2022-07-08 11:20:59
ሦስት ፓርቲዎች " በመጪው ሰኞ መላው ኢትዮጵያዊያን ጥቁር ልብስ በመልበስ ለተጨፈጨፉ ዜጎች ሀዘናቸውን እንዲገልፁ ጥሪ አቀረቡ።"
አሻም ዜና |ሐምሌ 1፣ 2014 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ)፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) እና እናት ፓርቲ ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው ጥሪውን ያቀረቡት።
"ጥቁር ከመልበስ በተጨማሪ፣ በዕለቱ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም፣ ከቀኑ 6:30 የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እንዲደረግ" ጥሪ አቅርበዋል።
ፓርቲዎቹ " መንግስት፣ የጭፍጨፋ መደላድሎችንና የማዘናጊያ መግለጫዎችን በማውጣት ለዘር ፍጅቱ የማይናቅ አስተዋፅዖ አድርጓል።" ሲሉ ወንጅለዋል።
የጋራ መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት የእናት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ያየህ አስማረ" አሸባሪ እያሉ የጠሩት ኦነግ ሸኔ ወደሀገር ቤት አገባቡ ጀምሮ የተሠሩ መንግስታዊ ስህተቶች ጥርጥር ባይኖርም አንድ እግሩን አዲስ አበባ፣ አንድ እግሩን ምዕራብ ኦሮሚያ ጫካዎች ውስጥ ከተከለ በኋላም በከፍተኛ ሁኔታ መንግስታዊ መዋቅርና ማዘናጊያዎችን እንደሚጠቀም" ማሳያዎችን መጥቀስ ይችላል ብለዋል።
"ከሁሉም የሚያሳዝነው ሽብር ቡድኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስጃለሁ፤ በቡድኑ የተያዘ አንድም አካባቢ የለም" የሚሉትን "በሚዘወራቸው መገናኛ ብዙሃን በማስተጋባት የጭፍጨፋ መደላድሎችንና የማዘናጊያ መግለጫዎችን በማውጣት የዘር ፍጅቱ እንዳይወገዝ፣ ዓለምአቀፉ ማህበረሰቡ ትኩረት እንዳይደረግበት ለፍጅቱ የማይናቅ አስተዋፅዖ አድርጓል።" ሲሉ ከስሰዋል።
(በምሽቱ የዜና ሰዓታችን የፓርቲዎቹን መግለጫ በዝርዝር እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን)
ዮሐንስ አሰፋ
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asha
1.9K views08:20