Get Mystery Box with random crypto!

AHADU

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahadu_goh — AHADU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahadu_goh — AHADU
የሰርጥ አድራሻ: @ahadu_goh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.37K
የሰርጥ መግለጫ

የ 𝚈𝙾𝚄 𝚃𝚄𝙱𝙴 ቻናሌን 𝚂𝚞𝚋𝚜𝚌𝚛𝚒𝚋𝚎 👏 ያድርጉ
👇👇 👇👇
https://www.youtube.com/c/Ahadu
ለማንኛውም አስተያየትዎ - @Ahadu_Commbot

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-10 23:26:18
እስኪ ተመስገን በሉ

እዚ ምድር ላይ እስካለህ አመስጋኝ ለመሆን ሞክር ዛሬ አንተ ያለህበት ቦታ ለሌሎች ህልማቸው ነውና



ᴊᴏɪɴ ᴜs @Ahadu_Goh
@Ahadu_Goh
 
590 viewsedited  20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 17:04:08
በየቀኑ ትለፋለህ...ትለፋለህ...ግን ብዙ የሚያስገርም ለውጥ የለህም አይደል? ስለ ቀርከሀ የምታውቅ ከሆነ ልፋትህን መቼም አታቆምም።

ቀርከሀን ውሀ ብታጠጣው፣ ማዳበሪያ ገዝተህ ብትንከባከበው ወይ አሪፍ የአየር ሁኔታ ውስጥ ብታረገው እንኳን በመጀመሪያዎቹ 5 አመታት ብዙም አያድግም፤ አስገራሚው ነገር 5 አመት ከአንድ ወር ሲሞላው ግን ከ 5 ሜትር በላይ ቁመቱ ይመዘዛል። ለካ 5 ዓመት ሙሉ ለውጡን ያላየነው ረጅም ቁመቱን መሸከም የሚችል ስር መሬት ለመሬት እየዘረጋ ስለነበር ነው። አይታይህም እንጂ ጥረትህ ፅዋውን እየሞላ ነው! የልፋትህ ውጤት ሊከፈልህ ትንሽ እንደቀረህ እያሰብክ ጠንክረህ ተማር! ጠንክረህ ስራ!

ይህ ሀሳብ ለሚያስፈልጋቸው ወዳጆቻችሁ ሁሉ ሼር አድርጉ ቤተሰቦች


ᴊᴏɪɴ ᴜs @Ahadu_Goh
@Ahadu_Goh
 
768 views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 21:36:01
አይምሮህ ውስጥ በሀሳብ የዘራኸውን በገሀዱ አለም በተግባር ታጭደዋለህ፤ ይሄ ሁሉ በድብቁ የአይምሮ ክፍል (Subconscious Mind) ምክንያት ነው። ገብስ የዘራ ገበሬ ገብስ ያጭዳል፤ በስንፍናው ሳይዘራ የቀረ ደግሞ አረም የወረረው ማሳ ታቅፎ ይቀራል። አሁን ይሄንን የአይምሮ ምስጢር እያወቅን ካለማድረግ በላይ ደካማነት የለም። አይምሯችን ውስጥ እችላለው የሚል መንፈስ መዝራት አለብን፣ ከባድ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ብንሆን አይ ይቺንማ በቀላሉ አልፋታለው ማለት አለብን፤ ድብቁ አይምሮ ስራው ደጋጋግመን የነገርነውን በተግባር ገልጦ ማሳየት ነው።


ᴊᴏɪɴ ᴜs @Ahadu_Goh
@Ahadu_Goh
 
185 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 20:34:22
ጠንክረህ መስራትህ ምንም ትርጉም ካልሰጠህ እስር ቤት ውስጥ ነህ! መስራት ስለምትፈልገው፣ መማር ስለምትፈልገው፣ መሆን ማሳካት ስለምትፈልገው አብዝተህ አስብ ምክንያቱም ወደ ፀሀይ ስትዞር ጥላህ ወደኋላ ይሸሻል። ወዳጄ ትርጉም ስለሚሰጥህ ነገር ብቻ አስብ!

ᴊᴏɪɴ ᴜs @Ahadu_Goh
@Ahadu_Goh
835 views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 12:44:06
መንፈስ (Ghost)

የፓራኖርማል ኤክስፐርቶች እንደሚሉት ከሆነ ብዙ የሙት መንፈስ የሌለበት ቦታ የመቃብር ስፍራ ነው ይላሉ ፤ እነሱ እንደሚሉት ከሆነ በማታ አንድ የመቃብር ስፍራ ካሉት የሙት መንፈሶች ይልቅ በምንተኛበት ክፍል ውስጥ ብዙ መንፈሶች አሉ ። የፓራኖርማል ኢንቨስቲጌተሮች እንዳሳወቁት የሙት መንፈሶች (Ghost) ቤት ውስጥ ባዶውን የተቀመጠ ወንበር ላይ መቀመጥ ያዘወትራሉ ምተኙበት ክፍል ውስጥ ባዶ ወንበር ካለ እሱ ላይ ተቀምጠው ያፈጡባቹሃል ፣ በህልማቹ ያቃዧቹሃል ፣ ድምፃቹንም በመንጠቅ ለራሳቸው እስክትነቁ ይጠቀሙበታል ። ድንገት ሻማ ለኩሳቹ የለኮሳቹት ሻማ ሰማያዊ ሆኖ ሚበራ ከሆነ ወይም የሻማው እሳት ያለ ምንም ንፋስ በድንገት ከጠፋ አጠገባቹ መንፈስ አለ ማለት ነው ይላሉ የዘርፉ ተመራማሪዎች ።

ፓራኖርማል ሳይንስ በመላምልቶች እንጂ በእውነታ የተደገፈ አደለም

T.me/Ahadu_Goh
T.me/Ahadu_Goh
982 views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 10:16:13
ለመላው የ ኦርቶዶክስ አማኞች እንኳን ለ ቅድስት ድንግል ማርያም ደብረ ምጥማቅ አደረሳቹ

ግንቦት 21 እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ የተገለጠችበት ቀን ነው።

ጥበቃዋ በረከት ረዴኤቷ አይለየን።

@Ahadu_goh
943 viewsedited  07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 20:08:16
​​ በአሜሪካ ህግ መሰረት አንድ ሰው ከባንክ ብር ተበድሮ መክፈል ካልቻለ ንብረቱ በሙሉ እንዲሸጥ ይደረጋል ፤ ይህም ቁምጣና ሱሪው ሳይቀር ማለት ነው ፡፡ ነገር ግን የፈለገውን ያህል እዳ ቢኖርበት ለሽያጭ የማይቀርብ አንድ ወሳኝ ንብረት አለ ይኸውም የጋብቻ ቀለበት ነው !!!

@Ahadu_goh
1.1K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 09:35:01

1.1K views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 09:12:37

1.5K views06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 17:35:52
ብሪታኒያ ውስጥ ነው፤ አንዲት ሴት አውራ-ጎዳና ላይ እርቃኗን ስትንጎራደድ ትቆዪና መንገድ ዳር ቆመው ተሳፋሪ ከሚጠብቁ ታክሲዎች ወደ አንዱ ዘው ብላ ትገባለች። የገባችበት ታክሲ ቻይናዊ ሹፌርም ግራ በመጋባትና በመገረም ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ በጥያቄ ስሜት መላልሶ ማየት ይጀምራል።

አጅሪት ግን ምንም ያልተፈጠረ በማሥመሰል መሄድ የምትፈልግበትን ተናግራ እንዲንቀሳቀስ በዓይኗ ምልክት ትሰጠዋለች። ቻይናዊው ታክሲ ሹፌር ግን ያልተመለሠለት ጥያቄ ነበርና አሁንም ከእግር እስከራሷ መላልሶ ማየቱን ይቀጥላል።
ይኼኔ ቆንጂት በሷ ብሶ በስጨት እንደማለት እያደራረጋት " ልብስ ያልለበሰች ሴት አይተህ አታውቅም???" ብላ ታፈጥበታለች። ይኼኔ ቻይናዊው ታክሲ ሹፌር እንዲህ በማለት በትህትና መለሠ " ... የኔ እህት... እኔ ግራ ተጋብቼ የማይሽ እርቃንሽን መሆንሽ ገርሞኝ ሳይሆን... ለአገልግሎቴ ልትከፍዪኝ የሚገባኝ ገንዘብ የቱጋ እንዳለሽ ጥያቄ ስለሆነብኝ ነው።"

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
*እየውልህ ወንድሜ በዚህች ዓለም ስትኖር ልክ እንደቻይናዊው ሹፌር ማተኮር ያለብህ ሰለሚመለከትህ ጉዳይ ብቻ ነው። ስለማያገባህ ጉዳይ ስትፈተፍት በመዋልና በማደር ለራስህ የምትጨምረው ነገር የለም። አቅምህ እስከቻለው ለሌሎች መልካም አድርግ የሌሎችን ግላዊ ህይወት ግን ለባለቤቶቹ ተውላቸው።

አሁዱ ነኝ
@Ahadu_goh
1.5K viewsedited  14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ