Get Mystery Box with random crypto!

ሂዩውማን ራይተስዎች ከሰኔ የጅምላ ግድያ የተረፉ የምዕራብ ወለጋ ነዋሪዎች ጥበቃ እየተደረገላቸው አ | Asham TV

ሂዩውማን ራይተስዎች ከሰኔ የጅምላ ግድያ የተረፉ የምዕራብ ወለጋ ነዋሪዎች ጥበቃ እየተደረገላቸው አይደለም አለ፡፡

አሻም ዜና |ነሀሴ 25፣ 2014 ዓ.ም

ዓለም አቀፉ የሰባዓዊ መብቶች ጥበቃ ተከራካሪ ድርጅት እ.አ.አ. ነሐሴ 31 ቀን 2022 ባወጣው መግለጫ ከባለፈው ሰኔ ወር በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን ቶሌ ቀበሌ ከተፈፀመው የጅምላ ግድያ የተረፉ የአካባቢው ነዋሪዎችን ለመጠበቅ የመንግስት ፀጥታ ሐይሎች የሰሩት ስራ አነስተኛ ብሏል፡፡

በሰኔው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን፣ አብዛኞቹ ህፃናትና ሴቶች በጅምላ መገደላቸውን ያስታወሰው ድርጅቱ ከዚህ ጥቃት የተረፉት ነዋሪዎች ግን ከሦስት ወራት በኋላም ቢሆን አስተማማኝ ጥበቃ እየተደረገላቸው አለመሆኑን ጠቁሟል፡፡

የሂዩውማን ራይትስዎች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላቲቲያ ባደር ” ታጣቂዎቹ መንድሮቹን አንድ በአንድ ሲወድሙ፣ በጭካኔ መላው ቤተሰብን ሲገድሉ በአቅራቢያው የነበሩ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ምንም ሳያደርጉ ቀርተዋል፡፡” ሲሉ የሰኔውን ጥቃት አስታውሰዋል፡፡

”የኢትዮጵያ መንግስት ተዓማኒነት ያለው ገለልተኛ አካል ማጣራት እንዲያደርግ፣ ለጥቃቱ ሀላፊነት የሚወስዱትን እንዲለይና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እርዳታ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡” ብለዋል፡፡

ከሰኔ እስከ ነሐሴ 2022 25 ሰዎችን በስልክ አነጋግሪያለሁ የሚለው ሂዩውማን ራይትስ ዎች 19ኙ የዓይን እማኞችና ቀሪዎቹ ደግሞ የጥቃቱ ሰለባዎች ዘመድ መሆናቸውን የጠቀሱለት ሲሆን መኖሪያቸውም ጉቲን፣ ጨቆርሳ፣ ሲልሳው፣ ቤገን ተሰኙ መንደሮች ናቸው፡፡

ከዓይን ምስክሮቹ፣ ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊትና በኋላ ከሳተላይት ተገኝተዋል ካላቸው ምስሎች በመነሳት የተገደሉት ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሰውኛል ብሏል፡፡

ያነጋገራቸውን የዓይን እማኞች ምስክር ያደረገው ድርጅቱ በወቅቱ ስለነበሩት ”አሰቃቂ” ጥቃቶች በዝርዝር አትቷል፡፡

ከጅምላ ግድያው የተረፉት ነዋሪዎች በአካባቢው በተደጋጋሚ በሚፈፀሙ ጥቃቶች የተነሳ ፍርሃት ውስጥ መውደቃቸውን፣ በቂ ጥበቃና ሰብዓዊ ድጋፍ አለመኖሩን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ የተሳም ብዙዎች የኦሮሚያ ክልልን ለቅቀው እየወጡ መሆኑን መግለጫው አመልከቷል፡፡

እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) መረጃ ከቶሌ ቀበሌ አራት ሺህ ስምንት መቶ(4800) እንዲሁም ከምዕራብ ኦሮሚያ ደግሞ ከአምስት መቶ ሺህ(500 000) በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ያመላክታል፡፡

ድርጅቱ በመግለጫው ማጠቃለያ ለኢትዮጵያ መንግስትና በሽብርተኛ ድርጅትነት ለተፈረጀው ኦነግ ሸኔ ማድረግ አለባቸው ያላቸውን ምክረ ሀሳቦች አስፍሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በወርሃ ሰኔ ስለተፈፀሙት ግድያዎች፣ የንብረት ውድመት፣ ሌሎች የሰብዐጫዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ መረጃ እንዲሰጥ፣ አስቸኳይ የሰብዓዊአ እርዳታዎችን እንዲያደርስ፣ የአከባባውን የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ምናልባት ጉዳዩን ቸል በማለት ለምን ንፁሃን ሊጠብቁ እንዳልቻሉ ማጣራትና ውጤቱን ይፋ ማድረግ፣ ተዓሚኒ፣ ገለልተኛ፣ ውግንና የሌለው ምርመራዎችን እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

በሽብርተኝነት ለተፈረጀው ኦነግ ሸኔ ባስተላለፈው መልዕክት ደግሞ ሁሉንም ዓይነት ከህግ ውጪ የሆኑ ግድያዎች እንዲያቆም፣ ጥቃቱን የፈፀሙ የጦር አዛዦችን በአግባቡ እንዲቀጣ ሲል ጠይቋል፡፡

በምሽቱ የዜና ሰዓታችን የፌደራል መንግስት፣ የኦሮሚያ ክልል እንዲሁም የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንን አነጋግረን በዝርዝር እንመለከተዋለን፡፡
ዮሐንስ አሰፋ
——————————
አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ
Facebook - https://www.facebook.com/AshamMediaTrading
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham