Get Mystery Box with random crypto!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

የቴሌግራም ቻናል አርማ abaynehkassie — ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie
የቴሌግራም ቻናል አርማ abaynehkassie — ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie
የሰርጥ አድራሻ: @abaynehkassie
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.03K
የሰርጥ መግለጫ

ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እና ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ማናቸውም አሳቦች ሁሉ ዕይታዬን የማቀርብበት መድረክ።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 18:07:04
ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬ አሁን ተፈትቷል።

"በታሰርሁባት ሌሊት አብረውኝ ታስረው ከነበሩት ጋር አስደናቂ የጸሎትና የትምህርት ጊዜ እግዚአብሔር አዘጋጅቶ ጠበቀኝ። እኔም እንደ ዐዲስ ተመገብሁት።" በማለት አጫውቶኛል።

ከታሰርሁበት ድረስ መጥተው፦

፩. አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
፪. አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ከህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
፫. አቡነ ማቴዎስ
፬. አቡነ ዮሴፍ ዘሲዳማ ሀገረ ስብከት
፭. አቡነ ፊልጶስ ዘደቡብ ኦሞ

ከሌሎች በርካታ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር በመኾን ጠይቀውኛልና እግዚአብሔር ይስጥልኝ ብሏል።

ጊዜ ሰጠን ብላችሁ በግል ጥላቻ ምክንያት እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን እየጠቆማችሁ ለማሸማቅቀ የምትሞከሩ አውደልዳዮች እረፉ።
1.4K viewsAbayneh Kassie (ዓባይነህ ካሤ) Tegegne, 15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:43:00 ቅዱስነታቸው ሕክምናቸውን አጠናቅቀው የሚመለሱብት ቀን ተቆርጧል። ጽ/ቤታቸው አካባቢ ረብሻ አለ የሚል ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብዙኀን መገናኛ (ቴሌቪዥን) ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬም ታስረዋል እየተባለ ነው።

ምን እየተካሔደ ነው? በኢትዮጵያ ከምሽቱ ፪፡ ፴ (2፡30) ጀምሮ ይጠብቁን።



2.1K viewsAbayneh Kassie (ዓባይነህ ካሤ) Tegegne, edited  16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 06:57:47 ለሀገሬ ስል ዋጥ

እጅግ በጣም በርካታ ስሕተቶች ይታዩኛል። የሚያዳምጥ በሌለበት መናገሩ ለሀገሬ ጠላቶች ጉልበት መጨመር መስሎ ይሰማኛል። እናም ለሀገር ጥቅም ሲባል ዋጥ አድርጌዋለሁ።

አንዱን ግን አለመናገር አልችልም። ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ የታሠሩ ፋኖዎች በአስቸኳይ ይፈቱ። በሚሳደዱት ላይም የታወጀው ዘመቻ በፍጥነት ይቁም። እነርሱ በሀገር ላይ አያኮርፉም አላኮረፉምም።
2.4K viewsAbayneh Kassie (ዓባይነህ ካሤ) Tegegne, 03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 22:03:03
ቅዱስነታቸው ሕክምናቸውን ተከታትለው ጤንነታቸውም መሻሻል አሳይቷል።

በወርኀ ጳጉሜን በመጀመሪያዋ ዕለት ወደ ቅድስት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰው ይገባሉ። በዚህ የሚደሰት እንጅ የሚከፋ ባይኖር ደስ ይለናል።
2.5K viewsAbayneh Kassie (ዓባይነህ ካሤ) Tegegne, 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:23:32 እነሆ ጽዋዕ ተመልሳለች - ንዑ ተጋብኡ ትላለች።

ነሐሴ ፳፬ የተወዳጆቹ ሦስት ቅዱሳን ዓመታዊ በዓል ይከበራል። ከዲያቆን ዮርዳኖስ ጋር ኾነን እንዘክራቸዋለን። በኢትዮጵያ ፲፩ (11፡00) ሠዓት ሲል በቀጥታ ሥርጭት ያገኙታል።



2.5K viewsAbayneh Kassie (ዓባይነህ ካሤ) Tegegne, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:03:20
ከመላእክት ማኅበር የገባ ዜግነት ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። በምድር በቅሎ ከሰማያዊያኑ ሱራፌል ገብቶ የተቆጠረ ድንቅ ተክል አለን። አባ ተክለ ሃይማኖት የሚባል።

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል ብሎ የለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ።

እንኳን ለጻድቁ በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ!!!
2.6K viewsAbayneh Kassie (ዓባይነህ ካሤ) Tegegne, 04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 03:30:21 በኢትዮጵያ በጭራሽ ተስፋ አልቆርጥም!


"ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራ ሥራ ቢጎድል፣ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፣ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፣ ላሞችም በጋጡ ባይገኙ፣ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፣ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሴት አደርጋለሁ" እንዳለ ዕንባቆም ነቢይ።
ዕን ፫፡ ፲፯።


አይዞን የሀገሬ ልጆች!!!
2.4K viewsAbayneh Kassie (ዓባይነህ ካሤ) Tegegne, 00:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 06:14:59 ከደጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል እኩያን ፖለቲከኞች ዘወር ቢሉለት ሰላሙን ለማጽናት የሃይማኖት አባቶች እና ሽማግሌዎች ይበቁታል።


በእርግጠኝነት በሕዝቡ መካከል ጠብ የለም። ሕፃናቱንማ አቀላቅለን ብንለቅቃቸው ሰከንድም አይባክንባቸው።
2.7K viewsAbayneh Kassie (ዓባይነህ ካሤ) Tegegne, 03:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 05:28:36
ጋኔን ይመስል ለቀቅሁ ማለት ምንድን ነው?
2.9K viewsAbayneh Kassie (ዓባይነህ ካሤ) Tegegne, 02:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:28:01
በዚህ ዓለም የተመቸ ለት እግዚአብሔርን ረስቶ ቅዱሳኑን ትቶ እኔ እኔ ማለት ይበዛል። የጨነቀ ለት ደግሞ እግዚኦ ድረስልን መጯጯህ ያይላል።


አበውም እንዲህ ያለውን መርመጥመጥ ታምሞ የተነሣ እግዜርን ረሳ ይሉታል።


ሲገፉት ሲያስሩት ሲያሳድዱት እንዳልባጁ አሁን ጭንቅ ሲመጣ ፋኖ ፋኖ ማለት ጀመሩ። እግዚአብሔር በተመቸ ጊዜ ለምን ረሳችሁኝ ብሎ እንደማይጨክነው ሁሉ ፋኖ ሀገሩን እንጅ በደሉን አይቆጥርም።


ግን ግን የታሰሩት ሁሉ በአስቸኳይ መፈታት አለባቸው። የሚሳደዱትም በክብር እንዲመለሱ መኾን ይገባዋል። አለበለዚያ . . . ተከፍሎ የማያልቅ መከራ ይኾናል።
3.0K viewsAbayneh Kassie (ዓባይነህ ካሤ) Tegegne, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ