2023-01-12 11:17:38
በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተካሄደ ያለዉን ቤት የማፍረስ ዘመቻን ለማጣራት በሄዱበት የታሰሩት የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ፍርድ ቤት በዋስ እንዲፈቱ መወሰኑ ተገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተካሄደ ባለው ቤት የማፍረስ ዘመቻ ምክንያት ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ሶስት የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች እና አንድ ሹፌር ታህሳስ 27 ዓለም ባንክ አካባቢ ጥቆማውን ለማጣራት በሄዱበት ወቅት በፖሊስ ተይዘው አራቱም ሰራተኞች መታሰራቸዉ ይታወሳል፤
ሠራተኞቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ከተጠየቀባቸው 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ውስጥ አምስት ቀናት ተፈቅዶ በትላንትናዉ ዕለት ለሁለተኛ ጊዜ በሰበታ ወረዳ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በዋስ እንዲወጡ መፍቀዱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘየደ ገብረፃዲቅ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ የጠየቀዉን የ7 ቀን ቀነ ቀጠሮ ዉድቅ በማድረግ የዋስትና መብታቸዉ እንዲከበር ለፖሊስ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ገልፀዉ በዛሬዉ እለት ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታዉቀዋል፡፡
ኢሰመጉ የታሰሩት ሰራተኞቹ እንዲፈቱ ለፌደራል መንግስት፤ ለኦሮሚያ ክልል እና ለተለያዩ ተቋማት ደብደቤ ማስገባቱ ይታወሳል፡፡
የኢሰመጉ ሰራተኞች በተፈቀደላቸዉ የዋስ መብት መሰረት ዛሬ ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
2.7K views08:17