Get Mystery Box with random crypto!

ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬ አሁን ተፈትቷል። 'በታሰርሁባት ሌሊት አብረውኝ ታስረው ከነበሩት ጋ | ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬ አሁን ተፈትቷል።

"በታሰርሁባት ሌሊት አብረውኝ ታስረው ከነበሩት ጋር አስደናቂ የጸሎትና የትምህርት ጊዜ እግዚአብሔር አዘጋጅቶ ጠበቀኝ። እኔም እንደ ዐዲስ ተመገብሁት።" በማለት አጫውቶኛል።

ከታሰርሁበት ድረስ መጥተው፦

፩. አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
፪. አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ከህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
፫. አቡነ ማቴዎስ
፬. አቡነ ዮሴፍ ዘሲዳማ ሀገረ ስብከት
፭. አቡነ ፊልጶስ ዘደቡብ ኦሞ

ከሌሎች በርካታ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር በመኾን ጠይቀውኛልና እግዚአብሔር ይስጥልኝ ብሏል።

ጊዜ ሰጠን ብላችሁ በግል ጥላቻ ምክንያት እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን እየጠቆማችሁ ለማሸማቅቀ የምትሞከሩ አውደልዳዮች እረፉ።