2022-05-14 17:17:21
የማለዳ ወግ ...
ከቶ ሸህ ከሊፋ ቢን ዛይድ ማን ነበሩ ?
==========================
* የሸህ ከሊፋ ለህዝብና ለሀገራቸው ...
* የሸህ ከሊፋ ብልህ ዲፕሎማሲ ...
* የሸህ ከሊፋ ሲወደሱና ሲወቀሱ ...
* ህልም አሳኪው የኤምሬት መሪ ...
ሸህ ከሊፋ ቢን ዛይድ ለሀገራቸው...
======================
ሸህ ከሊፋ ከባለ ራዕዩ አባታቸው ከሸህ ዛይድ አል ተነያን ህልፈት በኋላ እ.ጎ. አ ከ2004 ዓም ነበር የመሪነት ስልጣኑን የተረከቡት። ለተከታታይ 18 አመታት የአስተዳደር ዘመን የተባበሩት ኤምሬትን ካስረከቧቸው ከአባታቸው ከሸህ ዛይድ አል ተነያን የተሰጣቸውን አደራ ያልበሉ ትጉህ መሪ ነበሩ። ሸህ ከሊፋ በአጭር የእድገት ግስጋሴ የኤምሬት ዋና የገቢ የነዳጅ ዘይት ምርቱን ከፍ አድርገውታል። ቀጣይ ህልም ግባቸው ኢምሬትን ከነዳጅ ኢኮኖሚ መር ለማላቀቅ በስኬታማ መንገድ ጀምረው ጫፍ ላይ ያደረሱ ሸህ ከሊፋ ናቸው።
የተባበሩት ኤምሬትስ የታዋቂ አለም አቀፍ ኩባንያዎች መናህሪያ አድርገው ያደረጉ ፣ ዱባይንና አቡ ዳቢን የመሰሉ ውብ ስልጡን ፣ የዘመኑ ምጡቅ ከተማዎችን ገንብተዋል። በመደጋገፍ አመራር Team work ለሀገር ተቆርቋሪ አስተዳዳሪዎችን አፍርተው እና መድበው ከተሞቻቸው የአረቦች New York " ኑዩ ወርክ" የሚባሉ የዘመኑ ምቹ ከተሞች ላይ የንግድ ግብይት ማዕከላት አደራጀተዋል። ሸህ ከሊፋ ከነዳጅ መር ኢኮኖሚ ለመውጣት ከሰሯቸው ስራዎች መካከል የውጭ ባላሀብቶች በነጻነት ግዙፍ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በኢንዱስትሪ ፣ በቱሪዝም በስነ ቴክኒክ የስራ እድሎች እንዲሰማሩ ምቹ ሁኔታ የፈጥረ ብልህ መሪ ሸህ ከሊፋ ናቸው።
በሸህ ከሊፋ አመራር የተባበሩት ኤምሬት የቱሪዝም ውብ መዳረሻ እና የንግድ ቀጠና እንድትሆን ጥረው ግረው አሳክተዋል። ዛሬ ሀገራቸው በአለም አቀፍ ፖለቲካ መድረክ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገራት ተርታ በቀዳሚነት ያሰለፉ ታታሪ መሪም ሸህ ከሊፋ ቢን ዘይድ ናቸው ...
ሸህ ከሊፋ የውጭ ዜጎች በተባበሩት ኤሜ ምሬት የስራ እድል ፈጥረው ፣ የስራ ባህል ያለነበራቸውን ኤምሬታውያንን የስራ ባህል ከውጭ ዜጎች እንዲማሩ ያደረጉና ያሳኩ መሪ ናቸው። ሸህ ከሊፋ በውጭ ዜጎች ሰብአዊ መብት ረገጣ ከሚከሰሱትን አረቦች የተሻለ ፍትሃዊ አስተዳደርን በማስፈን ከፍ ያለ አድናቆት የሚሰጣቸውና የሚከበሩ መሪ ነበሩ። ከኤምሬት ነዋሪ እኩል የውጭ ዜጎችን አቅርበው በማሰራት ለሀገራቸው እድገትና ብልጽግና በማስፈን የሸህ ከሊፋ አስተዳደር የቀሩት የባህረ ሰላጤ ሀብታም አረብ ሀገራት ምሳሌ የሆኑ አርአያ መሪ ሸህ ከሊፋ ነበሩ ።
የተባበሩት ኤምሬትን ሀገረ መንግስት ግንባታ ህልማቸውንም በተግባር ሰርተው ያሳኩ መሪ ሸህ ከሊፋ የብልህ አመራራቸው ውጤት በ18 አመታት አስተዳደር ሀገራቸው ከፍ በማድረግ አዘምነዋል። ሸህ ከሊፋ ህዝባቸውን በሰላም እንዲኖር ፣ ሁሉም ሰርተው እንዲለዎጡና በተሻለ ምቾት እንዲኖሩ ያደረጉ ባለ ውለታ መሪ ነበሩ።
የሸህ ከሊፋ በአለም ዲፕሎማሲው ...
========================
ሸህ ከሊፋ ቢን ዛይድ ከአረብና ከአለም ሀገራት ጋር በነበራቸው ብልህ ዲፕሎማሲ ምስጉን መሪ ነበሩ። የነዳጅ ምርት ተቀባይና የስልጣኔ ውርርስ ሀገራቸውን ለማሳደግ ከአሜሪካና ከምዕራባውያን ባለጸጋ ሀገራት ጋር በተጓዙት ዲፕሎማሲ ግንኙነት ልዩ ክብር አሰጥቷቸዋል። ሸህ ከሊፋ በብርቱ ዲፕሎማሲው ከአሜሪካ ፣ ከአረብ ሀገራትና ከምዕራባውያን ስልጡን ሀገራት ጋር በላቀ የንግድ ትስስር ታቅፈው ለታላቋ ኤምሬት መሰረት ጥለዋል። የተባበሩት ኤሜሬት በመካከለኛው ምስራቅ የባህረ ሰላጤ ሀገራት መካከል የአሜሪካ የቅርብ አጋር አድርገው የነዳጅ ምርታቸውን ሰፊ ገበያ አሳክተዋል ። ነጃጅ ዘይት አቀብለው ፣ በነጻ ገበያው ስልጣኔ እና የቴክኖሎጅ እድገትን ወደ የተባበሩት ኤምሬት አስገብተዋል።
የተባበሩት ኤምሬት ከአሜሪካና ከቀሩት ምዕራባውያን ሀገራት ጋር በነበራቸው ወታደራዊ ግንኙነት መስክ የሀገራቸው የተባበሩት ኤምሬት መከላከያ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ እንዲታጠቅ አድርገዋል። ከአሜሪካና ከቀሩት ምዕራባውያን ሀገራት ጋር በተለያየ ወታደራዊ ዘመቻ የኢምሬት ተሳትፎ ይጠቀሳል። በተለይም እነ አሜሪካ በጸረ ሽብር ዘመቻ ስም በአረባዊቷ ኢራቅ በአፍጋኒስታንን ወረራ ሀገረ ኤምሬት ድጋፍ ሰጥታለች ። ሳውዲ በራሷ ጉዳይ "የአረቦች ህብረት " ብላ የመንን ስትዎርና ስትደበድብ የኤምሬት ጉልህ ተሳትፎ ብዙ አረብ ሀገራት ጋር አኮራርፏቸዋል።
የአረቦችን ወቀሳ ፣ ኩርፊያ ፣ ተቃውሞ በመላ ታግሰው ከአሜሪካና ከምዕራባውያን ጋር በአጋርነት ሲጓዙ ጥበብ በተሞላበት መንገድ ነበር ። በብልህ መንገዳቸው ሁሉ አኩራፊዎችን እያጎረሱ በስልት በመደለል ተቃውሞውን አብርደዋል። በመንገዳቸው የተባበሩት ኤምሬት የህዋ ሳይንቲስቶችን እንድታፈራና ወደ ህዋ ምርምር እንድትገባ በታላቅ ዲፕሎማሲያዊ ጥበብ ክፉ ደጉን ያለፉ መሪ ሸህ ከሊፋ ናቸው።
የሚወቀሱት ሸህ ከሊፋ …
=================
ሸህ ከሊፋ ቢን ዛይድ በብልህ አመራራቸው ቢመሰገኑም በአሜሪካ ፣ በምዕራባውያንና በሳውዲ አረቢያ ጋር የነበራቸው ወታደራዊ ግንኙነት ተከትሎ በተሳተፏቸው ዘመቻዎች ስህተቶች ፈጽመዋል ተብለው ብርቱ የሆነ ተቃውሞ ፣ ወቀሳና ትችት ይሰነዘርባቸዋል። ሀገራቸው ከሳውዲ አረቢያ ፣ ከአሜሪካ እና ምዕራባውያን ኃያላን ጋር ወታደራዊ ዘመቻ ተሳትፎ ባለግርማ በሚባሉት የኢራቁ መሪ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴንና የሊቢያውን መሪ ፕሬዚደንት ኮሎኔን ሙአመር ጋዳፊ ከስር ተለቅለው እንዲዎገዱ ኤምሬት በሴራው ተሳታፊ በመሆኗ በክህደት ትዎቀሳለች። አሁን ድረስ ባላለቀው በሳውዲ መራሹ እና በየመን ሁቲ አማጽያን ጦርነት የኢምሬት ቅድሚያ ተሳትፎ ወቀሳ አልተለየውም ። ሳውዲ አረቢያ፣ አሜሪካና ምዕራባውያን ለጥቅማቸው በጀመሩት የደነደነ ስውር ሴራ የተሸፈነ ዘመቻ ኤምሬት እያዎቀች ተሳታፊ በመሆኗ በሸህ ከሊፋ አመራር የተፈጸመ " ትልቅ ስህተት ነው " ሲሉ በሸህ ከሊፋ ላይ የሰላ ጭብጥ ሂስ የሚያቀርቡ አረቦች ቁጥር በርካታ መሆናቸውን አውቃለሁ።
ሸህ ከሊፋ ፣ አረቦችና ፍልስጥኤም …
=======================
"አረቦች ላለመስማማት ተስማምተው ወደ ስብሰባ ይገባሉ " የሚባሉትን የአረብ ህብረት ለማጠናከር አስተውለው የታገሉ ግን ያልተሳካላቸው መሪ ሸህ ከሊፋ ናቸው። ሁሌም የአረቦች ህብረትና መለያየት ዋነኛ ምክንያት በሆነው የፍልስጥኤም ነጻነት ጉዳይ በአደባባይ እና በህቡዕ ትግሉን ደግፈዋል ፣ የፍልስጥኤም ነጻ መካከል ያለውን ልዩነት እንዲፈታ አደራድረዋል። ዳሩ ግን በፍልስጥኤም የነጻነት ጥያቄ ዙሪያ የአረብ ሀገራቱ መካከል ያለው ልዩነትና አለመግባባት ብዙ አላራመዳቸውም ። ሸህ ከሊፋ በፍልስጥኤማውያን ነጻነት ትግል ለመደገፍ እና የፈራረሰች ጋዛን ለመገንባት በአረብ መሪዎች መግባባት አለመቻል ያደረጉት መከራ ሙሉ ስኬት ለማየት ባይታደሉም እስከ ህልፈታቸው ድረስ የቻሉትን ሰርተው ማለፋቸው አይካድም።
3.5K views14:17