2023-01-17 16:26:23
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ኃይሎች ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን ህዝቡን ማድመጥ የሚጠበቅባቸዉ ጊዜ ላይ መሆናቸዉን አረጋጠዋል፡፡
የሰላም ስምምነቱ ያመጣውን ውጤት መሰረት በማድረግ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ወደ ክልሉ በማምራት ህዝቡ የሚገኝበትን ሁኔታ መረዳት አለባቸው ሲሉ ነው የፖለቲካ ኃይሎች የገለጹት፡፡
አሁን ህዝቡ እኛን ያድምጠን የምንልበት ጊዜ አለመሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል ያሉት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች ም/ል ኃላፊው ተስፋዬ አለማየሁ ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደም ባሉት ጊዚያት ለህዝቡ እኛ የፖለቲካ ኃይሎች ብዙ ተናግረን የፈታንለት ብዙም ችግር የለም ስለሆነም ከአሁን ወዲህ የህዝቡን እውነተኛ ስሜት ብቻ በማድመጥና ጦርነቱ ካስከተለው ጉዳት እንዲወጣ በማገዝ ጊዚያችንን ማሳለፍ ይጠበቅብናል ነዉ ያሉት፡፡
ይህንን ከማድረግ ውጭ በዚህ ስዓት እኔ እሻልሃለሁ የምንልበት ሞራል የለንም ሲሉም ገልጸዋል
በተጨማሪ የባይቶና ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበር ክንፈ ገ/ዮሐንስ እንዳሉት የተጀመረው የሰላም ሂደት ዘላቂ እንዲሆን ሂደቱን ወደኋላ የሚጎትቱ ነገሮችን በማስወገድ መስራት እንደሚገባ ነው ያነሱት፡፡
በተጨማሪም በሁለቱም ወገኖች በደል ያደረሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ እንሰራለን ነዉ ያሉት፡፡
ይህን ማድረግ እስካልተቻለ ድረስ በዘላቂነት የህዝቡን ሰላም ማረጋገጥ አይቻልም ይህ እንዲሆን ደግሞ በሚገባን ልክ እንሰራለን ሲሉ አስታዉቀዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
1.8K views13:26