2022-05-15 19:38:46
የአፋር ክልል ጤና ቢሮ፣ ከውጭ ድርጅቶች እና የዞን ሁለት አመራሮች ጋር በመሆን አሸባሪው የህወሃት ቡድን በዞኑ ላይ የሚገኙ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ላይ ያስከተለውን ውድመት ጎብኝተዋል!
¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶ ¶
በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን ወራሪው የህወሃት ሃይል በንፁሃን ህዝብ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት ከፍቶ ሴቶች፣ ህፃናት፣ አዛውንቶችን በማፈናቀል ለወራቶች ተቆጣጥሮ የነበረውን ኤሬብቲ፣ አብአላ፣ ኮነባ እና በራህሌ ወረዳዎች ሆስፒታልና ጤና ጣብያዎች ላይ ውድመት አድርሷል!
በዞኑ የህወሃት ሃይል ያስከተለውን ውድመት ተከትሎ የክልሉ ጤና ቢሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የኤሬብቲ፣ ኮነባ እና በራህሌ ጤና ጣብያዎች እቃ በማቅረብ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ አድርገዋል!
በጉብኝቱ ወቅት የነበሩ የውጭ ድርጅቶችም በአሸባሪው ህውሃት ቡድን ድርጊት በማዘን አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ ለክልሉ ቃል ገብተዋል!
የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ያሲን ሀቢብ የጁንታው ሃይል ወረራ ከፈፀመበትና ውድመት ማስከተል ከጀመረበት ሰዓት ጀምሮ የሚመለከታቸው አካል ጋር በመነጋገር የጤና ማቴሪያሎችን በዘመነ መልኩ እያስገባ ይገኛል!
4.5K views16:38