2023-01-04 14:27:32
በበዓላት ወቅት በሀሰተኛ መንጃ ፍቃድ የሚያሽከረክሩ ግለሰቦች በብዛት እንደመታየታቸው ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን አሳሰበ፡፡
በበዓል ግብይት ወቅት ወንጀል እንዳይፈጸም አደጋ እንዳይከሰት ምን ዝግጅት ተደርጓል ሲል አሀዱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰን ጠይቋል፡፡
በምላሻቸውም በበዓላት ወቅት ወንጀል ሊፈጸም ፤ የትራፊክ አደጋም ሊከሰት የሚችል በመሆኑ ማህበረሰቡ በብዙ ዘርፉ ጥንቃቄ ሊያድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በዚህ ረገድ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን እና የትራፊክ አደጋዎችን ለመከላከል የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
በዓላትን ብቻ መነሻ በማድረግ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መኖራቸውን የተናገሩት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ስርቆት፤ዝርፊያ፤ንጥቂያ ሌሎችም ወንጀሎች ሊፈጸሙ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
የበዓል ሰሞን ድንገተኛ አደጋዎች ጭምር ሊከሰት እንደሚችል የተናገሩት ኮማንደር ማርቆስ ሀሰተኛ መንጃ ፍቃድ ወይም ያለመንጃ ፍቀድ ሚየሽከርክሩ ሰዎች ጎልተው የሚታዩበት ነው ብለዋል፡፡
ለመዝናናት ነው በሚል ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ማሽከርከር ተገቢ እንዳልሆነ እና የሚያደርሰው አደረጋም የከፋ ነው ባይ ናቸው፡፡
ኮምሽኑም በዚህ ረገድ ዝግጅት በማድረግ ህገ-ወጥናትን በመካለከል ቀድሞ የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን
#አሐዱ_24 #Ahadu
1.9K views11:27