2022-12-30 11:52:29
ሶሪያ ሩሲያና ቱርክ ከአውሮፓውያኑ 2011 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መስብሰባቸው ተነግሯል፡፡
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንና ከሶሪያው ፕሬዝዳንት ባሺር አልአሳድ ጋር ተቀምጠው ለመምከር የሚያስችላቸውን ሀሳብ ያመጡ መሆናቸው ተገልጻል፡፡
በዚያ መሰረትም የሶሪያ የቱርክና የሩሲያ የመከላከያ ሚንስትሮች በሩሲያዋ ዋና ከተማ ሞስኮው ውስጥ ተገናኝተው መምከራቸው ነው የተሰማው፡፡
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ኤርዶሃን በሰጡት መግለጫ በሶስቱ ሀገራት ሚንስትሮች ደረጃ የተጠራው ስብሰባ በስተመጨረሻው በሶስቱ ሀገራት መሪዎችም እንደሚደረግም መናገራቸው ይታወቃል፡፡
ቱርክና ሶሪያ በሶሪያ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ለ11ዓመት ይፋዊ የሆነ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንደሌላቸው ይታወቃል፡፡
የቱርኩ የዜና ማሰራጫ አናዶሉ በሰራው ዘገባ የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሁሉሲ አካር የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭና የሶሪያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሊ ሙሐመድ በሞስኮው ያደረጉት ውይይት ገንቢና ውጤታማ መሆኑን ገልጿል፡፡
ዘገባው፡-የዘ ናሽናል ነው፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.6K views08:52