Get Mystery Box with random crypto!

Ahmed Habib Alzarkawi

የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi
የሰርጥ አድራሻ: @alzarkawihabib
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.53K
የሰርጥ መግለጫ

Hello World

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 104

2022-05-22 15:03:26
አፋር -ካናዳ

በክቡር አምባሳደር ሃሳን አብዱልቃድር የተመራው የተለያዩ የክልሉ የሴክተር መስሪያቤት ሃላፊዎች የተካተቱበት ልዑክ ወደ አሜሪካ ሀገር ካናዳ በመምራት በካናዳ የሚገኙ የአፋር ዲያስፖራ ኮሚኒታ ጋር በክልሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንዲሁም በጦርነቱ የተፈናቀሉትን ወገኖችን እንዲረዱ ከኮሙኒቲው ጋር በቀጣይ ቀናት ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል ለመወያየት ካናዳ ሲገቡ ለልዑካኑ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
6.3K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 22:39:35
የአልጄሪያ መንግስት ባለ 500 ዲናር ሳንቲም አል አቅሳ መስጂድ እና "እየሩሳሌም የኛ ናት" የሚል የተጻፈበት ሳንቲም አትማ ለአገልግሎት አውላለች!!!
2.5K viewsedited  19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 20:51:47
ሰበር!!!

ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ያለችው እስስቷ ግብፅ እራሷ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባት ጭንቅ ውስጥ መግባቷ ተነገረ!!!!

ግብፅ እስከዛሬ ኢትዮጵያን ለማዳከም ለማዋከብ ያላደረገችው ነገር የለም ያልተጠቀመችው ቴክኖሎጂ የለም። የግብፅ መንግስት ሁሉኑም የልማት ስራ አቁሞ እንቅልፍ አጥታ ስታደርግ የኖረችው እንቅስቃሴ ሁሉ በመጨረሻም ውጤት አልባ ሆኖባታል። በዚህ ምክንያት የግብፅ ህዝብ በኢትዮጵያ ክብራችን አስነክታችኋል በአለም ዲፕሎማሲ መድረኮች አንገታችን አስደፍታችሁናል። ብሄራዊ ጥቅማችን ማስጠበቅ አልቻላችሁም የሚለው የግብፃውያን ውስጥ ለውስጥ የተብላላው ጥያቄ ዛሬ ገንፍሎ በመውጣት የአልሲሲን አገዛዝ አደጋ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። የግብፅ መንግስት ህዝቡን ለመሸወድ የሚጠቀማቸውን ምክንያቶች አሟጦ ተጠቅሟል። አለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የግብፅ አክቲቪስቶች ፖለቲከኞች አንድ ሆነው አልሲሲን አስወግደን የግብፅን ክብር የሚመልስ መንግስት እንመሰርታለን በማለት ተስማምተው እንቅስቃሴ መጀመሩ ከዚህ በፊት Ctv Egypt ዘግቦአል።

በሌላ በኩል ይሄ ተቃውሞ ለወደፊት መሰረቷ የተናጋ ግብፅን ይመሰርታል እንጂ ጠንካራ ግብፅ አይመሰርትም የሚሉ ሌለኞቹ የግብፅ ፖለቲከኞች ስጋታቸውን እየገለፁ ነው።

ግብፅ ከዚህ በኋላ ከኢትዮጵያ ጋር ልትደራደር የምትችለው በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች
4.7K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 14:00:52
ኢትዮጵያ .....

ሀገራችን ወደ ሃያልነት የምታደርገው ጉዞ አጠናክራ ቀጥላለች። የምትመለከቱት ሀገራችን ምድር ሃይሏን ለማጠናከር ከተለያዩ ሀገራት የገዛችውን የአለማችን የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው ታንኮች ሀገራችን ደርሰዋል። የታንኮችን ብዛት ፈጣሪ ይወቀው እኔ መገመትም አልችልም....Ahmed Habib Alzarkawi

t.me//alzarkawihabib
6.4K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:28:15 የኢንተርኔት መቆራረጥ አፋር ክልል ብቻ ነው ወይስ ሌላ ቦታም አለ ?
3.4K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 19:00:54
"ኣሸባሪው ሕወሓት በኤርትራ ላይ ይፋዊ ጦርነት ከከፈተ ኤርትራ ራሷን ትከላከላለች እንጂ የኢትዮዽያን መንግስትና ህዝብ ፈቃደኝነት ሳታገኝ ጦሯ የትግራይን ምድር ኣይረግጥም! " ጄ/ፊሊጶስ ወ/ዮሓንስ

"እኛ የኢትዮዽያን ህዝብ እና መንግስት ሉኣላዊነት እናከብራለን። ምንም እንኳን ኣሸባሪው ሕወሓት በኢትዮዽያ የህዝብ ወኪሎች በኣሸባሪነት ቢፈረጅም ወንበዴው ቡድን የመሸገበት የትግራይ ምድር ደግሞ የኢትዮዽያ ሉኣላዊ ግዛት ኣካል ነው።

ሆኖም ግን ኣሸባሪው የሕወሓት ወንበዴ ቡድን በኤርትራ ላይ ይፋዊ ጦርነት ከከፈተ ኤርትራ ራሷን ትከላከላለች እንጂ የኢትዮዽያን መንግስትና ህዝብ ፈቃደኝነት ሳታገኝ ጦሯ የትግራይን ምድር ኣይረግጥም! "
ምንጭ ፦Eritrean Press-Amharic
5.1K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 16:39:02
“ሩሲያ ዶንባስን ወደ ሲኦል ለውጣታለች”
የዩክሬንፕሬዚዳንት ዘለንስኪ

ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ሩሲያ የዩክሬኗን ዶንባስ ክልል ወደ ሲኦል ቀይራታለች አሉ፡፡

ዜሌንስኪ ሞስኮ ምስራቃዊ ዶንባስ ክልልን ወደ ሲኦል ለውጣታለች ሲሉ ክስ ያቀርባሉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በኪዬቭ በነበራቸው ንግግር በኦዴሳ ክልል እንዲሁም በማዕከላዊ ዩክሬን ከተሞች ጥቃቶች ያለማቋረጥ መቀጠላቸውን አጽንኦት ሰጥተውበታል ፡፡

ዶንባስ የተሰኘው ክልል ሙሉ ለሙሉ ወድሟል ፡፡

ፕሬዚዳንቱ እንደሚሉት የክሪሚሊን ፖለቲከኞች ለዚህ ሁሉ ጥፋት ምንም ዓይነት ወታደራዊ ማብራሪያ የላቸውም፡፡
ሩሲያ አቅዳ ያደረገችው እና በተቻላት መጠን ዩክሬናውያንን ለማጥፋት የተነሳሳችበት ጦርነት ነው በሚልተደጋጋሚ ትችቶች ይሰነዘራሉ፡፡
ሐሙስ የዩክሬን የመከላከያ ሚንስቴር ሞስኮ በዶንባስ ጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላለች ፤ንፁኃን ዜጎችም ከአካባቢው እንዳይወጡ ከልክላለች በሚል ወንጅሏታል፡፡ ሮይተርስ
5.6K views13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 16:19:58
አስደሳች ዜና!!!!

ኢትዮጵያ በኤርትራ ወደቦች ለመገልገል ባሳየችው ፍላጎት መሰረት ከምፅዋ ወደብ እስከ ኣስመራ ከተማ የተዘረጋው የባቡር መስመር ጥገና እየተደረገለት ነው።

በቀጣይም ለረጅም ኣመት ኣገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረው ከኣስመራ- ኸረን- ባረንቱ- ተሰነይ የባቡር መስመር ጥገና እንደሚደረግለት እና ኣዲስ የባቡር ሓዲድ ከተሰነይ-ሑሞራ ለመገንባት እቅድ መያዙን የኤርትራ ትራንስፖርት መስሪያ ቤት ኣሳውቋል።

የጣሊያን መንግስት ባደረገው ጥናት ኢትዮጵያ በአሰብ ወደብ ተጠቃሚ እንድትሆን በትንሽ ወጪ ኢትዮጵያና ኤርትራን በባቡር ትራስፖርት ማገናኘት እንደሚቻልና ወጪውንም እንደሚሸፍን ከኣሑን በፊት መግለፁ የሚታወስ ነው።

የኤርትራ ትራንስፖርት ሚኒስቴር
5.4K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 10:29:50
ዶክሌ አረፈ

#Ethiopia | ተወዳጁ ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሜድስታር ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ሀሙስ ግንቦት 11, 2014 በተወለደ በ57 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ዶክሌ ላለፋት ሁለት አስርተ አመታት በኮሜዲው ዘርፍ አዝናኝ፣ አስተማሪ እና ቁምነገር አዘል የኮሜዲ ስራዎችን ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል። ወንድወሰን ሀገራችን ካፈራቻቸው ብርቅዬና ግንባር ቀደም ኮሜዲያኖች አንዱ ሲሆን ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር።

የኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ የቀብር ስነስርአት የሚፈጸመው በትውልድ ሀገሩ ኢትዩጵያ ስለሆነ ለዚህም ማስፈጸሚያ የሚሆን እና ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይህ የጎፈንድሚ አካውንት ተከፍቷል። ወዳጅ ፣ዘመድ፣ ጓደኞቹ ፣አድናቂዎቹ ና መላው የጥበብ አፍቃሪያን ይህ ታላቅና አይተኬ ኮሜዲያን በክብር ይሸኝ ዘንድ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን!!!

https://www.gofundme.com/f/4bry7-emergency
6.3K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 22:23:48
ለሚወዳት እናት ሀገሩ የህይወት መስዋእትነትን ጭምር በመክፈል አለኝታነቱን ላረጋገጠው ጀግናው ሰራዊታችን በምላሹ ህዝብና መንግስት የሰራዊቱና የቤተሰቡ አለኝታ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ወሳኝ ስራዎቻችንን መስራት እንቀጥላለን!!!

ኢትዮጰያን የሚመጥንና የሚመስል ዘመናዊ ሰራዊት መገንባታችን እንቀጥላለን!!

Dr.Abreham Belay
2.5K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ