2022-12-28 13:48:27
ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በሁለት ዙር 17 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሰብአዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታወቀ፡፡
በፌድራል መንግስቱ እና በህዉሀት መካከል የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ በሁለት ዙሮች ወደ 17 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሰብአዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ የተላከ ሲሆን አንዱን በሽሬ በኩል አንዱ ደግሞ በመቀሌ በኩል መላኩን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰብአዊ ዲፕሎማሲ እና የኮምንኬሽን አገልግሎት ሀላፊ አቶ መስፍን ደረጄ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡
የሰብአዊ እርዳታዉ ቀጣይነት ያለዉ መሆኑን ገልፀዉ ህብረተሰቡን በማስተባበር እና ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ቀጣይነት ያለዉ ድጋፍ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን አስታዉቀዋል፡፡
ሰብአዊነት የሚሰማዉ ድጋፍ ማድረግ የሚችል ማንኛዉም ዜጋ በ9400 አጭር የፅሁፍ መልዕክት እና በየአካባቢዉ ባሉ የቀይ መስቀል ቅርንጫፎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን "በበይነ መረብ" በሚሰሩ የተለያዩ አማራጮች መጠቀም እንደሚችሉ አስታዉቀዋል፡፡
አለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እያሳዩ በመሆናቸዉ ድጋፉን እንዲያደርጉ በመነጋገር ላይ መሆናቸዉን ገልፀዋል፡፡
ሰብአዊ እርዳታዉን በማድረግ ህይወት የማዳን ስራዉ በተቻለ መጠን እንደሚቀጥል አቶ መስፍን አክለዉ ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.2K viewsedited 10:48