Get Mystery Box with random crypto!

Asham TV

የቴሌግራም ቻናል አርማ asham_tv — Asham TV A
የቴሌግራም ቻናል አርማ asham_tv — Asham TV
የሰርጥ አድራሻ: @asham_tv
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.58K
የሰርጥ መግለጫ

Asham Tv is a privately owned media company, based in Addis Ababa, Ethiopia, that provides news, Analysis, information and other programs.

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 12:32:36
በትግራይ ተቋርጦ የነበረው የሰብዓዊ ድጋፍ ዳግም መጀመሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

አሻም ዜና |ነሀሴ 25፣ 2014 ዓ.ም

የድርጅቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ(ኦቻ) ነሐሴ 29 ቀን 2022 እ.አ.አ. ባወጣው መግለጫ፣ ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ ከነሐሴ 24 2022 ጀምሮ የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጡን ገልፆ ነበር፡፡

ነሐሴ 30 ቀን 2022 የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱያሪች በሰጡት ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ኦቻ እንዳረጋገጠው የሰብዓዊ እርዳታዎች ዳግም መዳረስ ጀምረዋል፡፡

ኦቻ ባወጣው መግለጫ ”እኛ እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የፀጥታው ሁኔታ በፈቀደው መጠን ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡” ብሏል፡፡

ይህንኑ የኦቻ መግለጫ በንባብ ያቀረቡት ስቴፋኒ ዱያሪችም በአፋርና አማራ ክልሎች ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በአፋር ክልል ከያሎና ጉሊና ወረዳዎች በሺዎች የሚቆጡሩ ሰዎች በአካባቢው በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት ተፈናቅለዋል፤ ከአማራ ክልል አዋሳኝ በሆነው የጭፍራ አካባቢም በተመሳሳይ መልኩ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልፀዋል፡፡

በአማራ ክልል፣ በሰሜን ወሎ ዞን፣ በጃራ የመጠሊያ ጣቢያ ተጠልለው የነበሩ 30ሺህ ያህል ተፈናቃዮችም ለሁለተኛ ጊዜ መፈናቀላቸውን ተናግረዋል፡፡ በደቡብ ወሎ ዞን፣ ደሴ ከተማም መፈናቅሎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ሁሉም ተፋለሚ ሀይሎች ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ ህግጋትን መሠረት በማድረግ ንፁሃንና የንፁሃን መገልገያ የሆኑትን እንዲጠብቁ፣ ንፁሃን ደህንነታቸው ወደሚጠበቅበት ስፍራ እንዲሄዱ እንዲፈቀዱላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዮሐንስ አሰፋ
1.1K views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:31:54
ሕወሐት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ መክፈቱ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ

አሻም ዜና |ነሀሴ 25፣ 2014 ዓ.ም

አገልግሎቱ መግለጫው መንግሥት ለሰላም አማራጭ ዕድል ለመስጠት ሲል የሕዝብ ማዕበል አስነሥቶ ሕጻናትን፣ ወጣቶችንና አረጋውያንን ለመማገድ የመጣውን የአሸባሪው ሕወሐት ታጣቂ፣ በምሥራቅ አማራ በኩል በጀግንነት ሲከላከል መቆየቱን ገልጿል።

በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ ከፍቷል። ይሄንን የሕወሐት ወረራ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት በተሟላ ዝግጅትና በጽኑ ቁመና እየተከላከለ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ለሰላም የተዘረጋው እጅ በሕወሐት ዕብሪታዊ ወረራ ምክንያት እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁንም ያሳስባል ሲል በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

“ወገናችን የሆነው የትግራይ ሕዝብም ይሄንን የዕብሪት ወረራ በማውገዝ ሕወሐት ከሚያስከትልበት መከራ ራሱን ነጻ እንዲያወጣ ጥሪ እናቀርባለን”ብሏል፡፡
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
824 views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:31:46 ሂዩውማን ራይተስዎች ከሰኔ የጅምላ ግድያ የተረፉ የምዕራብ ወለጋ ነዋሪዎች ጥበቃ እየተደረገላቸው አይደለም አለ፡፡

አሻም ዜና |ነሀሴ 25፣ 2014 ዓ.ም

ዓለም አቀፉ የሰባዓዊ መብቶች ጥበቃ ተከራካሪ ድርጅት እ.አ.አ. ነሐሴ 31 ቀን 2022 ባወጣው መግለጫ ከባለፈው ሰኔ ወር በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን ቶሌ ቀበሌ ከተፈፀመው የጅምላ ግድያ የተረፉ የአካባቢው ነዋሪዎችን ለመጠበቅ የመንግስት ፀጥታ ሐይሎች የሰሩት ስራ አነስተኛ ብሏል፡፡

በሰኔው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን፣ አብዛኞቹ ህፃናትና ሴቶች በጅምላ መገደላቸውን ያስታወሰው ድርጅቱ ከዚህ ጥቃት የተረፉት ነዋሪዎች ግን ከሦስት ወራት በኋላም ቢሆን አስተማማኝ ጥበቃ እየተደረገላቸው አለመሆኑን ጠቁሟል፡፡

የሂዩውማን ራይትስዎች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላቲቲያ ባደር ” ታጣቂዎቹ መንድሮቹን አንድ በአንድ ሲወድሙ፣ በጭካኔ መላው ቤተሰብን ሲገድሉ በአቅራቢያው የነበሩ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ምንም ሳያደርጉ ቀርተዋል፡፡” ሲሉ የሰኔውን ጥቃት አስታውሰዋል፡፡

”የኢትዮጵያ መንግስት ተዓማኒነት ያለው ገለልተኛ አካል ማጣራት እንዲያደርግ፣ ለጥቃቱ ሀላፊነት የሚወስዱትን እንዲለይና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እርዳታ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡” ብለዋል፡፡

ከሰኔ እስከ ነሐሴ 2022 25 ሰዎችን በስልክ አነጋግሪያለሁ የሚለው ሂዩውማን ራይትስ ዎች 19ኙ የዓይን እማኞችና ቀሪዎቹ ደግሞ የጥቃቱ ሰለባዎች ዘመድ መሆናቸውን የጠቀሱለት ሲሆን መኖሪያቸውም ጉቲን፣ ጨቆርሳ፣ ሲልሳው፣ ቤገን ተሰኙ መንደሮች ናቸው፡፡

ከዓይን ምስክሮቹ፣ ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊትና በኋላ ከሳተላይት ተገኝተዋል ካላቸው ምስሎች በመነሳት የተገደሉት ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሰውኛል ብሏል፡፡

ያነጋገራቸውን የዓይን እማኞች ምስክር ያደረገው ድርጅቱ በወቅቱ ስለነበሩት ”አሰቃቂ” ጥቃቶች በዝርዝር አትቷል፡፡

ከጅምላ ግድያው የተረፉት ነዋሪዎች በአካባቢው በተደጋጋሚ በሚፈፀሙ ጥቃቶች የተነሳ ፍርሃት ውስጥ መውደቃቸውን፣ በቂ ጥበቃና ሰብዓዊ ድጋፍ አለመኖሩን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ የተሳም ብዙዎች የኦሮሚያ ክልልን ለቅቀው እየወጡ መሆኑን መግለጫው አመልከቷል፡፡

እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) መረጃ ከቶሌ ቀበሌ አራት ሺህ ስምንት መቶ(4800) እንዲሁም ከምዕራብ ኦሮሚያ ደግሞ ከአምስት መቶ ሺህ(500 000) በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ያመላክታል፡፡

ድርጅቱ በመግለጫው ማጠቃለያ ለኢትዮጵያ መንግስትና በሽብርተኛ ድርጅትነት ለተፈረጀው ኦነግ ሸኔ ማድረግ አለባቸው ያላቸውን ምክረ ሀሳቦች አስፍሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በወርሃ ሰኔ ስለተፈፀሙት ግድያዎች፣ የንብረት ውድመት፣ ሌሎች የሰብዐጫዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ መረጃ እንዲሰጥ፣ አስቸኳይ የሰብዓዊአ እርዳታዎችን እንዲያደርስ፣ የአከባባውን የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ምናልባት ጉዳዩን ቸል በማለት ለምን ንፁሃን ሊጠብቁ እንዳልቻሉ ማጣራትና ውጤቱን ይፋ ማድረግ፣ ተዓሚኒ፣ ገለልተኛ፣ ውግንና የሌለው ምርመራዎችን እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

በሽብርተኝነት ለተፈረጀው ኦነግ ሸኔ ባስተላለፈው መልዕክት ደግሞ ሁሉንም ዓይነት ከህግ ውጪ የሆኑ ግድያዎች እንዲያቆም፣ ጥቃቱን የፈፀሙ የጦር አዛዦችን በአግባቡ እንዲቀጣ ሲል ጠይቋል፡፡

በምሽቱ የዜና ሰዓታችን የፌደራል መንግስት፣ የኦሮሚያ ክልል እንዲሁም የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንን አነጋግረን በዝርዝር እንመለከተዋለን፡፡
ዮሐንስ አሰፋ
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
1.0K views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:58:46
መንግሥት የተመረጡ የህወሓት ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እወስዳልው አለ

አሻም ዜና |ነሀሴ 20፣ 2014 ዓ.ም

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ የፌደራሉ መንግሥት የተመረጡ የህወሓት ወታደራዊ ዐቅሞች ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ህወሓት ጥቃቱን እንደቀጠለበት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።

በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለህወሓት ቡድን ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

"ስለሆነም በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የህወሓት ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል።" ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
2.2K views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 13:14:32
የፌዴሬሽን ምክር ቤት 12 ክልል እንዲቋቋም የሚያስችል ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወሰነ፡፡

አሻም ዜና |ነሀሴ 12፣ 2014 ዓ.ም

ምክር ቤት ነሀሴ 12 ባካሄደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ አመት፣ በ1ኛ አስቸኳይ ጉባኤው በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የ6 ዞኖችና የ5 ልዩ ወረዳ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአንድ ክልል የእንደራጅ አቤቱታን ተቀብሎ ከመረመረ በኃላ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ ወሰናል፡፡

ህዘበ ውሳኔ የሚያካሄዱት ምክር ቤቱም የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የደቡብ ኦሞ፣ የጌዴኦ፣ የኮንሶ ዞኖች፣ እንዲሁም የደራሼ፣ የአማሮ፣ የቡርጂ፣ የአሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ናቸው ፡፡

ቀሪዎቹ የሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ ዞኖችና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አንድ ላይ የሚቀጥሉ ይሆናል ተብሏል፡፡
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
2.9K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 17:24:51 በተያዘው ሳምንት በኢትዮጲያ አፋር ክልል አንዳንድ ክፍሎችን ጨምሮ በሱዳን እና ኤርትራ ከባድ ዝናብ እንደሚጠበቅ የምስራቅ አፍሪካ የልማት የበይነ መንግስታት (ኢጋድ) አስታወቀ፡፡

አሻም ዜና |ነሀሴ 10፣ 2014 ዓ.ም

ኢጋድ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ በምስራቅ፣ በደቡብ እና በምዕራብ ሱዳን፣ በሰሜን-ምእራብ ኤርትራ እና በኢትዮጲያ አፋር ክልል አንዳንድ አከባቢዎች ላይ ከባድ ዝናብ ሊከሰት እንደሚችል አሳስቧል፡፡

በሰሜን ሱዳን፣ በምዕራብ ደቡብ ሱዳን፣ በምዕራብ ኬንያ፣ በአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ክፍሎች፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ታንዛኒያ ደግሞ ከሚጠበቀው አማካይ የሙቀት መጠን በላይ ሊስተናገድ እንደሚችል ነው የተተነበየው፡፡

በትንበያውም ከነሐሴ 10 - 17 ቀን 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ በደቡብ ሱዳን እና በሰሜን ምዕራብ ኤርትራ ውስጥ ባሉ ጥቂት ቦታዎች ከ 200 ሚሜ በላይ የሆነ ከባድ ዝናብ ይኖራል ብሎ ተንብዮል፡፡

በመካከለኛ ዝናብ መጠን ከ50-200 ሚሜ የሚደርስ ዝናብ ያገኛቸዋል የተባሉት ደግሞ ከደቡብ እስከ መካከለኛው ሱዳን፣ አብዛኛው የደቡብ ሱዳን ክፍሎች፣ ከመካከለኛው እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ፣ ሰሜን ኤርትራ፣ አብዛኛው የኡጋንዳ ክፍሎች እና አንዳንድ የምዕራብ ኬንያ ክፍሎች ናቸው ተብለዋል፡፡

በምስራቅ እና በሰሜን ታንዛኒያ፣ በሩዋንዳ፣ በባህር ዳርቻ እና በመካከለኛው ኬንያ፣ በአብዛኛዎቹ የሶማሊያ ክፍሎች፣ ከመካከለኛው እስከ ሰሜን ሱዳን፣ በደቡብ-ምስራቅ ኢትዮጵያ እና በጅቡቲ ክፍሎች ላይ የሚጠበቀው ቀላል ዝናብ ከ50 ሚሊ ሜትር ያነሰ እንደሆነም ነው የተጠቆመው፡፡

በቡሩንዲ፣ አብዛኛው የታንዛኒያ ክፍል፣ ምስራቃዊ እና ሰሜናዊ ኬንያ፣ ደቡብ-ምስራቅ ኢትዮጵያ እና አንዳንድ የሰሜን ሶማሊያ አካባቢዎች ደረቅ የአየር ፀባይ ያስተናግዳሉ ተብሏል።

በሰሜን ሱዳን፣ በኢትዮጵያ አፋር ክልል ፣ በጅቡቲ፣ በባሕር ዳርቻ ኤርትራ እና በሰሜን ምዕራብ ጠረፍ ሶማሊያ ላይ ከ32 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የሆነ የሙቀት መጠን ይጠበቃል።

በሰሜናዊ ሱዳን ክፍሎች ከሚጠበቀው አማካይ የሙቀት መጠን በላይ ሊስተናገድ ይችላል የተባለ ሲሆን ፣ ሄውም በምዕራብ እና ደቡባዊ ሱዳን የሚገኙ አንዳንድ ክፍሎች ብሎም በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች ሞቃታማ ሊሆን እንደሚችል የምስራቅ አፍሪካ የልማት የበይነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ ለአሻም በላከላት መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡
2.2K views14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 17:23:50
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም አስቸኳይ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ተጠቆመ

አሻም ዜና |ነሀሴ 10፣ 2014 ዓ.ም

የምክር ቤቱ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም አስቸኳይ ጉባኤውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል፡፡

እንደዳይሬክተሩ ገለጻ ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የምክር ቤቱ አስቸኳይ ጉባኤ ከመካሄዱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የምክር ቤቱ አራት ቋሚ ኮሚቴዎች ከአስቸኳይ ጉባኤው አጀንዳዎች ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተናግረዋል፡፡

ሰሞኑን ከክልልነት አደረጃጀት ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች እየቀረቡ መሆኑ ይገለጻል፡፡

ጉባዔው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራልነ ከመባሉ በስተቀር ከክልልነት አደረጃጀቶች ጋር በተያያዘ እየቀረቡ ስላሉ ጥያቄዎች ስለመወያየቱ በግልጽ የተባለ ነገር የለም፡፡
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
1.5K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 14:31:10
ባልደራስ አቶ እስክንድር ነጋ በመንግስት ታፍነዋል ወይም ታስረዋል የሚል ጥርጣሬ የለኝም አለ፡፡

አሻም ዜና |ነሀሴ 09፣ 2014 ዓ.ም

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ነሐሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሬዝዳንቱ እስክንድር ነጋ ከሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ወዲህ ቢሮ መግባት እንዳቆሙ አስታውቋል፡፡

አቶ እስክንድር ነጋ በባልደራስ ፓርቲ የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ”ራሴን ከፓርቲው መሪነት አግልያለሁ” ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ፓርቲው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ”ቤተሰቦቻቸውን ለማውራት ችለናል፤ በመንግስት ታስሯል ወይም ታፍኗል የሚል ጥርጣሬ እንደሌላቸው” ገልጸዋል፡፡

አቶ እስክንድር ነጋ ከፓርቲው መሪነት ራሳቸውን ማግለላቸው በሀገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ጫና የሚያሳይ ነው ሲል ፓርቲው በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

ተስሊም ሙሀመድ

(በምሽቱ የዜና ሰዓታችን መግለጫውን በዝርዝር እንድትመለከቱት ከወዲሁ እንጋብዛለን)
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
1.9K views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 16:09:13
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከጉራጌ ዞን በኩል የክልልነት ጥያቄ አልደረሰኝም አለ።

አሻም ዜና |ነሀሴ 06፣ 2014 ዓ.ም

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ግን የምክር ቤቱን ምላሽ ተቃውሞታል፡፡

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት በጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም ” የጉራጌ ህዝቦች በክልል ለመደራጀት የጠየቀው ህገ መንግስታዊ መብቱን ስለተነፈገ የቀረበ ቅሬታና አቤቱታ ” ሲል ሰይሞ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስገባውና ለአሻም የደረሳት ቅጂ እንደሚያስረዳው ዞኑ ለምክር ቤቱ የክልልነት ጥያቄ ማቅረቡን ነው፡፡

በዚሁ ደብዳቤ ዞኑ፣ ለክልሉ ምክር ቤት በታህሳስ 22 ቀን 2011 ዓ.ም የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄውን ማስገባቱን ያስረዳል፡፡

ይሁንና ’የክልሉ ምክር ቤት ጥያቄው በቀረበለት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ህዝበ ውሳኔ ማደራጀት ቢገባውም ሃላፊነቱን ሳይወጣ የህዝቦች መብት እንዲጣስ አድርጓል” ሲል ይኸው ደብዳቤ ይከስሳል፡፡

በወቅቱ የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ጌታሁን ነጋሽ ተፈርሞ በወጣው ደብዳቤ የክልሉ ምክር ቤት ጥያቄውን ሊቀበለኝ ስላልቻለ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አስገብቺያለሁ ባይ ነው፡፡

ደብዳቤውን የተመለከተችው አሻም የፌዴሬሽን ምክር ቤትን አነጋግራለች፡፡ የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ተረፈ በዳዳ የቀረበልን ጥያቄ የለም ብለዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ነሐሴ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሀሳብን በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ፅዮን ታደሠ
(በምሽቱ የዜና ሰዓታችን ሁለቱ ምክር ቤቶችን ያነጋገርንበትን ዝርዝር ዘገባ እንድትተከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን፡፡)
2.1K views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 12:10:08
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሕዳሴ ግድብ ሦስተኛ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ከስፍራው አበሰሩ

አሻም ዜና |ነሀሴ 06፣ 2014 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዐባይ ስጦታችን ነው፣ ስጦታችንን መጠቀም የእኛ ኃላፊነት ነውም ብለዋል።

ሦስቱ የተፋሰስ ሀገራትም በጋራ ከዚህ ስጦታ ተጠቃሚ ናቸው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የዐባይ ወንዛችን የሚገባውን አስቀርቶ የሚገባቸውን ይዞ መጓዙን ቀጥሏል በማለት የሁሉንም የተፋሰስ ሀገራት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ እንደምትሠራ አስታውሰዋል።

ለመላው አፍሪካውያን የእንኳን ደስ አለን መልዕክትም ማስተላልፋቸው ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
1.6K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ