2022-05-25 19:45:48
የአሳኢታ ንግድ ባንክ ሙሉ ገንዘብ ለመንግስት ያስረከቡት ሃቢብ መሀመድ ያዮ
የአስተዳዳሪነት ቁንጮ የታማኝነት ቀንዲል
መላው አፋር ሁሉ እጅግ የሚወዳቸው ና የሚያከብራቸው ተወዳጅ አባት ናቸው።እንዲህ አይነት ስብዕና በምድራችን ላይ የተቸሩት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።
የደርግ መንግስት መውደቁ መቃረቡን ተከትሎ በዘመኑ የአፋር አስተዳዳሪ ና መሪ የነበሩት እጅግ የተከበሩት ሃቢብ መሀመድ ያዮ አሣኢታ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግዶ ባንክ ሙሉ ገንዘብ ሳንተም ሳትቀር በጆንያ ጭነው ወደ ጎረቤት አገር ጅቡቲ አመሩ።ግንቦት 22 1983 ጅቡቲ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ባንድ ቆጥረው ሚሊየን ብሮች በደረሰኝ አስከበሩ።ይኸ የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረትነቱን አሳውቀው።
በተጨማሪም 3 ኮብራ ና 11 ቶዮታ መኪናዎች እያስነዱ ከወሰዱ በኋላ በጅቡቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስረክበዋል።
የአገር ታመኝነታቸው በተግባር አረጋገጡ።እኔ እኮ ራሴ አገር ነኝ የሚሉት ሃቢብ መሀመድ ያዮ በዚያን ዘመን አሁንስ ቢሆን እሳቸው የሚያህል ማንስ አለና እውነትም አገር ናቸው።
ከአፋር ሱልጣን ከሆኑት ደጃች መሀመድ ያዮ የሚወለዱት አባት ሃቢብ ከአያቶቻቸው ጀምሮ የወረሱትን ህዝብን መምራት ና ማስተዳደር ከልጅነታቸው ጀምሮ እየቀሰሙበት ያደጉበት የዕለት ተዕለት ሁነኛ ተግባር ነው።በ1950ዎቹ ደሴ በሚገኘው አንጋፋው ወይዘሮ ስህን ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የአብዮት ንቅናቄ ከመሠረቱት ና ካቀጣጠሉት ሪቮዎች ብርሃነ መስቀል ረዳ ና ዋለልኝ መኮነን ጋር ተምረዋል።
ለማስታወስ ያህል እንጂ የሃቢብ መሀመድ ያዮ ታሪክ እንደ አፋር ታሪክ ተፅፎ የማያልቅ፣እንደ ጀግነታቸው ተተርኮ የሚደንቅ ነው። ይህን እንደ ኘሮቫ አሊያም ቅንጫቢ የመፅሃፍ መግቢያ ብቻ መሆኑን ያጢኑት።
ጊዜ ሰጥተው ከደረጀ ሀይሌ(ሀይለ ዘ በቅሎ ቤት)ጋር በደራው ጨዋታ የሬዲዮ ኘሮግራም ጋር ያደረጉትን ዘለግ ያለ ጨዋታ ያድምጡት።ደረጀን ከሸገር በሮ ሰመራ እንዲመጣ ያደረገው ጓደኛችን ማስረሻ ያዘው እንደሆነ አያይዞ ገልጧል።
ማርስ ምስጋና ያንስብሃል።ደሬማ ልዮ ነው አቀራረብህ።
ለአባታችን ሃቢብ መሀመድ ያዮ ረጅም ዕድሜ ና ጤና እንመኛለን።
4.3K views16:45