Get Mystery Box with random crypto!

Ahmed Habib Alzarkawi

የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi
የሰርጥ አድራሻ: @alzarkawihabib
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.53K
የሰርጥ መግለጫ

Hello World

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 105

2022-05-19 21:57:52 እስካሁን 2 ሺ ገደማ የዩክሬን ወታደሮች ለሩሲያ እጅ ሰጥተዋል

ባለፉት 24 ሰዓታት 771 የዩክሬን ወታደሮች ለሩሲያ እጅ መስጠታቸውን የሩሲያ ጦር አስታወቀ፡፡ ጦሩ ከ771ዱ 80ዎቹ የተጎዱ ናቸው ብሏል፡፡ እስካሁን በአጠቃላይ 1 ሺ 730 የዩክሬን ወታደሮች እጅ መስጠታቸውንም ነው ያስታወቀው፡፡
3.1K views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 21:11:15
3.9K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 21:11:09 “ቀፊራ” እድሜ ጠገቡ የድሬዳዋ ገበያ
=======
የድሬዳዋ ነዋሪዎች ሳምንቱን ሙሉ የሚገበያዩባቸው ገንደቆሬ፣ ሰኢዶ፣ ቀፊራ የሚባሉ ሦስት የመገበያያ ስፍራዎች አሏቸው። ከእነዚህም ውስጥ በድሬደዋና አካባቢዋ በቅርብ እርቀት ከሚገኙ ከተሞች የተሰባሰቡ ሻጭ እና ሸማቾች የሚገናኙበት ግዙፍ እድሜ ጠገብ የመገበያያ ሥፍራ ቀፊራ ነው። ቀፊራ ገበያ ከተመሰረተ 100 ዓመታትን እንዳስቆጠረ ይነገርለታል።

“ቀፊራ” የሚል ስያሜውን ያገኘው “ቀፊር” ከሚል የአረበኛ ቃል መሆኑን ይነገራል። ቀፊር “ዘብ” የሚል አቻ ትርጓሜ አለው። የገበያው ውጫዊ አጥር የአርመኖች የምህንድስና ጥበብ ውጤት ነው። ይህ የኪነ-ሕንፃ ጥበብ የተገነባው እኤአ 1942 ሲሆን ስድስት መግቢያዎች አሉት። የኪነ-ሕንፃ ግንባታው ከሀረር ጀጎል ግንብ ጋር የተቀራረበ ይዘት አለው። በቅርጽና በዓይነት ጀጎልን የሚመስለው ማራኪ ግንብ አንድ መቶ ዓመታትን እንዳስቆጠረ የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ። በድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም በቅርስነት የተመዘገበው “ቀፊራ” ማራኪ ዕይታ ያለው ነው።

ለከተማዋ የቱሪስት መስህብ ከሆኑ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው “ቀፊራ” የተለያየ ባህል፣ ሐይማኖት፣ ቋንቋ፣ ፖለቲካዊ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ሲያገበያይ የሁለት ትውልድ ዕድሜ ያህል ዘልቋል።

ቀፊራ በተለይ በበአላት መዳረሻ ቀናት ላይ በገዢ እና ሻጭ ትርምስ ይጨናነቃል። የግብይት ሂደቱ እንደደመቀ ከማለዳ እስከ ምሽት በሚዘልቅበት ቀፊራ ተፈልጎ የሚታጣ የሸቀጥ ዐይነት እንደሌለ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።

አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ቅመማ ቅመም፣ የእህል ዓይነቶች (የቅባት እህሎች፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣…)፣ በቆሎ እሸት፣ ኩድራ (የሽንኩርት አይነቶች፣ ቲማቲም ድንች…)፣ ከዛፍ የሚገኙ ጭሳጭሶች (ወይራ፣ ብክብካ…)፣ ከሰል፣ እንጨት፣ ባህር ዛፍ፣ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮች፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ቅቤ እና የመሳሰሉት በስፋት የሚገኙበት ሰፊ የገበያ ስፍራ ነው።

በማኅበራዊ ህይወት ተሳስረው፣ በኪሳራቸው ተዛዝነው፣ ከትርፋቸው ተካፍለው በጋራ መኖር ያውቁበታል የሚባልላቸው የቀፊራ ነጋዴዎች አብዛኞቹ የእድሜያቸውን ግማሽ ያሳለፉት እዚሁ ቀፊራ ውስጥ ነው። “ቀፊራ” ተወልደው፣ “ቀፊራ” አድገው፣ “ቀፊራ” ውስጥ በንግድ ሥራ የተሰማሩም ይገኛሉ።

“ቀፊራ በጅምላም ሆነ በችርቻሮ ለገበያ የሚቀርቡ ሸቀጦች መገኛ በመሆኑ ሁሉም ይመርጠዋል” የምትለው ወ/ሮ በላይነሽ ተሾመ ለገበያ የሚቀርቡት ሸቀጦች ዐይነት እና ብዛት ብቻ ሳይሆን ገጠሩን ከከተሜው ማስተሳሰሩ የገበያው ተጨማሪ ድምቀት እንደሆነ ነግራናለች።

የቀፊራ ነጋዴዎች በስድስቱ ትልልቅ በሮች በሚያስገባው ገበያ የየራሳቸው ቦታ (መደብ) አላቸው። የግብይት ሂደቱ ሲጠናቀቅ እቃቸው ተሸምኖ በሚገባ ታስሮ ይቀመጣል። በር የሌለው ሱቅ ያላቸው የኩድራ ነጋዴዎች የሚበዙ ቢሆንም “እቃዬ ይዘረፍ ይሆን” የሚል ስጋት የለባቸውም።

ምንጭ፡ አዲስ ዘይቤ
3.9K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 20:40:42
ሰበር !!!

በሱዳን የሚገኝ ሳምሪ የተባለ የህወሓት ቡድን የህዳሴ ግድብ ስራን ለማወክ ያለመ ተልዕኮ በግብፅና ሱዳን ተስጥቶት በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በዝግጅት ላይ እንዳለ ከዓይን በተሰወሩ የኢትዮጵያ ድሮኖች ተመቶ ሙሉ ለሙሉ ወደ አመድነት ተቀሯል።

ድል ለኢትዮጵያ

tt.me//alzarkawihabib
4.3K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 19:29:10
አውሮፓ እና አሜሪካ በፈንጣጣ መሰል ወረርሽኝ ተመቱ!!!!

በዝንጆሮዎች ላይ በብዛት የሚከሰተው ይህ ወረርሽኝ ከሰው ወደ ሰው በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ነው ተብሏል
አውሮፓ እና አሜሪካ በፈንጣጣ መሰል ወረርሽኝ ተመቱ፡፡
በአውሮፓ እና አሜሪካ በተለምዶ የዝንጆሮ በሽታ በሚባል የሚታወቀው ፈንጣጣ ወረርሽኝ መመታታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ይህ ወረርሽኝ እስካሁን በእንግሊዝ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋል እና አሜሪካ ሰዎችን ያጠቃ ሲሆን በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በማዕከላዊ እና ምዕራብ አፍሪካ በዝንጆሮዎች ላይ ነበርም ተብሏል፡፡

ይህ በሽታ በአካላዊ ንኪኪ የሚተላለፍ ሲሆን በቫይረሱ የተያዘ ሰው 10 በመቶ የመሞት እድል እንዳለው ተገልጿል፡፡
ወረርሽኙ ከዚህ በፊት ስምንት ጊዜ በዓለማችን የተከሰተ ሲሆን አሁን ደግሞ በፖርቹጋል አምስት ሰዎች፣ ስፔን የበሽታው ምልክት ያሳዩ 23 ሰዎችን እንደለየች ገልጻለች፡፡
በአሜሪካ ደግሞ አንድ ሰው በዚህ ተላላፊ በሽታ የተጠቃ ሰው የተገኘ ሲሆን ከቫይረሱ ተላላፊነት አንጻር ተጨማሪ በሽተኞች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡የዝንጆሮ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ጎርጎሮሲያዊያን ዘመን አቆጣጠር በ1958 በዝንጆሮ ላይ ነበር የተገኘው፡፡
በህ በሽታ አሁን ላይ በእንግሊዝ ዘጠኝ ሰዎች መጠቃታቸው ከታወቀ በኋላ ሰዎቹ እንዴት ሊጠቁ እንደቻሉ ተመራማሪዎች እርግጠኛ መሆን አልቻሉም፡፡
ተመራማሪዎቹ እስካሁን በዚህ ቫይረስ መጠቃታቸውን ያላወቁ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ ያላቸው ሲሆን ሰዎች የተለየ ስሜት ከተሰማቸው ወደ ጤና ተቋም እንዲመጡ አሳስበዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ ሰዎች ያለገደብ ወደ ፈለጉት ሀገር እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ለዚህ በሽታ መሰራጨት ዋነ ኛው ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረም የእንፈግሊዝ ተመራማሪዎች ገልጸዋል፡፡
5.0K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 19:18:05
ጆርጅ ቡሽ በንግግራቸው የሩሲያን ወረራ ከኢራቅ ማምታታታቸው እያነጋገረ ነው!!!

ቡሽ አሜሪካ እ.ኤ.አ በ 2003 ወታደሮቿን ወደ ኢራቅ እንድትልክ ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ሩሲያ ``ዩክሬንን ወረረች`` በማለት ፋንታ የኢራቅ ስም ማንሳታቸው እያነጋገረ ነው፡፡
ጉዳዩን አነጋጋሪ ያደረገው ደግሞ እ.አ.አ በ 2003 አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ ኢራቅ ስትልክ ትዕዛዙን የሰጡት ቡሽ መሆናቸው ነው፡፡
የ75 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት በአሜሪካ ዳላስ በተዘጋጀ የዴሞክራሲ ውይይት ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲንን ለመተቸት`` ሩሲያ ዩክሬንን ወረረች`` በማለት ፋንታ የኢራቅ ወረራ ብለው ነበር፡፡
ቡሽ ከወቅታዊው የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ጋር በተያያዘ፤ የሩሲያውን ፕሬዝዳንት እያወገዙ ሳለ ነው ስህተቱን የፈጸሙት፡፡ በዳላስ ባደረጉት ንግግር የፈጸሙትን ስህተት ወዲያው ቢያርሙትም መነጋገሪያነቱ ግን ቀጥሏል፡፡

ምንጭ ፦አል አይን
4.8K views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 17:39:35
የግል አካውንት እና የስራ አካውንት ደባልቆ መስራት ውጤቱ

የኢትዮ ቴሌኮም ትህትና ግን
5.5K views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 16:05:36
ሰበር ዜና...!!!

ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ እህል ጭነው የሄዱት ተሳቢ መኪኖች ሲመለሱ እያንዳንዱ መኪና 3 ሰው ከአልጋው ስር ደብቀው ለማስገባት ሲሞክሩ ንስሮቹ የአፋር ልዩሃይሎች ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ ተደብቀው ሊገቡ የነበሩትን ጁንታዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል። ሾፌሮቹ እስካሁን ሰዎቹ ለምን አላማ ደብቀው ለማስገባት እንደሞከሩ ማወቅ አልተቻለም። ሾፌሮቹ የWFP መኪኖች አይፈተሹም የሚል ማስተባበያ ቢያቀርቡም የአፋር ልዩሃይል ይሄ አሜሪካ አይደለም ከጠላት ቀጠና እየመጣችሁ እናንተን ሳንፈትሽ አናሳልፍም በማለት ፈትሸዋቸዋል።Ahmed Habib Alzarqawi

t.me//alzarkawihabib
6.3K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 21:47:35
የጀግንነት ጥግ!!!

ሴኔጋላዊው የPSG ተጫዋች እንድሪሳ ጋናን ጉዬ በግብረሰዶማውያን ቀለም የተፃፈ ቁጥር ያለበት መለያ ለብሼ አልጫወትም በማለቱ የተለያዩ ውግዘቶች እየደረሱበት ነው።

የተጫዋቹን ተግባር የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ያደነቁ ሲሆን "የሀይማኖት መርሆዎችን የትም በምንም ሁኔታ መጣስ የለባቸውም።"ሲሉ ተናግረዋል።

የተጫዋቹ ጉዳይ ዛሬ በአለም ሀሽታግ አንደኛ ሆኖ የዋለ ሲሆን የተለያዩ ድጋፎችን እና ውግዘቶችን እያስተናገደ ይገኛል።
7.5K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 21:14:14
7.3K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ