Get Mystery Box with random crypto!

Asham TV

የቴሌግራም ቻናል አርማ asham_tv — Asham TV A
የቴሌግራም ቻናል አርማ asham_tv — Asham TV
የሰርጥ አድራሻ: @asham_tv
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.58K
የሰርጥ መግለጫ

Asham Tv is a privately owned media company, based in Addis Ababa, Ethiopia, that provides news, Analysis, information and other programs.

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-07 13:14:50 በነዳጅ እና የተሸከርካሪ መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ ተደረገ፤

አሻም ዜና |ሰኔ 30፣ 2014 ዓ.ም

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረጉን አሳውቋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒሰቴር የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ መሰረት በማድረግ የአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጊያለው ብሏል፡፡

የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ፡-
- በደረጃ አንድ በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5360 ሲሆን አዲሱ ታሪፍ 0.5600 ብር በኪሎሜትር ሆኗል፡፡ ጭማሪ በኪሎ ሜትር 0.0240 ሳንቲም ነው፡፡

ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎሜትር ነባር ታሪፍ 0.6150 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.6464 ነው፡፡ ጭማሪ በሰው በኪሎሜትር 0.0314 ሳንቲም ይሆናል፡፡

- ደረጃ ሁለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5120 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.5420 ነው፡፡ ጭማሪ 0.0300 ሳንቲም፡፡

ደረጃ ሁለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5680 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.6054 ብር ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.0374 ሳንቲም፡፡

- ደረጃ ሶስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.4750 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.5081 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.0331 ሳንቲም ነው፡፡

ደረጃ ሶስት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5360 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.5735 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.375 ሳንቲም ነው፡፡

የታሪፍ ስሌቱ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ
- በደረጃ አንድ ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 53.60 ሲሆን በአዲሱ ታሪፍ ብር 56.00 ሆኗል፡፡ ጭማሪ በ100 ሊሎሜትር ብር 2:40 ነው፡፡

- በደረጃ ሁለት ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 51.20 የሚያስከፍል ሲሆን በአዲሱ ታሪፍ ብር 54.20 ሆኗል፡፡ ጭማሪ በ100 ኪሎሜትር ብር 3.00 ነው፡፡

- በደረጃ ሶስት ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 47.50 የሚያስከፍል ሲሆን በአዲሱ ታሪፍ ብር 50.81 ያስከፍላል፡፡ ጭማሪ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 3.31 ነው፡፡

ታሪፉ ከላይ በተገለጸው መሰረት ከዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የጀመረ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል ፡፡

——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
1.6K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 11:25:16
የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ስድስተኛው የአንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛው መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ነው

አሻም ዜና |ሰኔ 30፣ 2014 ዓ.ም

በጉባኤው ላይ የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2015 ዓ.ም ረቂቅ በጀትና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።

የአባላቱ ጥያቄዎች በዋነኛነት በዜጎች የጸጥታና ደህንነት፣የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡበት ይገኛሉ።

በምላሻቸውም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገው ግድያ አንዳንዶች እንደሚገልጹት በቸልታ መንግስት ስራውን ስለማይሰራ ሃላፊነቱን ስለማይወጣ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ብለዋል።

መንግስት 24 ሰዓት የዜጎችን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፤ በዚህም በጣም በርካታ ህይወት መታደግ ችሏል፤ ያመለጡ የጠፉብን ዜጎች እንዳሉ እንደተጠበቁ ሆኖ፤ በሚፈጠረው ችግር ሁሉ ህይወታቸውን የሚገብሩ የጸጥታ አካላት እንዳሉ መገንዘብ ተገቢ ነው ብለዋል።
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
1.4K views08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 15:18:27
ፍርድ ቤቱ፣ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝን ከእስር ለምን እንዳልፈታ ምክንያቱን እንዲያቀርብ ለሰኔ 30 ቀጠሮ ሰጠ፡፡

አሻም ዜና |ሰኔ 29፣ 2014 ዓ.ም

የፍትሕ መፅሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በ100ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈታ ፍርድ ቤቱ ቢፈቅድም ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ግን እንዳልተፈታ ጠበቃው ሔኖክ አክሊሉ ለአሻም ነግረዋታል፡፡

ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ያስቻለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ፀረ-ሽብር ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እንዲፈታ ካልሆነም የፖሊስ ኮሚሽነሩ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት 8 ሰዓት ችሎት ቀርበው ምክንያታቸውን እንዲያብራሩ ትዕዛዝ መስጠቱን ጠበቃ ሔኖክ ገልፀዋል፡፡
ሃና ታደሰ
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
1.4K views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ