Get Mystery Box with random crypto!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከጉራጌ ዞን በኩል የክልልነት ጥያቄ አልደረሰኝም አለ። አሻም ዜና |ነሀሴ | Asham TV

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከጉራጌ ዞን በኩል የክልልነት ጥያቄ አልደረሰኝም አለ።

አሻም ዜና |ነሀሴ 06፣ 2014 ዓ.ም

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ግን የምክር ቤቱን ምላሽ ተቃውሞታል፡፡

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት በጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም ” የጉራጌ ህዝቦች በክልል ለመደራጀት የጠየቀው ህገ መንግስታዊ መብቱን ስለተነፈገ የቀረበ ቅሬታና አቤቱታ ” ሲል ሰይሞ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስገባውና ለአሻም የደረሳት ቅጂ እንደሚያስረዳው ዞኑ ለምክር ቤቱ የክልልነት ጥያቄ ማቅረቡን ነው፡፡

በዚሁ ደብዳቤ ዞኑ፣ ለክልሉ ምክር ቤት በታህሳስ 22 ቀን 2011 ዓ.ም የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄውን ማስገባቱን ያስረዳል፡፡

ይሁንና ’የክልሉ ምክር ቤት ጥያቄው በቀረበለት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ህዝበ ውሳኔ ማደራጀት ቢገባውም ሃላፊነቱን ሳይወጣ የህዝቦች መብት እንዲጣስ አድርጓል” ሲል ይኸው ደብዳቤ ይከስሳል፡፡

በወቅቱ የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ጌታሁን ነጋሽ ተፈርሞ በወጣው ደብዳቤ የክልሉ ምክር ቤት ጥያቄውን ሊቀበለኝ ስላልቻለ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አስገብቺያለሁ ባይ ነው፡፡

ደብዳቤውን የተመለከተችው አሻም የፌዴሬሽን ምክር ቤትን አነጋግራለች፡፡ የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ተረፈ በዳዳ የቀረበልን ጥያቄ የለም ብለዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ነሐሴ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሀሳብን በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ፅዮን ታደሠ
(በምሽቱ የዜና ሰዓታችን ሁለቱ ምክር ቤቶችን ያነጋገርንበትን ዝርዝር ዘገባ እንድትተከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን፡፡)