2022-12-24 13:03:48
ሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ማድረጉ የገለልተኝነቱ ጥያቄ እንደማያስነሳበት ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እና የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሥምምነት ስለመፈራረማቸው ተገልጿል፡፡
ሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ማድረጉ ገለልተኝነቱን ጥያቄ ውስጥ አይከተውም ወይ ሲል አሀዱ ጠይቋል፡፡
ምላሽ የሰጡት የኮምሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ዬናስ አዳዬ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተለያየ አመለካካት፤ ሀይማኖት እና ባህል ያላቸው ዜጎች የሚገኙበት መሆኑ ከወገንተኝነት ይልቅ ገለልተኝነትን የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሀገር በቀል እውቀቶች፤ የምርምር ስራዎች የሚገኝባቸው እንደ መሆኑ ማንኛውም የፖለቲካ አመለካከት አይኖርም ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከእውቀት ማዕከልነታቸው ጋር ተያይዞ አስፈላጊ እገዛዎችን እንዲያደርጉ ለማስቻል እና በትምህርት ተቋማቱ ያሉትን ቁሳቁሶች ለሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ለመጠቀም እድልን መፍጠርም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24 #Ahadu_News_24 #News_24 #Ahadu #News
1.6K views10:03