2022-12-23 12:02:12
በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ያለመከሰስ መብት ያላቸው ሰዎች ላይ የተፈጸሙ እስሮች ህጋዊ መሰረት የሌላቸው እንደሆኑ ተገለጸ፡፡
ፍርድ ቤት ነጻ ያለውን ፖሊስ በድጋሚ የሚያስርበት ሁኔታ እየተስተዋለ እና በአጠቃላይ አሁን ለሚታዩ ችግሮች የሰሜኑ ክፍል ጦርነትን በምክንያትነት መጥቀስ ተገቢ ነው ወይ የሚል ጥያቄ በትላንተናዉ እለት በአሀዱ መድረክ ተነስቷል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የፍትህ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና የኮምንኬሽን ጉዳዮዎች ዳይሬክተር አቶ አወል ሱልጣ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የነበረው ጦርነት በሌሎች ስራዎች ላይ እንቅፋት ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ሌሎች ስራዎችን መስራት እንዳንችል አድርጎናል ማለት አያስደፍርም ብለዋል፡፡
2014ዓ.ም በሰሜኑ ክፍል ከነበረው ጦርነት ውጪ ከ24 ሺ በላይ የሚሆኑ ወንጀለኞችን ማስቀጣት እንደተቻለ እና ከ15ሺ በላይ መዛግብቶች በላይ ውሳኔ እንደተሰጠባቸውም ገልጸዋል፡፡
የፖሊስ ፤ፍርድ ቤቶች እንዲሁም የፍህት ሚኒስቴር ቅንጅታዊ ስራን በተመለከተ እርምት ለመውሰድ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡
የፓርላማ አባላት፤ዳኞች ሌሎችንም ጨምሮ ያለመከሰስ መብት ያላቸው ሰዎች እጅ ከፍንጅ ወንጀል ሲፈጽሙ ካልተያዙ በቀር በቁጥጥር ስር እንደማይውሉም ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.5K views09:02