Get Mystery Box with random crypto!

የናይጄሪያ ጦር በዛምፋራ ግዛት በፈጸመው ጥቃት በርካታ ሽፍቶችን መግደሉ ታውቋል፡፡ የናይጄሪያ ጦር | AHADU RADIO FM 94.3

የናይጄሪያ ጦር በዛምፋራ ግዛት በፈጸመው ጥቃት በርካታ ሽፍቶችን መግደሉ ታውቋል፡፡
የናይጄሪያ ጦር ሀይል በአየር ሀይሉ እየታገዘና በምድር ጦሩ ባደረገው ጥልቅ አሰሳ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በትንሹ 16 ሽፍቶችን መግደሉን አስታውቋል፡፡
በናይጄሪያ ከምደርና ከሰማይ የተቀናጀና የተጠናከረ አሰሳ ለረዥም ጊዜ ሲፈለግ የነበረው የሽፍቶቹና የአሸባሪዎቹ ዋና መሪና አስተባባሪ ኪንግፒን ማምለጡም ነው የተነገረው፡፡
በዛምፋራ ግዛት የናይጄሪያ ጦር ሀይል በፈፀመው ጥልቅ አሰሳ ያመለጠው የሽፍቶቹና የአሸባሪዎቹ ዋና መሪና አስተባባሪ ክፉኛ ቆስሎ መሆኑም ተሰምቷል፡፡
የናይጄሪያ ጦር ሀይል አሰሳውንና ጥቃቱን የፈጸመው በአዲሱ የአውሮፓውያኑ 2023 አዲስ ዓመት ዋዜማ መሆኑን ዘገባው ያብራራል፡፡
የአሸባሪዎቹ ሀይሎች በመሪያቸው ላይ ስለተቃጣው የግድያ ሙከራ እጅጉን ማዘናቸውን የዘገበው ፐንች ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24