Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ ዓለም የተመቸ ለት እግዚአብሔርን ረስቶ ቅዱሳኑን ትቶ እኔ እኔ ማለት ይበዛል። የጨነቀ ለት | ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

በዚህ ዓለም የተመቸ ለት እግዚአብሔርን ረስቶ ቅዱሳኑን ትቶ እኔ እኔ ማለት ይበዛል። የጨነቀ ለት ደግሞ እግዚኦ ድረስልን መጯጯህ ያይላል።


አበውም እንዲህ ያለውን መርመጥመጥ ታምሞ የተነሣ እግዜርን ረሳ ይሉታል።


ሲገፉት ሲያስሩት ሲያሳድዱት እንዳልባጁ አሁን ጭንቅ ሲመጣ ፋኖ ፋኖ ማለት ጀመሩ። እግዚአብሔር በተመቸ ጊዜ ለምን ረሳችሁኝ ብሎ እንደማይጨክነው ሁሉ ፋኖ ሀገሩን እንጅ በደሉን አይቆጥርም።


ግን ግን የታሰሩት ሁሉ በአስቸኳይ መፈታት አለባቸው። የሚሳደዱትም በክብር እንዲመለሱ መኾን ይገባዋል። አለበለዚያ . . . ተከፍሎ የማያልቅ መከራ ይኾናል።