Get Mystery Box with random crypto!

በየቀኑ ትለፋለህ...ትለፋለህ...ግን ብዙ የሚያስገርም ለውጥ የለህም አይደል? ስለ ቀርከሀ የምታው | AHADU

በየቀኑ ትለፋለህ...ትለፋለህ...ግን ብዙ የሚያስገርም ለውጥ የለህም አይደል? ስለ ቀርከሀ የምታውቅ ከሆነ ልፋትህን መቼም አታቆምም።

ቀርከሀን ውሀ ብታጠጣው፣ ማዳበሪያ ገዝተህ ብትንከባከበው ወይ አሪፍ የአየር ሁኔታ ውስጥ ብታረገው እንኳን በመጀመሪያዎቹ 5 አመታት ብዙም አያድግም፤ አስገራሚው ነገር 5 አመት ከአንድ ወር ሲሞላው ግን ከ 5 ሜትር በላይ ቁመቱ ይመዘዛል። ለካ 5 ዓመት ሙሉ ለውጡን ያላየነው ረጅም ቁመቱን መሸከም የሚችል ስር መሬት ለመሬት እየዘረጋ ስለነበር ነው። አይታይህም እንጂ ጥረትህ ፅዋውን እየሞላ ነው! የልፋትህ ውጤት ሊከፈልህ ትንሽ እንደቀረህ እያሰብክ ጠንክረህ ተማር! ጠንክረህ ስራ!

ይህ ሀሳብ ለሚያስፈልጋቸው ወዳጆቻችሁ ሁሉ ሼር አድርጉ ቤተሰቦች


ᴊᴏɪɴ ᴜs @Ahadu_Goh
@Ahadu_Goh