Get Mystery Box with random crypto!

AHADU

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahadu_goh — AHADU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahadu_goh — AHADU
የሰርጥ አድራሻ: @ahadu_goh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.37K
የሰርጥ መግለጫ

የ 𝚈𝙾𝚄 𝚃𝚄𝙱𝙴 ቻናሌን 𝚂𝚞𝚋𝚜𝚌𝚛𝚒𝚋𝚎 👏 ያድርጉ
👇👇 👇👇
https://www.youtube.com/c/Ahadu
ለማንኛውም አስተያየትዎ - @Ahadu_Commbot

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-19 04:22:37
ድንች በፈላ ውሀ ቢቀቀል ውስጥ አቅም ያጣና ይደክማል፤ እንቁላል ግን በሞቀ ውሀ ሲያገኝ ውስጡ ያለው ፈሳሽ ብሶበት ጠንካራ ይሆናል፤ አየህ በዚህ አለም ወሳኙ የገጠመህ ችግር አይደለም፤ ማርሽ ቀያሪው ያንተ ምላሽ ነው።

አንተም ወይ እንደ ድንቹ ትልፈሰፈሳለህ ወይ እንደ እንቁላሉ የገጠመህ ፈተና ላይ ትጠነክራለህ፤ ወዳጄ ችግር የሚያበረታህ እንጂ የሚሰብርህ ሰው መሆን የለብህም!


ᴊᴏɪɴ ᴜs @Ahadu_Goh
@Ahadu_Goh
 
@Ahadu_goh
1.6K views01:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 07:57:25 ለዲኤስቲቪ ተዎንያን እንፈልጋለን.
በሁሉም ፆታ ከ24-70 የዕድሜ ክልል እናተም ተሳተፉ ለጓደኞቻችሁም ንገሩ ።

0943854812 ለመደወል
0974737255 ለቴሌግራም
1.9K views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 09:02:58
አመለካከትህ፣ በራስ መተማመንህ፣ የጊዜ አጠቃቀምህ፣ የገንዘብ አያያዝህ፣ ለራስህ የምትሰጠው ቦታ፣ አላማህን ማወቅና በእቅድ መመራት ስትጀምር ብዙ ለውጥ ታያለህ!

ራስህ ላይ ስትሰራ እመነኝ ወዳጄ ኪስህ የሚገባው ገንዘብ፣ የፍቅር ግንኙነትህ ወይ የቤተሰብ ግነኙነትህ፣ መንፈሳዊ ህይወትህና በዙሪያህ ያሉ ነገሮች በሙሉ ይቀየራሉ! ህይወትህ የሚለወጠው አንተ ስትለወጥ ብቻ ነው!

@Ahadu_goh
https://www.youtube.com/c/Ahadu
476 views06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 07:12:42
ስኬት እንደ ኪራይ ቤት ነው፤ ገዝተኸው ቁጭ ማለት አትችልም ስለዚህ ሁሌም ትጥራለህ፣ ጠዋት ትነሳለህ፣ ታነባለህ፣ ትሰራለህ፣ ትማራለህ በቃ ለአላማህ እስከጠቀመህ ድረስ ዋጋ ትከፍላለህ።

ይሄን ማድረግ ቀላል አይደለም! ቀላል ቢሆንማ ሁሉም ያደርገው ነበር፤ ግን አትርሳ ወዳጄ ቀላሉን ከሰራህ ህይወት ከባድ ትሆናለች ከባዱን ከሰራህ ግን ህይወት ቀላል ትሆናለች።

@Ahadu_goh
691 viewsedited  04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 09:29:57
መሬትን ስትረግጣት ታሰምጠኝ ይሆን አንድ ነገር ታደርገኝ ይሆን ብለህ አትረግጣትም፤ አምነህ ነው ምትራመድባት፤ ታዲያ መሬትን የፈጠረውን ፈጣሪ ምን ያህል ታምነዋለህ?

አንድ ነገር አስተውል እውቀት ከሞላው እምነት የሞላው ይበልጣል።

ዳዊት ጎልያድን እንዲጥለው ያደረገው ጉልበቱ አይደለም!

የሆነ ነገር ጀምረህ የምታቆመው እኮ እምነት ስለሌለህ ነው፤ ነገሮች ባልፈለከው መንገድ ሲሄዱ አይ ይሄ ነገር ለኔ አይሆንም ብለህ ታቆማለህ። ለምን? ስለማታምን ነዋ!

 
@Ahadu_goh
796 views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 16:34:24
በዚህ አለም ማዳመጥን የመሰለ ኃይል የሚሰጥ ነገር የለም፤ ለምን?

ብዙ ስታዳምጥ ብዙ ስለማታወራ ስህተት አትሰራም

ብዙ ስታዳምጥ ሳታስበው ብዙ እያወክ ነው

ሰዎችን በተመስጦ ስታደምጣቸው እንደምታከብራቸው ስለሚያስቡ ካንተ ጋር እንደመሆን የሚያስደስታቸው ነገር የለም (በተለይ ሴቶች ለሚያደምጣቸው ወንድ ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ)

ሁሉንም አድምጠህ በመጨረሻ የምትናገር ከሆነ ያንተ ሀሳብ የማሸነፍ ዕድሉ ሰፊ ነው።

ወዳጄ ምንም ቢሆን አይጎዳህም አሪፍ አዳማጭ ሁን!
 
@Ahadu_goh
814 views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 08:52:29
ልብስ ቢቆሽሽ ይታጠባል፣ ትንሽ ጊዜ ከቆየ ደግሞ በሌላ ልብስ ይተካል ግን እስክንሞት ድረስ አንድ ልብስ ብቻ መልበስ ቢኖርብን የምናደርገውን ጥንቃቄ አስቡት እስኪ?
ያ አንድ ልብስ እንዳይቆሽሽ ስንጠነቀቅ፣ ከቆሸሸብን ደግሞ ስናጥበው እንዳይሳሳ ስንጠነቀቅ፣ በቃ በተቻለን አቅም እኛ ሳናልቅ እሱ ቀድሞ እንዳያልቅ እንጠነቀቃለን።

የተሰጠን ህይወት እንደዚህ ልብስ ነው፤ ሌላ ተቀያሪ የለንም። ታዲያ ለምንድነው ግድየለሽ የምንሆነው? ሰዎች ምን ይሉኛል ብለን የማንፈልገውን የምናደርገው? አንድ አይን ያለው ሰውኮ በአይን አይቀልድም! የተሰጠንን የህይወት ዘመን የምንፈልገውን ለማሳካትና በደስታ ለማጣጣም መጠቀም አለብን።
 
@Ahadu_goh
852 views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 14:19:27
"አንድ ሰው መኪና ቢኖረውና የሚሄድበት ቦታ ግን ከሌለው ቤቱ ታቅፎት ይቀመጣል፤ የሚሄድበት ቦታ ያለው ሰው ግን መኪና ባይኖረው በታክሲ ወይ በእግሩ ይሄዳል፤ እግር ባይኖረው እንኳን በዳዴም ቢሆን መድረስ ወደሚፈልግበት ለመሄድ ይንፏቀቃል።

አየህ አላማ የሌለለው ሰው እንደ መጀመሪያው ሰው ነው! ገንዘብ ቢኖረው ጤና ቢኖረው ሁሉ ቢሟላለት እንኳን እዛው ታቅፎት በዘፈቀደ ይኖራል። አላማ ያለው ሰው ግን ምንም ባይኖረው እንኳን መድረሻ ግብ ስላለው ያንን ለማሳካት ሁሌም ይሮጣል። አላማ ወሳኝ ነው!"

 
@Ahadu_goh
877 views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 09:06:23
𝙰𝙷𝙰𝙳𝚄
ውሃ በተሞላ ድስት ውስጥ አንዲት እንቁራሪት ብንጨምርና ከዚያም ውሃውን ማፍላት ብንጀምር፤ ውሃው እየፈላ በሄደ ቁጥር እንቁራሪቷም የሰውነት ሙቀቷን ማስተካከል ትጀምራለች፡፡

☞ የውሃው ሙቀት ከፍተኛ እየሆነ ሲሄድ እሷም የሰውነቷን ሙቀት በዛው ልክ ማስተካከሉን ትቀጥላለች፡፡ የውሃው ሙቀት ጨምሮ የመፍላት ነጥብ (boiling point) ላይ ሲደርስ ግን ማስተካከል የማትችልበት ደረጃ ስለደረሰ እሯሷን ለማዳን ከድስቱ ዘላ ለመውጣት ትፈልጋለች ትሞክራለች፤ ግን ዘላ መውጣት አቅም አይኖራትም አትችልም፡፡
ምክንያቱም ያላትን አቅም ሁሉ ሙቀቷን በማስተካከል የውሃውን ቃጠሎ ለመከላከልና ለመላመድ ባደረገችው ተጋድሎ ጨርሳዋለችና፤ ወዲያው ትሞታለች፡፡

እንቁራሪቷን ምን ገደላት?
አብዛኞቻቸችን የፈላ ውሃ እንል ይሆናል፤ እውነታው ግን ይህ አይደለም ፡፡ እንቁራሪቷን የገደላት የፈላው ውሃ ሳይሆን መች መዝለል እንዳለባት የመወሰን አቅም ማጣቷ ነው፡፡

አብዛኞቻችን ከሰዎችም ይሁን ከነገሮች ጋር ያለንን ነገር ለማስተካከልና ለመላመድ እንሞክር ይሆናል፤ ግን እስከ መቼ ማስተካከል እንዳለብንና መች መወሰን እንዳለብን ማወቅ ይሳነናል፡፡
አንዳንዴ ነገሮችን የለመድናቸውና ለኛ የማይጎዱ መስለው ይታዩናል፤
በመጨረሻው ቅፅበት ግን እንዳልለመድናቸው ቢገባንም
ማምለጥና መውጣት የማይቻለን ሰአት ይሆናል፡፡ በጥፋት/ወንጀል/ መንገድ ውስጥም ስንሆን እንዲሁ ነው፤ ትንሹን ወንጀል እንለምደዋለን የሚጎዳን አይመስለንም፤ ደስታ ውስጥ ያለን ይመስለናል፤ ደስታው ሙቀት ይፈጥርልናል፡፡ ሙቀቱ ወደ እሳት የተቀየረ ጊዜ ግን . . .!!!??

ከሙቀቱ መውጣት ካልቻልን ከእሳት እንደማንወጣ እውን ነው!
ሙሉ አቅም ባለን ጊዜ እንዝለል!!!
 
@Ahadu_goh
78 views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 15:38:10
'እስከዛሬ መጀመር ነበረብኝ' እያሉ ራሳቸውን የሚወቅሱት ሰነፎች ናቸው፤ 'ዛሬ ያውም አሁን እጀምራለው! ምርጡ ጊዜ ከፊቴ ነው ያለው' ይህ የስኬታማ ሰዎች አመለካከት ነው። ከጎደላቸው ይልቅ ያላቸውን፤ ካጡት ይልቅ ያገኙትን አይተው በጎ አስበው በጎ ይሰራሉ።

የሌለህንማ ልቁጠር ካልክ የማቱሳላ ዕድሜ አይበቃህም፤ ባለህ ተደሰትና ሁሉንም በጥረቴ አሳካዋለው በል! እህቴ የጎደለሽን አይተሽ ከማዘንሽ በፊት በተሰጠሽ አመስግነሻል? ገና ብዙ ጊዜ አለሽ እኮ ለምድነው ጊዜዬ አለፈ፣ ምንም አልሞክርም የምትዪው? ያለፈው ጊዜ እንደ ንፋስ ነው አልጨብጠውም የሚመጣው ግን የኔ ነው በይ!

ᴊᴏɪɴ ᴜs @Ahadu_Goh
@Ahadu_Goh
273 views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ