Get Mystery Box with random crypto!

AHADU

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahadu_goh — AHADU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahadu_goh — AHADU
የሰርጥ አድራሻ: @ahadu_goh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.37K
የሰርጥ መግለጫ

የ 𝚈𝙾𝚄 𝚃𝚄𝙱𝙴 ቻናሌን 𝚂𝚞𝚋𝚜𝚌𝚛𝚒𝚋𝚎 👏 ያድርጉ
👇👇 👇👇
https://www.youtube.com/c/Ahadu
ለማንኛውም አስተያየትዎ - @Ahadu_Commbot

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 20

2022-07-12 21:36:09
ስለ 46ተኛው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አንዳንድ መረጃዎች

እኤአ በ1972 ባይደን የመጀመሪያ
ባለቤታቸውን ኒሊያ እና ሴት ልጃቸውን ናሆሚ በመኪና አደጋ የተነጠቁ ሲሆን
በ2015 ሌላኛውን ወንድ ልጃቸው
በጭንቅላት ካንሰር ተነጥቀዋል፡፡

ባይደን ከመጀመሪያ ፍቅረኛቸው ጋር
በነበራቸው ሁለተኛ የእራት ግብዣ ቀጠሮ ላይ ገንዘብ አልነበራቸውም፡፡

ጆባይደን ወደ ቬትናም ጦርነት ሊያመሩ የነበረ ቢሆንም የአስም ህመም ስለነበራቸው ከጦርነቱ ቀርተዋል፡፡ አሜሪካ በዚህ ጦርነት ላይ ብዙ እልቂት ስላጋጠማት ምናልባትም ህይወታቸው ሊያልፍ ይችል ነበር፡፡

እኤአ በ1988 እና በ2008 ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተወዳድረው ነበር፡፡
በአሜሪካ ታሪክ በእድሜ ትልቁ ፕሬዝዳንት በመሆን ነጩ ቤተመንግስት ገብተዋል፡፡

ሲጋራ አጭሰውም አልኮል ጠጥተው
አያውቁም ምክንያቱም ቤተሰቦቻቸው በአልኮል እና በሲጋራ ዋጋ ከፍለዋል፡፡

ጆ እና ጂል ባይደን የተሰኘ ድጋፍ የሚያደርግ ፋውንዴሽን ያላቸው ሲሆን በህፃናት፡ ሴቶች እና በካንሰር በተጠቁ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በ2007 ተመስርቷል፡፡

በከባድ የአንገት ህመም የተነሳ ባይደን ለሁለተኛ ጊዜ ያህል የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ህክምና አድርገዋል፡፡

በአንድ ወቅት ራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ አድርገው ነበር፡፡

@Ahadu_goh
@Ahadu_goh
1.2K views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 23:29:14
ክፍል ውስጥ በሚማርበት ጊዜ የቀን ህልመኛ ነው ይሉት ነበር መምህሮቹ ። ጋዜጣ እየዞረ ስለሚሸጥ ክፍል ውስጥ እንቅልፍ ይጥለው ነበር ፤ ከህፃንነቱ ጀምሮ ጋዜጣ ላይ የሚወጡ የካርቶን ስእሎችን አስመስሎ ለመስራት ይጥር ነበር ። አርቲስት መሆን ትልቁ ህልሙ ነበር አኒሚሽን መስራት ደግሞ ፍላጎቱ ነበር ። የመጀመሪያውን ስቱዲዮውን ቢገነባም ኪሳራ አጋጠመው ፤ ተከታታይ የአኒሜሽን ታሪኮችን ቢያዘጋጅም የባለቤትነት መብቱን እና የሚያገኘውን ትርፍ አጋሮቹ ከለከሉት ።

በዚ ብስጭት እና እልህ ከሁሉም ሰው ልብ ውስጥ የማይጠፋ የፊልም ገፀ ባሃሪ ፈጠረ #ሚኪ_ማውዝ የሚባል ፤ ከዛም በድፍረት የመጀመሪያ የሆነውን የአኒሜሽን ፊቸር ፊልም ሰራ ፤ በኦስካር ታሪክ ውስጥ ሪከርድ በሚባል ደረጃ 59 ጊዜ ታጭቶ 22 ጊዜ ያሸነፈ ሰው ነው ። በአለማችን ከፍተኛውን ገቢ የሚያስገባውን ዋልት ዲዝኒ ስቱዲዮ መስራች ከመሆኑም በላይ የፕላኔታችን የደስታ መንደር የሳቅ ጥግ የሆነውን ዲዝኒ ላንድ የተባለውን አስገራሚ አለም የገነባ ሰው ነው ።

ዋልት ዲዝኒ ይባላል የሰው ልጅ የሚፈልገውን ሁሉ ማሳካት እንደሚችል ከሱ በላይ ምስክር የለም።

@Ahadu_goh
@Ahadu_goh
1.6K views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 23:10:06
ዛሬ የአንጋፈው አርቲስት የ ክቡር
ዶክተር ቴድሮስ ካሳሁን የልደት ቀን ነው

መልካም ልደት ቴዶ

@Ahadu_goh
1.4K views20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 22:17:43
7% የሚሆኑ ወንዶች #Paruresis በተባለ የጭንቀት በሽታ የተጠቁ ናቸው ይህም ማለት ሌሎች ሰዎች በአቅራቢያቸው ካሉ ሽንት መሽናት አለመቻል ነው::

@Ahadu_goh
@Ahadu_goh
1.5K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 16:13:14
የቀጠለ

ያም ጥቁር ሰው በምንም መካካሻ ልትሰጠኝ አትችልም አለኝ እኔም ለምን አልኩት እኔ የሰጠሁህ ደሃ በነበርኩ ጊዜ ከድህነቴ ነው፡፡ አንተ ግን ልትሰጠኝ የመጣኸው ባለጠጋ በሆንክ ጊዜ ነው፡፡ እነዚህን ሁለቱን እንዴት አካክሰህ ልትሰጠኝ ትችላለህ፡፡

ቢልጌትም ያጥቁር ወጣት በርግጥም ከእኔ የሚበልጥ ባለጠጋ ነው፡፡ ለመስጠት ባለጠጋ መሆንህን ወይም ባለጠጋ እስክትሆን ድረስ አትጠብቅ ፡፡ መስጠት የልብ ጉዳይ ነው እንጂ የአቅም ጉዳይ አይደለም፡፡


@Ahadu_goh
@Ahadu_goh
1.7K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 16:07:50
"ቢልጌትስ በሐብት የሚበልጠኝ አንድ ጥቁር ብቻ ነው" አለ

የአለማችን ቀዳሚ ባለጠጋ በአንድ ኢንተርቪው እንዲህ ተጠየቀ ከአንተ የሚበልጥ ባለጠጋ ማን ነው ?
ከአንተ የሚበልጥህ ባለጠጋ አለ ?

‹‹አዎ የሚበልጠኝ ሰው አለ፡፡ የሚበልጠኝ አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ከብዙ ዓመት በፊት ወደ ኒውዮርክ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ወደ ኒውዮርክ ለመሄድ አየር መንገድ ላይ ሳለሁ የተለያዩ ጋዜጦችን የጋዜጣ አዟሪዎች እጅ ላይ አየሁ፡፡ ካየኋቸው ጋዜጦች መካከል አንዱን ወደድኩት ለመግዛት አስቤ ኪሴ ስገባ ዝርዝር ስላጣሁ ሳልገዛው መልሼ ተውኩት፡፡
በድንገትም አንድ ጥቁር ጋዜጣ አዟሪ ልጅ መጣና ጋዜጣውን ሰጠኝ፡፡ ዝርዝር የለኝም አልወስደውም አልኩት እርሱም ችግር የለውም በነጻ ውሰደው አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡

ከሦስት ወር በኋላ ተመልሼ በዚያው አየር መንገድ ማለፍ ነበረብኝና በዚያ አየር መንገድ ሳልፍ አሁንም አጋጣሚ ሆነና ያንን ጋዜጣ አዟሪ ጥቁር ልጅ አገኘሁት፡፡ አሁንም በነፃ ጋዜጣ ሰጠኝ፡፡ እኔም በነፃ አልቀበልህም አልኩት እርሱም ግድየለም ከትርፌ ላይ እቀንሳለሁ ውሰድ አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡

ከ19 አመትም በኋላ ባለጠጋ ከሆንኩ በኋላ ያንን ልጅ ፈልጌ ለማግኘት ወሰንኩና ፈለኩት ከአንድ ወር ተኩል ፍለጋም በኋላ አገኘሁት፡፡ ከዚያም አወቅከኝ ብዬ ጠየኩት ፡፡ አዎ አውቅሃለሁ ዝነኛው ቢልጌት አይደለህም አለኝ፡፡ ከብዙ አመት በፊት ሁለት ጊዜ ጋዜጣ በነጻ ሰጥተኸኛል፡፡ ያንን ውለታህን አካክሼ መመለስ እፈልጋለሁና የፈለከውን የትኛውንም ነገር እሰጥሃለሁ ጠይቀኝ አልኩት፡፡

ይቀጥላል ...
@Ahadu_goh
@Ahadu_goh
1.5K views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 19:04:57
በዚህ አለም ላይ የበሽታዎች ሁሉ በሽታ ለማንም ሰው ምንም አይነት መፍትሄ የማይሰጥ ሰው ሆኖ መኖር ነው” - Mother Teresa

የአንድን ሰው ችግር ለማቃለል እንደተፈጠርክ አድርገህ ራስህን ማየት መጀመር አለብህ፡፡ አንድን ነገር ለውጥ! አንድን መልካም ፈር ቅደድ! ለአንድ ሰው መፍትሄ ሁን! አንድ ሰው በብዙ ቢለፋ እንኳ በፍጹም ሊጨብጠውና ሊደርስበት የማይችለው ነገር አንተ ጋር ሊኖር ይችላል፡፡ ለዚህ ሰው ነገሮችን ልታቀልለትና መንገድ ልትከፍትለት ትችላለህ፡፡

በዘመንህ ያሉትን ለራሳቸው ብቻ ለመኖር የወሰኑትን ሰዎች የሚያሳፍርና ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ትውልድ ደግሞ ፈር የሚቀድድ መንገድ ፍጠር፡፡ ይቻላል!!!

@Ahadu_goh
@Ahadu_goh
1.6K viewsedited  16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:15:52 አነጋጋሪው ቪዲዮ ተለቋል አሁኑኑ እዩት!



1.5K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:14:53
#የቀጠለ...

ከለታት አንድ ቀን የማንዚማንን ህይወት የቀየረ የእናቱን እንባ ያበሰ ነገር ተፈጠረ…afrimax english የተባለ ማሀበራው ድረገፅ በልጁ ታሪክ በመሳብ ታሪኩ ላይ የሚያጠነጥን ዘጋቢ ፍልም ለአለም እንካቹ አለ። የማዚማን እናት አምስት ልጆችን ወልዳ የሞቱባት ቢሆንም ከባለቤቷ ጋር በርከክ ብሎ ነብስ ያለው ልጅ እንዲሰጣቸው ፈጣሪን ለምኖ ከፈጣሪ የተሰጣቸው ውድ ልጇ መሆኑን፡ አባቱ ልጁ በተወለደ በሁለተኛ አመቱ በመምቱ ማንዚማንን የማሳደጉ ሀላፋነት በእናቱ ጫንቃ ላይ የተጣለ መሆኑን በዘጋቢ ፋልሙ ተናግራለች።

ይህ ዘጋቢ ፋልም ከተለቀቀ በኋላ ማንዚማን በብዙዋች ዘንድ መናጋገርያ ሆነ። አለም አቀፍ የዜና አውታሮች ሁሉ የፋት ለፋት ገፅ እርዕስ አደረጉት። በታዳጊው ታሪክና በእናቱ ፅናት የብዙዋቹ ልብ ተነካ። እንዴት እንርዳቸው በምን እናግዛቸው የሚሉ የእርዳታ እጃቸውን የሚዘረጉ በዙ…የዘጋቢ ፋልሙ መለቀቅ ተከትሎ በተከፈተ gofundme (ጎ ፈንድ ሚ) አካውንት በስማቸው ተከፈተ።

የማንዚማን እናት የዚህ አይነት ፍቅር ከአለም ላይ አለ? ብላ እስክትጠይቅ ብዙ የእርዳታ እጆች ተዘረጉላት። በህልም አለም ያለች እስኪመስል በአካወንታቸ ሚሊዮን ዶላሮች ተለገሰ። የፅናትዋ ዋጋ፡ የምስጋናዋን ክፍያ ተቀበለች። ታሪክ ተቀይሮ ልጇን ዝንጆሮ ዝንጆሮ… እያሉ ያሳድዱት የነበሩ ሳይቀሩ አብረውት ፎቶ ሊነሱ ይማፀኑት ጀመረ።
…አምላክ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ሆነው በልጆቻቸው ተስፋ የማይቆርጡ እናቶችን እንባ ያብስ…


@Ahadu_goh
@Ahadu_goh
1.7K views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:10:36
ብዙዋቻቹ ምስሉ በመሀበራዊ ሚዲያዋች ሲዘዋወር አይታቹ ይሆናል። ማንዚማን ኤሊ ይባላል። ማንዚማን ኤሊ በደቡብ ሩዋንዳ በምትገኝ አንዲት መንደር ለየት ባለ አፈጣጠሩ በሰፈሩ የተጠላ፣የተገፋና እንደዝንጆሮና ጉሬላ የሚቆጠር የ23 አመት ልጅ ነው፡፡ ማንዚማን ኤሊ ከቤቱ የወጣ እንደሆን መንደርተኛው ሁሉ ዝንጆሮ ዝንጆሮ ጉሬላ ጉሬላ …እያለ ይጮህበታል።

ማንዚማን ኤሊ
ድምፅ የሚረብሽው አይነት ልጅ ስለነበር ጩህቱን ሽሽት መንደሯን ለቅቆ ወደ ጫካ ይሮጣል። መከረኛ እናቱ ልታስቆመው እያለቀሰች ትከተለዋለች፡ ማንዚማን ሲሮጥ ፈጣን በመሆኑ ለእናቱ እሱን ማስቆም በጣም ከባድ ነው። እናቱ ልጇን ለማስቆም በሳምንት እስከ 200 ኪ.ሜ የሮጠችበት ግዜያት ነበሩ …በዚህ ሁኔታ መቀጠል ቢከብዳት ከገመድ በተሰራ መጥለፍያ ተጠቅማ መሮጥ ሲጀምር ጠልፋ ትይዘዋለች፡፡

እናቱ አምስት ልጆችን ወልዳ የሞቱባት ሲሆን ማንዚማን ለፈጣሪ ተስላ የተሰጣት ልጅ ነው። ምንም እንኳ ማንዚማን በመንደሩ እንደ ዝንጆሮና ጉሬላ የሚታይ ልጅ ቢሆንም ለእናቱ የፀሎቷ ምላሽ፡ በረከቷ፡ብቸኛ የስለት ልጅ ነው። ስለዚህ ተከትላው ብትሮጥ፡ስለሱ ብትዘለፍ፡ስለሱ ብትሰደብ ታክቷትና ሰልችቷት አያውቅም።

#ይቀጥላል...

@Ahadu_goh
@Ahadu_goh
1.4K views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ