2023-01-09 14:26:10
በሌሎቹ የሃገሪቱ አካባቢዎችም የሽግግር ፍትህን መተግበር እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ፡፡
ባለፉት ጥቂት አመታት ግጭትና አለመረጋጋት ሰፍኖባቸው በቆዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ያስታወሰው ተቋሙ በሌሎቹ የሃገሪቱ አካባቢዎችም የሽግግር ፍትህን መተግበር እንደሚገባ ገልጿል፡፡
የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሰለባ የሆኑ ዜጎች ፍትህ እንዲያገኙ ለማስቻል የሽግግር ፍትህ ተግባራዊ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን ነገር ግን ትግበራው በሌሎቹም ግጭትና አለመረጋጋት ሰፍኖባቸው በቆዩና አሁንም ባልተረጋጉ አካባቢዎች ላይ መሆን እንዳለበት የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ለአሃዱ ገልጸዋል፡፡
ከነዚህም አካባቢዎች መካከል የኦሮምያ፣ ቤንሻንጉልና ደቡብ ክልሎች የሚገኙበት ሲሆን ይህም ሃገር አቀፍና ሙሉእ እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ያስችላል ነው ያሉት፡፡
ባለፉት ጥቂት አመታት ከሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ጦርነት ባሻገር በኦሮምያ፣ በቤንሻንጉል፣ ደቡብ እንዲሁም የጋምቤላ ውስን አካባቢዎች ግጭትን ተከትለው የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተለያዩ ጊዜያት ለህዝብ ይፋ መደረጋቸው ይታወሳል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24 #Ahadu_News_24 #News_24
1.5K viewsedited 11:26