Get Mystery Box with random crypto!

Ahmed Habib Alzarkawi

የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi
የሰርጥ አድራሻ: @alzarkawihabib
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.53K
የሰርጥ መግለጫ

Hello World

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 102

2022-05-25 14:18:09 በአሜሪካ ቴክሳስ 19 የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ህጻናትና 2 አስተማሪዎች ተገደሉ

ጆ-ባይደን ክስተቱን ለማሰብ አስከ ቅዳሜ ድረስ ሰንደቅአላማዎች ዝቅ ብለው እንዲውለበለቡ አዘዋል ጥቃቱ ባለፉት አስር ዓመታት በአሜሪካ ከተፈጸሙ ጥቃቶች ሁሉ የከፋ ነው ተብሏል

ራሞስ የተባለ የ18 አመት ወጣት በአሜሪካ ቴክሳስ 19 የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ሕጻናት ገደለ፡፡

ህጻናቱ የተገለደሉት ሳልቫዶር ራሞስ የተባለ አንድ የ18 ዓመት ወጣት በከፈተው ድንገተኛ የተኩስ እሩምታ መሆኑን የግዛቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡ በደቡብ ቴክሳስ ግዛት፣ ዩቫልዲ ከተማ ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ከተገደሉት ሁለቱ አዋቂዎች ሲሆኑ የተቀሩት ህጻናት መሆናቸውም ተገልጸዋል፡፡ ጥቃቱ ባለፉት አስር ዓመታት በአሜሪካ ከተፈጸሙ ጥቃቶች ሁሉ የከፋ መሆኑንም ነው የሮይተርስ ዘገባ የሚያመላክተው፡፡

የቴክሳስ የህዝብ ደህንነት ክፍል ሳጅን ኤሪክ ኢስታራዳ ፤ ታጣቂው ጥቃት በሚፈጽምበት ወቅት ጋሻ ለብሶ፣ ኤአር-15 ከፊል አውቶማቲክ ጠመንጃ እና ሽጉጥ ይዞ ነበር ብለዋል፡፡

ታጣቂው በህጻናቱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያነሳሰው ምክንያት ግልጽ አይደለም ሲሉም አክሏል ሳጅኑ፡፡

ጥቃቱ ከተፈጸመ ከሰዓታት በኋላ በከፍተኛ የድንጋጤ መንፈስ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን፤ ጥቃት ልጆቻቸውን፣ ቤተሰባቸውን ላጡ ሀዘናቸውን ገልጿል።

አሳዛኝ ክስተቱን ለማሰብ ቅዳሜ ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ባንዲራዎች በየእለቱ ዝቅ ብለው እንዲውለበለቡም አዘዋል ፕሬዝዳንቱ።

ከተገደሉት ሁለት አዋቂዎች አንዷ በዚያው ትምህርት ቤት የምታስተምር መምህርት ነበረች ተብለዋል።በስፋት የስፓኒሽ አሜሪካዊያን በሚበዙበት በዚህ ትምህርት ቤት 500 ሕጻናት ተማሪዎች ይገኙበታል።

ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ2ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ያሉ፤ ዕድሜያቸው ከ7 እስከ 10 ዓመት ያሉ ልጆች የሚማሩበት ነው። ሳልቫዶር ራሞስ ከዚህ በፊት የገዛ አያቱን በጥይት ተኩሶ የመታ ወጣት እንደሆነም የፖሊስ መረጃወች ይጠቁማሉ፡፡
5.7K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 12:50:33
የአለማችን ትልቁ የ ተ ም ር እርሻ

ሰሜን ምስራቅ ሳውዲ―ቡረይዳ ነው ።በአለም ትልቁ የተምር እርሻ ነው።ባለ ቤቱ አልራጂሂ ኩባኒያ ነው።ደረጃው አለማቀፍ እውቅና አግኝቷል። 45 የተምር አይነት ያመርታል።

በየአመቱ ብዙ ኩንታል ተምር መካና መዲና እየተላከ ለረመዳን ፆም ማፍጠሪያ በነፃ ይከፋፈላል።
5.8K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:29:29
ያው ዛሬም "እንዘምታለን" እያሉ ነው!

ፖሳቹም ተፖሳቾቹም በሱዳን የስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው።ኡምራኩባ ውስጥ!
ፅሑፉ 'በድል ተመለሱ' ይላል። የዘመቻ ሽኝት መሆኑ ነው።
ከምስሉ በላይ በቀኝ በኩል ያለው ልጅ ወዲ ነጋሽ የተባለው ነው ፤ሁመራ ነዋሪ ነበር።

ፖሳቹ (ቢኒያም ገ/የሱስ) ደግሞ አብደራፊ ውስጥ ይኖር ነበር።አርማጭሆን ወደ ትግራይ ለማካለል በሚል ከ500 በላይ የትግራይ ተወላጅ ገበሬዎችን በየቤታቸው እየዞረ ፔቲሽን ያስፈረመ ልጅ ነው።

ከታች ተደርድረው የቆሙትም እዛው አብደራፊ ውስጥ ይኖሩ ነበር።

Asfaw Abreha
2.4K views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 19:57:07
የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ሲሲ የኑሮ ውድነቱ እየጨመረ በመምጣቱ ግብፃውያን የዛፍ ቅጠሎችን እንዲመገቡ ጠየቁ።

.የሀገሩን በጀት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለማዳከም ተጠቅሞ ይሄን ባይል ነበር የሚገርመው
4.2K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 18:13:10
"ጦርነቱ ሊቋጭ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ከፑቲን ጋር መገናኘት ነው" - የዩክሬን ፕሬዝዳንት

ዘለንስኪ ስለ ጦርነቱ ማብቃት የምናወራ ከሆነ ያለ ፑቲን የሚሆን አይደለም ብለዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጦርነቱን ለመቋጨት ብቸኛው መንገድ የሩሲያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ማግኘት እንደሆነ ተናገሩ፡፡

ዘለንስኪ ፑቲንን በግንባር አግኝቶ ማውራቱ ጦርነቱን ለማቆም ብቸኛው መንገድ ነው ብለዋል፡፡

በሩሲያ ሁሉ ነገር የሚወሰነው በፕሬዝዳንቱ ነው ያሉት ዘለንስኪ ስለ ጦርነቱ ማብቃት የምናወራ ከሆነ ያለ ፑቲን የሚሆን አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይሄን ያሉት ትናንት ሰኞ ፤ በስዊዘርላንድ ዴቮስ በመካሄድ ላይ ባለው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ነው፡፡
ማሪዎፖል የተባለችውን የወደብ ከተማ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሯን ያስታወቀችው ሩሲያ በምስራቃዊ ዩክሬን የጀመረችውን ዘመቻ አጠናክራ መቀጠሏን አስታውቃለች፡፡

ዘመቻው በአካባቢው የሚገኙትን የዶንባስ አካባቢዎች ነጻ በማውጣት ሪፐብሊክ ሆነው እንዲመሰረቱ ለማድረግ ነው፡፡ የሩሲያ ጦር ከቀናት በፊት በሰጠው መግለጫ የሉሃንስክ ሪፐብሊክን እውን ለማድረግ ጥቂት ብቻ ይቀረናል ማለቱ ይታወሳል፡፡

ዜሌንስኪ በፎረሙ ባደረጉት ንግግር በሩሲያ ላይ የተጀመሩት ማዕቀቦች እና እገዳዎች ጠንከር ብለው እንዲቀጥሉ ስለመጠየቃቸውም ዘ ናሽናል ዘግቧል፡፡
5.1K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 23:07:21
አነጋጋሪው መረጃ

በደቡብ ሱዳን በአንዲት ሴት ግድያ ጥፋተኛ የተባለዉ በግ በሶስት ዓመት እስር እንዲቀጣ ተወስኗል!!

በደቡብ ሱዳን በአንዲት አዛዉንት ደረት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት በመፈጸም ለሞት ዳርጓል የተባለዉ በግ በሶስት አመት እስር እንዲቀጣ መወሰኑን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የበጉ ባለቤትም ለተጎጂው ቤተሰብ አምስት ላሞችን እንዲከፍል በደቡብ ሱዳን ሩምቤክ ከተማ የሚገኘው የአካባቢው ፍርድ ቤት ብይን ሰጥቷል።

ሱዳን ቱዴይ ጋዜጣ እንደዘገበው በደቡብ ሱዳን ሌክ ግዛት የሚገኘው የሩምቤክ ፖሊስ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሴትየዋን የገደለዉን በግ በቁጥጥር ስር አውሏል። በጉ በሴቲቱ ላይ ጥቃት ሰንዝሮ ከመሞቷ በፊት ደረቷ ላይ ብዙ ጊዜ እንደመታት ተነግሯል።

በልማዳዊ ህግ ማንኛውም የቤት እንስሳ ሰውን የገደለ እንደሆነ ለሟች ቤተሰብ ካሳ ይከፈለዋል የሚል መመሪያ ቢኖርም የቤት እንስሳ በእስር መቀጣቱን አነጋጋሪ ሆኗል።
1.9K views20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 21:53:15
የኡጋንዳ የሃገር ውስጥ ሚኒስትር “ድሆች ገነት አይገቡም” ማለታቸው እያነጋገረ ነው

ድሆች ገነት የማይገቡት ሁሌም ፈጣሪን በድህነታቸው ስለሚያማርሩ ነው የሚሉት ሚኒስትሩባለጸጋ መሆን ክብር ነው ሲሉ ስለመናገራቸውም ተዘግቧል፡፡

አፍሪካ አለም በማይሆን ንግግር ታስደምማለች ሌላው አለም በቴክኖሎጂ ያስደምመናል
3.1K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 21:33:46 በጣም አስገራሚ ተፈጥሮ ነው (እውነተኛ Mermaid) ለመጀመሪያ ጊዜ በቅርበት የተቀረፀ ሳይሆን አይቀርም እስኪ ቪዲዮውን ተመልከቱ። እናም ሁሌም አስደናቂ ቪዲዮዎችን ለማየት Follow አድርጉ
https://vm.tiktok.com/ZMLKAk4fn/?k=1
3.5K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 19:22:15
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2022 የታይምስ መጽሔት 100 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ።

መጽሔቱ ይፋ ባደረገው የ100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ዝርዝር በአመራር ዘርፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መካተታቸውን አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንጆቹ 2019 የመጽሔቱ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ አንዱ እንደነበሩ የሚታወስ ነው።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪም በታይም መጽሄት ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።

ታይስም መጽሔት የ100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ዝርዝር በዓለም ዙሪያ በመብቶች ተከራካሪነት፣ በፈጠራና በስኬት የተዋጣላቸው የሚላቸውን ሰዎች ይሰይማል።(FBC)
4.7K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 19:00:01
" የMokeypox በሽታ መስፋፋት ለኢትዮጵያም ስጋት ነው "

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘውዱ አሰፋ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

" ቫይረሱ ከዚህ በፊት ፈንጣጣ መሰሉ በሽታ ተጠቂ የሌለባቸው ሀገራት ሳይቀር እየተስፋፋ ነው፡፡

እንደማንኛውም ሀገር እኛም በቫይረሱ ስርጭት ስጋት አለን። በኢትዮጵያ የመግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ የተለመደው ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

በሀገሪቱ የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት መግቢያ እና መውጫ ላይ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እና ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይሄድ የተላላፊ በሽታዎች ክትትል እየተደረገ ነው።

የበሽታው ተጠቂ በኢትዮጵያ ቢገኝ ማድረግ ስለሚገባን ስራዎች፣ ለህብረተሰቡ መሰጠት ስለሚገባው የግንዛቤ ፈጠራ መልዕክት እና የህክምና ክትትል ስራዎችን ለመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ ነው "
4.6K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ