ አባነጋ ኤርፖርት ውስጥ ምሽግ ሰርቶ ነው እየተዋጋ ያለው፣አየር ማረፊያው እንዳይጎዳ መከላከያ ሰራዊቱ ጥንቃቄ የተሞላበት ውጊያ እያካሄደ ነው። የአየር ማረፊያውን ለመያዝ ትናንት የተጀመረው ውጊያ እንደቀጠለ ነው።ያሰለፋቸው ታጣቂዎች ሰሜን ዕዝን የመቱ እና ነባር የልዩ ሃይል አባላትን ነው። የመጨረሻ ያለውን ሀይል እየተጠቀመ ይመስላል።
@BruhDailyNews
5.9K views14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 17:04:36
የሠላም ንግግሩ ተጀምሯል።

እስከ የፊታችን እሁድ ድረስ ይቀጥላል።

በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት በፌደራሉ መንግስት እና በህወሓት መካከል የሚደረገው የሰላም ንግግር በዛሬው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ተጀምሯል፡፡

ዛሬ የተጀመረው የሰላም ንግግር እስከ የፊታችን እሁድ ድረስ እንደሚዘልቅ ሮይተርስ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ስሪል ራማፎሳ ቃል አቀባይ ነግረውኛል ሲል አስነብቧል፡፡

ቃል አቀባዩ ቪንሰንት ማግዌኛ በሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት እየተፋለሙ ያሉት ኃይሎች በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር የሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ፑምዚሌ ማላምቦ-ናኩክ እንደሚያስተባብሩት ተናግረዋል።

የሰላም ንግግሩ ፍሬ እንዲያፈራ ለአስተባባሪዎቹ መልካም ምኞታቸውን የገለፁት ቃል አቀባዩ፤ “የድርድሩ ውጤት ለመላው ኢትዮጵያውያን ዘላቂ ሰላም እንዲያመጣ ደቡብ አፍሪካ ምኞቷን ትገልጻለች” ብለዋል።

ከተጀመረ ኹለት ዓመት ሊሞላው ቀናት የቀሩትን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለመቋጨት፤ ይህ በፕሪቶሪያ የሚካሄደው የሰላም ንግግር የመጀመሪያው ይፋዊ የንግግር መድረክ ሲሆን፤ የውይይቱ በሰላም መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ወሳኝ መሆኑ እየተነገረ ያገኛል።

በዚህ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍም የፌደራል መንግሥት እና በህወሓት ተወካዮች ትናንት እና ከትናንት በስቲያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው ይታወሳል ሲል ሮይተርን ጠቅሶ አዲስ ማለዳ ዘግቧል።

@BruhDailyNews
6.5K views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 13:47:15 አርበኛ ዘመነ ካሴ

መንግስት አርበኛ ዘመነ ካሴን በወንጀል ጠርጥሬዋለሁ በማለት የጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ የቆየ ሲሆን በዛሬው እለት በ15/02/2015 በምርመራ መዝገቡ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ ለዐ/ህግ የተሰጠው ጊዜ ተጠናቋል ይህ ማለት በህግ አይን ዘመነ ካሴ ከዛሬ ጀምሮ ተጠርጣሪም ተከሳሽም አይደለም ይልቁንስ ከህግ ስርዓት ውጭ በመንግስት የታገተ ሰው ነው ማለት ነው። መንግስት ህግን ሊያከብር ይገባል።

የዘመነ ካሴ ጠበቃ ኅሩይ ባዩ ይህን ብሏል

@BruhDailyNews
5.8K viewsedited  10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 12:34:38 መቀሌ

ውጊያው መቀሌ ዙሪያ በመድረሱ በመቀሌ ከተማ ከፍተኛ የሆነ ስርዓት አልበኝነት እና ዝርፊያ እየተፈፀመ እንደሆነ ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ ከትናንት በስቲያ በመቀሌ ህወሃት በርካታ የመከላከያ ሬንጀር ለታጣቂዎቹ ሲያደል ውሏል። ለመቀሌ አቅራቢያ ኩይሓ አካባቢ ውጊያው እንደቀጠለ ነው።

@BruhDailyNews
5.8K views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 07:34:32
"ኦሮሞነት ከእስልምና በላይ ነው!"

ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ

@BruhDailyNews
5.8K views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 21:59:00 በአላማጣ የንፁሃን የጅምላ መቃብር ተገኘ።

አሸባሪውና ወራሪው የወያኔ ቡድን በራያ አላማጣ ንፁሃንን በግፍ እየገደለ የቀበረበት የጅምላ መቃብር በአላማጣ ከተማ ተገኝቷል።
የጅምላ መቃብሩ በኤክስካባተር የተቆፈረና በርካት ንጹሃን በጅምላ የተቀበሩነት እንደሆነ የአካባቢው የአይን እማኞች ተናግረዋል።
ወጣት ፈንታ ትኩዬ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ የጅምላ መቃብሩ የሽብር ቡድኑ አባላት የዘመቻ ሥራ አለ በሚል የጉልበት ሠራተኞችን ጭምር ወስደው መቃብር እንደሚያስቆፍሯቸው እና ምስጢር እንዳይወጣ በሚል ደግሞ በኤክስካባተር እንደሚቀብሩ ተናግሯል። ንጹሃንን በጅምላ ገድለው ቀብሩንም እራሳቸው በመረጡት ሰው ብቻ እንደሚያስፈፅሙና ምንም አይነት መረጃ እንዳያወጣ እንደሚያስጠነቅቁ ወጣት ፈንታው ገልጿል።
ሀዬሎም አሸብር የተባለ ሌላ ወጣት በበኩሉ ባለፉት 1 ዓመት ከአራት ወር ውስጥ በራያ አላማጣ እና በራያ ቆቦ አካባቢ በማንነታቸው ምክንያት ንጹሃን አማራዎች በግፍ እየገደሉ በጅምላ ይቀብሯቸው እንደነበር ምስክርነቱን ሰጥቷል።
በተለይም የሚቃወማቸውን እና ምስጢር የሚያውቅባቸውን ሰው እያፈኑ እንደሚሰውሩ የተናገረው ወጣት ሀዬሎም ከእነሱ በተቃራኒ የቆመውን የአላማጣን ሕዝብ ከጎናቸው ለማሰለፍ በማሰብ ሞርታር መሳሪያ በገበያ ላይ በመጣል በርካታ ንፁሃንን ጨፍጭፈው መንግሥት ነው በድሮን የገደላችሁ ከኛ ጋር ተሰለፉ ብለው ሲቀሰቅሱ ነበር ብሏል።
እየተሸነፉ ሲመጡ የራያ አላማጣ ሕዝብ ወጥቶ እንዲዋጋ ማስገደዳቸውን እና እያፈኑ መውሰዳቸውን የገለፀው ወጣት ሀዬሎም፤ አንሸነፍም እንጂ ብንሸነፍ እንኳን ባዶ መሬቱ ይቀራል እንጂ አንድ ሰው አይቀርም እያሉ ሲዝቱ እንደነበርም ተናግሯል።
ይህ ሁሉ የጅምላ መቃብር የተፈጠረው በአንድ ዓመት ከአራት ወር ውስጥ መሆኑን በመግለፅ ብዙዎችን ከእስር ቤት እያወጡ ገድለው እንደሚቀብሯቸው እና በቅርቡ ተሸንፈው ሊወጡ ሲሉም ሁሉንም እስረኞች ገድለው ሊቀብሯቸው ትላልቅ የጅምላ መቃብሮችን አዘጋጅተው እያለ በድንገት የወገን ጦር ሲደርስባቸው ተደናግጠው እንዳመለጡ ተናግሯል።
አቶ አሰፋ አባተ የተባሉ የዓይን እማኝ በበኩላቸው "የአማራ ማንነት ያላቸውን ገድለው በድብቅ ሲቀብሩ" እንደነበር ተናግረዋል።
በአካባቢው የመቃብር ስፍራ ስለመኖሩ ማንም ሰው እንደማያውቅ እና ምስጢራዊ እንደነበረ የተናገሩት አቶ አሰፋ በመቃብር ስፍራው ማንም ሰው ማለፍ የማይችልበት እንደነበርና የወገን ጦር አላማጣ ሲደርስ ሕዝቡ መመልከት ችሏል ነው ያሉት። ብዙ የተሰወሩ ወገኖቻችን እዚሁ ተቀብረው እንደሚሆን መገመት ይቻላል ብለዋል። መረጃው የአማራ ክልል ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ነው።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር

አሚኮ

@BruhDailyNews
5.8K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 21:58:54
በአላማጣ የንፁሃን የጅምላ መቃብር ተገኘ።
አሚኮ

@BruhDailyNews
5.1K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ