Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የቴሌግራም ቻናል አርማ zephilosophy — ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
የሰርጥ አድራሻ: @zephilosophy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.37K
የሰርጥ መግለጫ

ፍልስፍና  እውነትን በመፈለግ- ሀሳዊ እምነቶችን በማጋለጥ እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል።
በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤  ሀይሞኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-10 20:37:02 ኦሾ እንዲህ ይላል:-

ፖለቲከኛ የስነልቦናና የመንፈስ ታማሚ ነው። በአብዛኛው ፖለቲከኞች ጤናማ ተክለ ቁመና ይኖራቸዋል። አካላቸው እንከን አልባ ሲሆን ዋናው ሸክም የሚያርፍበት አእምሮአቸው ግን ህመምተኛ ነው። አእምሮአዊ ህመማቸው ሲበዛ ደሞ የመንፈስ ታማሚ ይሆናሉ። የህመሙ አይነት የዝቅተኝነት ( የበታችነት) ስሜት ወይም Inferiority complex የሚባለው አይነት ነው።

የስልጣን ጥማት ያለበት ማንም ሰው የበታችበት ስሜት ተጠቂ ነው። በውስጡ የሚሰማው ዋጋ ቢስነትና ከሌሎች ማነስ ብቻ ይሆናል። በተለያዩ መንገዶች ከሌሎች እናንሳለን። ይህ ማለት ግን የበታችነት ስሜት ሊሰማን የግድ ነው ማለት አይደለም። ፖለቲካኛ ግን የበታችነት ደዌ ተጠቂ ነው። ራሱን ምጡቅ ከሆኑ የሰው ልጆች ጋር ሊያነጻጽር መሞከሩ የበታችነት እንዲሰማው ያደርገዋል። ራሳችሁን ከአንስታይንና ሲግመንድ ፍሩድ ጋር የምታፎካክሩ ከሆነ ዋጋ ቢስነትና ትንሽነት ሊሰማችሁ ይችላል።
ይህ የዋጋቢስነት ስሜት በሁለት መንገዶች ይወገዳል። አንዱ ሀይማኖት ሲሆን ሌላው ደግሞ ፖለቲካ ነው።
ፔለቲካ ይህን ደዌ ይደብቀዋል እንጂ አያጠፋውም። የህመሙ ተጠቂ በዚህ የበታችነት ስሜት የሚሰቃየው ሰው ፕሬዚዳንት ሊሆን ይችላል። የመሪነትን ወንበር መያዝ በውስጣዊ ማንነታችሁ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?
ከሞራርጂ ዴሳይ ጋር ያጋጨኝ ይኸው ጉዳይ ነበር።በህንድ ከሚከበረው አመታዊ የሀይማኖቶች የጋራ ጉባኤ አስቀድሞ የጃይና መነኩሴው አቻርያ ቱልሲ ከጋበዛቸው ሀያ እንግዶች መካከል እኔና ዴሳይ ነበርንበት። ወቅቱ 1960 ነበር ። ተጋባዦች በቀጣይ የሚሳተፉትን ሀምሳ ሺ የሀይማኖት ተከታዮች በተመለከተ ለመወያየት ነበር ለቅድመ ትውውቅ የተጋበዝነው። ሆኖም ግን ከመጀመርያው ነበር ችግር የተፈጠረው።
የችግሩ መነሻ ደግሞ ጋባዣችን የሆነው ቱልሲ ከፍ ካለው መቀመጫ ላይ ሲቀመጥ ሀያችን ደግሞ መሬት ላይ ተቀመጥን። አቀማመጡን የተቃወመው ብቸኛ ሰው ሞራርጂ ዴሳይ ነበር። ከሀያዎቻችን መካከል ዴሳይ ብቸኛው ፖለቲከኛ ሲሆን ሌሎቻችን ከተለያዩ መስኮች ነበር የመጣነው።
አጠገቤ የተቀመጠው ዴሳይ ተቃውሞውን እንዲህ ሲል ለጋባዣችን አቻርያ ቱልሲ አሰማ።
"...እኛ እንግዶቹ መሬት ላይ ተቀምጠን አንተ ከፍ ያለውን ወንበር መያዝህ ተገቢ አይደለም። ስብሰባ እየመራህ ቢሆን ችግር የለውም። ነገር ግን ከሀያችን ከፍ ብለህ መቀመጥህ ምን አይነት ስነ ስርአት ነው?"

መነኩሴው ተደናገጡ። ከወንበራቸው ባይወርዱም በሀፍረት ተሸማቀዋል። ፖለቲከኛው ሞራርጂ ዴሳይ ላነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጠው የአቻርያ ቱልሲ ምክትል ነበር። የመነኩሴው አቀማመጥ ለውይይቱ አመቺነት ተብሎ መሆኑን በመጥቀስ ማንንም ዝቅ አድርጎ ለማየት አለመደረጉን ተናገረ።
ሞራርጂ ግን በቀላሉ የሚያቆም አልሆነም። "እዚህ ለተገኘነው በሙሉ አለቃችን አንተ አይደለህም። ለምን ከኛ ከፍ ብለህ ተቀመጥክ? ድርጊትህ ስርአት አልባ አይሆንም? በማለት ሲጠይቅ መነኩሴው ብቻ ሳይሆኑ ሁላችንም ተረበሽን።

" ከይቅርታ ጋር- እኔ ልመልስልህ?" በማለት ዴሳይን ጠየኩት።
"መልሱን ማወቅ እፈልጋለው- መልስልኝ" በማለት ሲፈቅድልኝ መናገር ጀመርኩ።

"በመጀመርያ እዚህ ብቻህን አይደለም የመጣኸው። ከአንተ ውጪ 19 እንግዶች ተገኝተናል። አንተን ብቸኛው ጠያቂ ያደረገህ ማነው?" በማለት ጠየኩትና ወደሌሎቹ ተጋባዦች ዞሬ "የመነኩሴው አቀማመጥ ላይ ተቃውሞ ያለው ሌላ ሰው ካለ እስኪ እጃችሁን አሳዩኝ" ስል ጠየኳቸው። አንዳቸውም አላሳዩኝም።

ከዛ ወደ ዴሳይ ዞሬ "በመነኩሴው አቀማመጥ ስሜቱ የተነካው ብቸኛ ሰው አንተ ነህ። በአስቸጋሪ የበታችነት ስሜት አረንቋ ውስጥ መሆንህን ያሳብቅብሀል።እንደ ዶ/ር ካታሪ ያሉ ምሁራን ፈጽሞ ቁብ ያልሰጡት ነገር አንተን ብቻ ነው ያስቀየመህ።
ከአቻርያ ቱልሲ በላይ ኮርኒሱ ላይ ምትኖረው ሸረሪት ትታይሀለች? ለመሆኑ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ መሆን የበላይ የሚያደርግ ይመስልሀል? እንግዲህ ስሜትህን የነካው ይሄ ነው። የህንድ የፋይናንስ ሚኒስቴር መሆን ያልፈወሰው ደዌ ውስጥህ አለ። አንድ ቀን የሀገራችን ጠ/ሚንስትር ለመሆን መፈለግህ አይቀርም" አልኩት።

በንግግሬ ተናደደ።"እብድ ነህ እያልከኝ ነው?" ሲል በቁጣ ጠየቀኝ

"አዎ" ስል መለስኩለት። "እነዚህ 18 ተሰብሳቢዎች ቅድም እጃቸውን አለማውጣታቸው ይህንኑ ያረጋግጥልሀል። የመነኩሴው ከፍ ብሎ መቀመጥ የረበሸው አንተን ብቻ ነው" ስል መለስኩለት።
"ለመሆኑመነኩሴው ቀድሞ ወንበሩ ላይ አስቀምጦህ ቢሆን ኖሮ መሬት ላይ ለተቀመጥነው ሌሎቻችን ክብር ስትል ተመሳሳይ ጥያቄ ታነሳ ነበር?" በማለት ጠየኩት።

"ፈጽሞ አስቤው አላውቅም ነበር። በርካታ ስብሰባዎች ስመራ ከፍ ያለ መድረክ ላይ ነው ምቀመጠው። ማንም ተሰብሳቢ ጥያቄውን አንስቶ አያውቅም።" በማለት መለሰልኝ።

"ጥያቄህ ለምን አቻርያ ቱልሲ ከፍ ያለ ቦታ ተቀመጠ የሚል አደለም። ያንተ ጥያቄ ለምን ከቱልሲ በታች ተቀመጥኩ የሚል ነው። የራስህን ህመም ወደ ሌላ ሰው አታጋባ።
" ምናልባት አንተ ብቻ ሳትሆን አቻርያ ቱልሲም የህመሙ ተጠቂ ይመስለኛል። በመነኩሴው ቦታ ብሆን ኖሮ መጀመርያ መድረኩ ላይ አልቀመጥም ነበር። ብቀመጥም ደግሞ ጥያቄ ስታነሳ ይቅርታ ጠይቄ እወርድ ነበር። ሆኖም ግን እንደምታየው አሁንም ከቦታው አልወረደም። ለጥያቄህ መልስ መስጠት ያቃተው ይመስላል። ከመነኩሴው ይልቅ እኔን ያሳሰበኝ የአንተ ሁኔታ ነው። በስልጣን ሚዛን እንዲሁም በበላይነትና በበታችነት የተሞላ ጭንቅላት ያላቸው ፖለቲከኞች ናቸው ።" በማለት ምላሽ ሰጠሁት።
በወቅቱ ዴሳይ ተናደደ። ላለፉት ሀያ አምስት አመታትም ቂም ያዘብኝ።


@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.6K views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 05:43:22 .... ካለፈው የቀጠለ

በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ያለን ነገር ወስደህ ለራስህ ማዳበሪያ መጠቀም ግን ትችላለህ፡፡ ወይም ደግሞ በቆሻሻ መጣያው ውስጥ በትግል መኖር ትችላለህ፡፡ ያለህ ምርጫ ይህ ነው፡፡ በስሜት ህዋሳትህ የተገነዘብከው ሁሉ ወደ ውስጥህ ስለሚገባ የምትቀበለውን ነገር በተመለከተ መምረጥ ባትችልም፣ የትኛውን እንደምትጠቀምና የትኛውን እንደማትጠቀም የማስተዋል ኃይል ግን አለህ፡፡ ራስህን በመመልከት ሕይወትህ ምን ያህሉ አስገዳጅ፣ ምን ያህሉ ደግሞ በማወቅ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ተመልከት፡፡ አብዛኛው ክፍል አስገዳጅ እንደሆነ ታያለህ፡፡ በአስገዳጅነት የተከሰትክ ከሆነ፣ ራስህ እንድትሆን በፈለግከው መንገድ አይደለህም ማለት ነው፡፡ በሕይወትህ ያለብህ አንድ ችግር፣ ሕይወት ሊሆን ይገባዋል ብለህ በምታስበው መንገድ የሚሆን አለመሆኑ ነው፡፡ በፈጣሪ የምታምን ከሆነ፣ አንድ ነገር በአንተ መንገድ ካልሄደ፣ በእርሱ መንገድ ሄዷል ማለት ነው። በፈጣሪ መንገድ የሄደ በመሆኑ ደስ ሊልህ ይገባል፡፡ ያ ግን እውነታ አይደለም፡፡ ችግሩ ዓለም በአንተ መንገድ አለመሄዱ ሳይሆን አንተ በራስህ መንገድ አለመሄድህ ነው።

በዓለም ላይ ማንም በአንተ መንገድ አይከሰትም፡፡ በዙሪያህ ያለ ማንኛውም ሰው መቶ በመቶ በአንተ መንገድ አይመጣም፡፡ አንተ ግን በራስህ መንገድ መሆን አለብህ፡፡ በራስህ መንገድ የማትሆን ከሆነ ግን አሳዛኝ ትሆናለህ፡፡ ሰው የመሆን አሳዛኝ ነገር ይህ ነው፡፡ ዓለም በአንተ መንገድ አለመሆኗ ችግር አይደለም፣ ችግሩ አንተ በራስህ መንገድ አለመሆንህ ነው፡፡ ውስጣዊ ነገሮችህን ካላስተካከልክ፣ በአጋጣሚ ለመኖር እየሞከርክ ነው ማለት ነው፡፡ ከአንድ ነገር ነፃ መሆንና አንድን ነገር አለማወቅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ የዓለምን መንገዶች ካላወቅክ፣ ዛሬ ወይም ነገ ልትጋጭ ትችላለህ፡፡ የዓለምን ተንኮለኛ  መንገዶች የምታውቅ ከሆነ ግን ወደዚህ ውስጥ አትገባም፡፡ ስለዚህ ስቃይ በማወቅ የሚመጣ አይደለም፡፡ ማንም ሰው አውቆ ራሱ ላይ ስቃይ አይፈጥርም፡፡ በሆነ መንገድ እየተሰቃየህ ከሆነ፣ ያ እየተሰቃየህበት ያለው ክፍል አያውቅም ማለት ነው፡፡ የተለያዩ ደረጃዎች ያሉት ስቃይ እየተከሰተ ከሆነ፣ በውስጥህ የተለያየ ደረጃ ያለው አለማወቅ አለ ማለት ነው፡፡

በውስጥህ ንቁ የሆነው የትኛውንም ነገር በምትፈልገው መንገድ ትጠብቀዋለህ፡፡ የማይታወቀውን የትኛውንም ነገር ደግሞ በምትፈልገው መንገድ ልትጠብቀው አትችልም፡፡ ስለዚህ በሕይወትህ ልታደርገው የሚያስፈልግህ ነገር ቢኖር ራስህን በበለጠ ሁኔታ ንቁ ማድረግ ነው፡፡ ሁሉም ነገር ሙሉ በሙሉ ንቁ እንዲሆን ጥረት የምታደርግ ከሆነ፣ አንተነትህ መቶ በመቶ በምትፈልገው መንገድ ይሆናል፡፡ ይህ አንድ ሽራፊ ሕይወት ልክ አንተ በምትፈልገው መንገድ ይሆናል፡፡ ያ በሚሆንበት ጊዜ ያለጥርጥር ራስህን እጅግ ደስተኛ ሰው እንደምታደርግ ጥያቄ የለውም፡፡

ምንጭ ፦ የህይወት ኬሚስትሪ (ሳድጉሩ)
ትርጉም ፦ ሀኒም ኤልያስ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.2K views02:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 05:42:44 አንድ ጊዜ አንድ በሬና አንዲት ወፍ መስክ ላይ እየተመገቡ ነበር። በሬው ሳር እየጋጠ ነበር፤ ወፏ ደግሞ ከበሬው አካል ላይ ነፍሳት እየለቀመች ነበር፡፡ በመስኩ ዳር የተተከለ አንድ ግዙፍ ዛፍ ነበር፤ ወፏ ዛፉን ወደ ላይ ተመለከተችና ጮክ ብላ “ይገርማል፣ እዚህ ዛፍ ጫፍ ላይ መውጣት የምችልበት ጊዜ ነበር፡፡ አሁን ግን የታችኛው ቅርንጫፍ ላይ እንኳን ለመውጣት ክንፎቼ በቂ ጥንካሬ የላቸውም፡፡” አለች፡፡ በሬውም “ምንም ችግር የለም፤ ዛፉ ጫፍ ላይ መውጣት የምትፈልጊ ከሆነ፣ በየቀኑ ከእኔ እበት የተወሰነ ውሰጂና ብይ፣ በሁለት ሳምንት ውስጥ ዛፉ ጫፍ ድረስ መውጣት ትችያለሽ፡፡” አላት፡፡ ወፏ እያመነታች ያላትን ማድረግ ጀመረች፡፡ ከዚያ በመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያው ቅርንጫፍ ላይ ወጣች፤ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ የዛፉ ጫፍ ላይ መውጣት ቻለች፡፡ ከዚያ የዛፉ የመጨረሻ ቅርንጫፍ ላይ ተቀመጠችና በምታየው ትዕይንት መደሰት ጀመረች፡፡ በሚወዛወዝ ወንበር ላይ ተቀምጦ የነበረ አንድ ገበሬ ወፍራሟ ወፍ ትልቁ ዛፍ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ሲመለከት ጠመንጃውን አንስቶ ወፏ ላይ ተኩሶ ጣላት፡፡ ከዚህ ታሪክ የምናገኘው ትምህርት ብዙ ጊዜ የማይረባ ሰውም ጫፍ ላይ ሊያደርስህ ይችላል፤ እዚያ እንድትቆይ ሊያደርግህ ግን አይችልም የሚል ነው፡፡

አንተም በብዙ መንገዶች ራስህን በማይረባ ነገር ደስታ ውስጥ ለማስገባት ትሞክራለህ፡፡ ብዙ ጊዜም እዚያ ደርሰሃል ግን መቆየት አልቻልክም፡፡ ይህንን ጊዜያዊ ደስታ በውሃ ዳር በመሮጥ፣ በመደነስ፣ በመዝፈን፣ አልኮል በመጠጣት፣ እጽ በመውሰድ፣ ብዙ ነገሮችን በማድረግ ልታገኘው ትችላለህ፡፡ ይህ ግን ወደ ደስተኝነት የሚወስድህ ለትንሽ ጊዜ ነው፡፡ ደስታ ውስጥ እንድትቆይ አያደርግህም፡፡ እዚያ ውስጥ ለመቆየት ባልቻልክ መጠን፣ በሕይወት የበለጠ ተስፋ የምትቆርጥ ትሆናለህ፡፡ ደስተኝነትን ለመመልከት ብዙ መንገዶች አሉ።

ለምሳሌ አሁን ደስታህን አጥተሃል እንበል፣ ደስታህን ካጣህ ሰላምህንም ታጣለህ፡፡ ያ ሲሆን በመጀመሪያ ወደ ቤትህ ሄደህ ሚስትህ ላይ፣ ልጅህ ላይ፣ እዚያ ያገኘኸው የሆነ ሰው ላይ ትጮሃለህ፡፡ የሚቀጥለው ቀን ጠዋት ላይ ከቀጠለ፣ ከጎረቤት ጋር ጸብ ትጀምራለህ። ከዚያም ከቀጠለ፣ ወደ ቢሮህ ስትሄድ ከአለቃህ ጋር ትጣላለህ። በሚስትህና በልጆችህ ላይ ስትጮህ የተለመደ ነው ብለው ያስባሉ፤ ከባድ ሁኔታ ውስጥ የሚያስገባህ ቦታ ላይ ስትጮህ ግን የህክምና እርዳታ እንደሚያስፈልግህ ያስባሉ፡፡ ስለዚህ ወደ ህክምና ይወስዱሃል፡፡ ዶክተሩ በመጀመሪያ ምን እንደሆንክ ሊያናግርህ ይሞክራል፤ የማትናገር ከሆነ የመጨረሻው ነገር የሚዋጥ ኪኒን መስጠት ነው፡፡ ኪኒን ደግሞ መጠነኛ ኬሚካል ነው፡፡ ያንን ኪኒን መውሰድ ስትጀምር ለጥቂት ጊዜያት ሰላማዊ ትሆናለህ፡፡ ለጥቂት ጊዜያትም ቢሆን ይሰራል፤ ይህ ማለት ሁሉም የሰው ልጆች ተሞክሮ በውስጡ ኬሚካላዊ መሰረት አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሰላማዊና ደስተኛ መሆን ለአንተ ተፈጥሯዊ የሚሆኑበት በውስጥህ ትክክለኛውን ኬሚስትሪ እንዴት መፍጠር እንደምትችል እንነጋገራለን፡፡ ይህ ከውጪ የምታገኘው ሳይሆን በውስጥህ ያለ ነው፡፡

ዛሬ በብዙ መንገድ ዓለም ለእኛ የተሻለ መንገድ እንድትሆን እንሰራለን፤ ስለ ራሳችን ግን ምንም አንሰራም፡፡ ውጪያዊ ሁኔታዎችን በምንፈልገው መንገድ ለመፍጠር በጣም እንጥራለን፣ ውስጣዊ ሁኔታዎቻችን ግን በምንፈልገው መንገድ አይደሉም፡፡ እኛ ተቀምጠናል፣ ውጪ ደግሞ የምንፈልገው አይነት የአየር ሁኔታ አለ፤ ውስጣዊ ሁኔታችን ግን ጥሩ አይደለም፡፡ ይህ አይጠቅምም፡፡ ምክንያቱም የትም ቦታ ሁን፣ ቤተ መንግስትም ተቀመጥ ወይም መንግስተ ሰማያት፣ ውስጣዊ ሁኔታህ ጥሩ ካልሆነ፣ ምንም ዋጋ የለውም፡፡

በዚህች ፕላኔት ላይ የሚከሰተው የሰው ልጆች ችግር ሁሉ ማምረቻ ቦታው ሌላ ሳይሆን አእምሮህ ውስጥ ነው፡፡ ይህ አእምሮ ወደ መለኮት ለመድረስ መሰላል መሆን ሲገባው፣ የደስታ ምንጭ መሆን ሲገባው፣ ለብዙ ሰዎች የድብርት፣ የጭንቀትና የውጥረት ምንጭ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም እንዴት እንደምትይዘው ባለማወቅህ ነው፡፡ በሰው ልጆች ውስጥ የሰው አእምሮ የተሳሳተ ሆኗል፡፡ አእምሮ የፈለግከውን ነገር ልትሰራበት የምትችልበት ተአምር ነው፡፡ አሁን ከፈለግክ በዚ አእምሮህ ራስህን ፍጹም ደስተኛ ማድረግ ትችላለህ፡፡ በዚሁ አእምሮ እራስህን አሁኑኑ እጅግ የተከፋህና የጠፋህ ማድረግም ትችላለህ።
ፈቃደኛ ከሆንክ ሁለቱም ይቻላል፡፡

አእምሯችን የተሳሳተ የሚሆነው የዚህን አካል፣ የዚህን አእምሮ ተፈጥሮ ሳንረዳ እንዲሁ በአጋጣሚ ለመኖር ስለምንሞክር ነው:: ሁሉም ነገር ጥሩ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን፤ ለብዙ ሺህ አመታት “አትጨነቅ ፈጣሪ ሁሉን ያደርግልሃል፣ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል” እየተባለ ሲነገርህ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ዓለምን ተመልከት፤ ሰዎች እያለፉባቸው ያሉትን ነገሮች ተመልከት፡፡ በውስጥህ ያለውን ሕይወት፣ ምን ያህል ደስተኛ እንደ ሆንክ፣ ምን ያህል ሰላማዊ እንደ ሆንክ የሚወሰነው በተረዳህበትና ልትይዘው በቻልከው መጠን ነው:: እስከምን ድረስ የመያዝ አቅም አለህ? ሕይወትን የምታውቀው እስከዚያ መያዝ እስከ ቻልክበት አቅም እስከዚያ ማወቅ እስከ ቻልክበት ጥልቀት ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ አእምሮን የምንይዝበትን መንገድ እንመልከት፤

የአእምሮ ተፈጥሮ በአምስቱ የስሜት ህዋሳት የምናገኛቸውን ነገሮች ሁሉ መሰብሰብ ነው፡፡ በአእምሮህ ውስጥ የሰበሰብካቸው አብዛኞቹ ነገሮች ባለማወቅ የገቡ ናቸው፡፡ በሕይወትህ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ የመተኛትና የመንቃት ቅጽበት ከአምስቱ የስሜት ህዋሳት ግንዛቤ ጋር የተነካካ ስለሆነ አእምሮ ውስጥ ተመዝግቧል፡፡ የሰበሰብከው እያንዳንዱ ድምጽ፣ እያንዳንዱ ሽታ፣ እያንዳንዱ ዳሰሳ፣ እያንዳንዱ እይታ አእምሮህ ውስጥ አለ፡፡ አንዳንዶቹን አውጥተህ ልትጠቀምባቸው ችለሃል፡፡ አብዛኞቹን ግን ማውጣት አልቻልክም፡፡ ግን እየሰራ ነው፤ እነዚህ ግንዛቤዎች በተለያዩ መንገዶች በአንተ ላይ ተጽዕኖ እየፈጠሩ ነው፡፡ ከእነዚህ ወደ አእምሮህ ውስጥ ከሚገቡ ግንዛቤዎች የትኛውን ማስገባት፣ የትኛውን ማስወጣት እንዳለብህ መለየት አትችልም፡፡ በመንገድህ የመጣ ማንኛውም ሰው በአእምሮህ ውስጥ የሆነ ነገር አስገብቶ ይሄዳል፡፡ ልታቆመው አትችልም፡፡ “ይህንን ሰው አልወደውም” ብትልም እንኳን ከእርሱ የምትቀበለውን ማስቀረት አትችልም፡፡ እንዲያውም ከዚያ ሰው የምትወስደው ከሌላ ሰው ከምትወስደው የበለጠ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ በአንድ መንገድ ካየኸው አእምሮህ የማህበረሰቡ ቆሻሻ መጣያ ነው፡፡

ምንጭ ፦ የህይወት ኬሚስትሪ (ሳድጉሩ)
ትርጉም ፦ ሀኒም ኤልያስ

          ይቀጥላል

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.2K views02:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 14:46:28 ሳይንስ ፤ ፍልስፍናና ስነ-ፅሁፍ

በሕዋ (Universe) ውስጥ አእምሮ በዕውቀትና ክህሎቱ ሰፍሮ የማይጨርሰውና መርምሮ የማይደርሰው ብዙ ተአምር አለ። እንደ ግል እይታዬ ይህ ያልተደረሰበት ተአምር ለሳይንስ፤ ለፍልስፍናና ለሥነ-ጽሑፍ አለፍ ሲልም ለእምነት ...የተተወ የተንጣለለ የኀሰሳ ሜዳና የቀና ዕድል ነው። እምነት ያው “ማመን” ስለሆነና አንጻራዊነት ስለሚጫነው እዚሁ ጋር እንተወው

ሳይንስ ለመከራው ማብቂያ ፣ለፍዳው መገላገያ የለውም። በቀን ያስጨንቃል፣ በሌት ያባንናል። ዓመታት ፈጅቶ የተደረሰበት መደምደሚያ እንኳ በቋፍ እንደተቀመጠ ብርጭቆ ነው። በሌላ መደምደሚያ “ተሳስተሃል” ይባላል — Disprove ይደረጋል። የአመታት እውነት በአንድ ሌት ውሸት ሆኖ ሊያድር ይችላል። ሳይንስ ነጻነት አይሰጥም። ሳይንስ የምርምር ንድፍና ሰርቶ ማሳያ ከሚሆኑ ፈጠራዎች ባለፈ “ቢሆንስ?” ለተባለና ላልተጨበጠ ምናብ የተተወ እንግዳ መቀበያ የለውም በእርግጥ አስተውሎት (observation) በሳይንስ ቤት ያለው ቦታ የማይናቅ ነው።

ጠልለው የተቀመጡ፤ ተመርምረው የተሰደሩ  ውጤቶቹን ባየሁ ቁጥር ለተመራማሪዎቹ አዝንላቸዋለሁ። ወዲህም የሰው አእምሮ አጀብ እላለሁ። ከሳይንስ ሁሉ ጊዜና ቦታን ጠቅልሎ የያዘው ሕዋ ላይ የሚደረግ ምርምር ደግሞ በእጅጉ ያባብለኛል። በአንድ ጫፍ የሰው ልጅ አፉን በመዳፍ ሸፍኖ ለሐሜት በሚተጋበት ምድር ላይ፤ በሌላው ጫፍ ሮኬት እንደፈረስ ጠምዶ ተመርምረው የተሰደሩ ጨረቃን ይረግጣል።

ፍልስፍና በመጠኑ መለስ ያለ የሕይወት ምርመራና፤ የትርጉም ኀሰሳ ነው። ፍልስፍና አንዳንድ የሀገሬ ሰው እንደሚያስበው የብሶተኛ ሮሮ ወይም ጥራዝ- ነጠቅ ምክንያታዊነት አይደለም። ምድር የምትመራው በሳይንስ ሳይሆን በፍልስፍና ነው። ርዕዮተ-ዓለሞች የሚረቅቁት፤ የመንግሥት ስርዓቶች የሚዋቀሩት፣ ግለሰባዊው ሰው የኑሮ ምርጫውን የሚዘረጋው ወደደም አልወደደም በኖረበት ማኀበራዊ እሴት ለስልሶና፤ በአፈንጋጭ የሕይወት መጠይቆቹ ሻክሮ ነው።

ሳይንስ ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ቢሆንም ለፍልስፍና ወድቆ ይገዛል። ረባም አልረባም የጊዜው አየር ላይ ከሚነፍሰው ፕሮፖጋንዳ ሥር ያሸበሽባል። ዲሞክራት ነን የሚሉ ሀገራት ሕዝቡን ያለ እውቅናው ጠምዝዞ ለመቆጣጠር፤ መውጪያና መግቢያውን ለመለየት፤ ተፈጥሮን በሰው ልጅ ጡንቻ ሥር ለማሰገድ ያውሉታል። ከሞኝ ሀገራት ደጅ ሞፈር ለመቁረጥ፣ ጥሬ ዕቃ ለመበዝበዝ፣ በምርትና አምራችነት ስም ራሳቸውን ለማበልጸግ፣ እንዲሁም ለሰው ተስማሚ የሆኑ አማራጭ ዓለማትን ለመፈለግ ያውሉታል።

አምባገነን ሀገራት ለጦር ኃይላቸው መዘመን፣ ኒውክለር ለማብላላት፣ ጸጥ ረጭ አድርገው ለመግዛት ከዲስኩርና ከሌሎች ስልታዊ ማደንዘዣዎች ጎን ለጎን ሳይንስን ይጠቀሙታል። ቀን በቀንም ቴክኖሎጂው እየዘመነ ኑሮ እየቀለለ እንዳለ ሁሉ፣ ለመጠፋፋትም እንዲሁ አቋራጭ ስልቶች እዚህም እዚያም ብቅ ማለት ጀምረዋል።

ሦስተኛውና “ያ” ክፍት ቦታ የተተወለት ዘርፍ ሥነ-ጽሑፍ ነው። በተለይ ልብ-ወለድ (Fictional) ሥነ-ጽሑፍ ከሁለቱ በተሻለ መልኩ ዕድሉ የቀና ነው። ለምን? ሥነ-ጽሑፍ ምናብን አቅፎ ይቀበላል። እውነትና ውሸትን ቢቀይጥ ከልካይ የለውም። እንዲሁም ነጻነት ከሌለው ሳይንስና፤ ደረቅ ከሆነው የትርጉም ሐቲት አውጥቶ ቢፈለጉ በማይገኙ ሰዎችና እንዳሻው በፈጠረው ዓለም ውስጥ
ሕይወትን ይፈትሻል።

ከሀገር ያጣ ሞት
ድርሰት - ሄኖክ በቀለ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.5K viewsedited  11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 14:39:46
“ሀገር ያጣ ሞት” ራሱ እንደሚhው “ከቅኝት ትዝታ፣ ከስሜትም ኀዘን” የሚገንንበት ፤ ሀዘኑ አንባቢን የሚወርስ፣ እንደ ዐፈር ግድግዳ የሚንድ፤ የሚያፈራርስ፤ መሪር ሂዩመሩ hሣቅ የተገለጠ ጥርስ በመሸማቀቅ አግጥጦ የሚያስቀር፣ ለፈገግታ የተዛና የጉንጭ ቆዳን በኀፍረት የሚሸበሽብ፤ የገዛ ስጋ ወደሙን ከአንባቢ የሚያዋሕድ ኃያል ድርሰት ነው፡፡"

@Zephilosophy
1.1K viewsedited  11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 21:58:43 እውነትን ስቀሏት!!

ስቀሏት! ስቀሏት! እውነትን ስቀሏት!
እሷ ስለሆነች የሰው ልጆች ጠላት
ምድር አትፈልግም የሀቅን ውለታ
ስቀሏት! ስቀሏት! በርባን ግን ይፈታ !
ካለችበት አገር እጇን የሚያስይዘን
ማነው አሳልፎ ስሞ የሚሰጠን?
ስቀሏት! ስቀሏት!
እውነትን ስቀሏት!!
በርባንን ፍቱልን
መቃብር ተከፍቶ ሂትለር ይነሳልን
አቦይ ሞሶሎኒን ሂዱ ቀስቅሱልን
ቦካሳና ስታሊን ተቃቅፈው ይምጡልን
ከሲኦል ደጃፍ ላይ ጋኔልን ጥሩልን
ልጅ ግራዝያኒ በቶሎ ይምጣልን
ውቡ ገጽታዋ መልኳም እንዲጠፋ
ደጋግመን “አክ!” እንበል ፊቷ ላይ እንትፋ
እውነትን ለመግደል እንጩህ አጥብቀን
ግን እንዳትነሣ በሶስተኛው ቀን!
ትውልድ እየመራች የምታባልገው
እሷ ስለሆነች ስሟ የገነነው
ወዳጅ ዘመዶቿን ፊት ለፊት ተጋፍጠን
በሆታ ተባብረን ፣ ጮኸን - ተጨጩኸን
በጎለጎታ ላይ መስቀል አሸክመን
ኣዋርደን - አዋርደን - እውነትን አዋርደን
ወዳጅ - ዘመዶቿን አሳደን - አሳደን
በገዛ ልብሶቿ እጣ ተጣጥለን
በጭንቅላቷ ላይ የእሾህ አክሊል ደፍተን
መራራውን ሃሞት እሬት አጠጥተን
ጎኗን በጦር ወግተን!
እንባዋን አፍስሰን!

ደሟን አንዥቅዥቀን!
ዳግመኛ እንዳትመጣ በሰው ልጆች አምሳል
እውነትን እንስቀል በወንበዴ መሀል!
እውነት ስለሆነች ...
ስንቱን ያዋረደች
ሜዳ ላይ የጣለች
እውነት ስለሆነች
ስንቱን ያጋለጠች
ሚስጥር ያባከነች
ቅሌት የፈጠራች
እሷ ስለሆነች ....
እውነት ስትፀና ኃላ ይቆጭሃል!
ስንት ሰው እንደእኔ ይጨልምብሃል?
የስንቱን ሰው አንጀት በእሷ ተቃጠለ
ኩሩው ተዋረደ - ታላቁ ቀለለ
እውነት ያጠፋችው ስንት ነገር አለ!!
እውነት ነች !እውነት ነች! እሾህ አሜኬላ
ይሄን አዲስ ትውልድ በክላ - በክላ
አምላኪዋ በዝቶ ኋላ ከመቸገር
ዛሬ ነው መስቀል ላይ እጅ - እግሯን መቸንከር!
እውነት ክፉ ናት መራራ ......
ያለ ስጋት ተኝታችሁ በሠላም እንድታነጉ
ሀቅን ማለባበስ አደል ጨርሶ ማጥፋት ነው ደጉ
“ታወቀ-አልታወቀ” ብሎ መፍራት መጨነቅ ምንድነው?
ሀቅን መሸፋፈን ሳይሆን አፏን አፍኖ መግደል ነው!
እውነትን ካላጠፋናት
መልሳ አጥፊያችን እሷ ናት

እውነትን ሲጥ አርገን ገለን
መቃብሯን በወታደር በመቶ አለቃዎች አጥረን
ሰልስቷን አርባዋን በልተን
ነፍሷን አይማረው ብለን
ስሟን ከታሪክ ላይ ፍቀን
ያዘኑላትን አፅናንተን
ደስ ያላቸውን ሸልመን
ያኔ ነው በሰላም እንቅልፍ
“እፎይ!” ብለን እምናርፍ፡፡
የስው ልጆችን ገመና የምታጋልጥ ለዓለም
ከእሷ በላይ የሚያሳድድ፣ የሚያስጨንቅ ጠላት የለም
ስቀሏት ይቺን ጠንቀኛ
በእሷ ሞት እንዳን እኛ!
ተፃፈ:- ፳፻ዓ.ም

ሰለሞን ሞገስ (ፋሲል)

#share
@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.4K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 21:57:01 ከራስህ አትሽሽ! ከእውነትህ ተፋጠጥ፤ የሰቀልከውን እውነት አውርድ!
(Face the reality!)
(እ.ብ.ይ.)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በየዓመቱ የሚፆመው የአብይ ፆም ሊገባደድ የአንድ ቀን ዕድሜ ነው የቀረው፡፡ ፆሙ የጌታችንንና የመድሐኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የአርባ ቀንና የአርባ ሌሊት ፆም መታሰቢያ የሚያደርግ ዓመታዊ ፆም ነው፡፡ በተለይ ይሄ ሊያልቅ ያለው ሳምንት የክርስቶስን ህማማቱን፣ ግርፋቱን፣ አንግልቱን፣ ስቃዩን የምናስብበት ሳምንት ነው፡፡ አዎ ጌታችን የሰቀሉትን ‹‹የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው›› ብሎ ነፍሱን ቢሰጥም በሶሰትኛው ቀን በመለኮታዊ ሃይሉ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል፡፡ ሞትን አሸንፏል፡፡ ፍቅሩ ምድርን ሁሉ ገዝቷል፡፡

የሚያሳዝነው ጉዳይ ግን ዓለማችን አሁንም እውነትን እንደሰቀለች መሆኗ ነው፡፡ በዚህ በኛ ዘመንና ትውልድ አሁንም ሐቅ እንደተሰቀለ ነው፡፡ በእውነት የሚነግድ ነጋዴ ጠፍቷል፡፡ በታማኝነት ሐገሩን የሚያገለግል ባለስልጣን ህልም እየሆነ ነው፡፡ ዛሬም እውነት በምድራችን ላይ የለችም የሚያስብል ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡ እውነት ያለው ፍቅር፣ እውነት ያለው እምነት፣ ሐቅ ያለው ንግድ፣ እውነት ያለው ወዳጅነት፣ እውነት ያለው ዝምድና፣ እውነት የሞላው ትዳር፤ እውነት ያለው ዕውቀት፤ ለእውነት የሚወግን ህግ፣ ለእውነት የቆመ መንግስት፣ በሀቅ የሚመራ የሰው ልጅ እየጠፋ ነው፡፡ በድብብቆሽ የጦፈ የሴሰኝነት ፍቅር፤ በወረት የሞቀ ወዳጅነት፣ በመከዳዳት የሚገባደድ ስምምነት፤ በመሰለቻቸት፣ በመጠላላትና በመጠፋፋት የሚያልቅ ወዳጅነት፤ በውክቢያና በችኮላ ተጀምሮ ግለቱን ቶሎ በሚጨርስ የወረት ፍቅረኝነት ዓለም እየታመሰች ነው፡፡ ሰው በገዛ የምኞት ገመዱ ተጠፍንጓል፡፡ ልቅ ፍላጎቱ መረን ለቅቆታል፡፡ ስሜቱ አዋክቦ ከሕሊናው አርቆታል፡፡ ደመነፍሱ ከራሱ ጋር አጣልቶታል፡፡ ስጋውና ነፍሱ፤ ስሜቱና መንፈሱ አልተዋሃደም፡፡ ለመብላት ብቻ የሚኖር ሆዳም ትውልድ ሆኗል፡፡ ለገዛ ጥቅሙ ብቻ ሲል የሌሎችን መብትና ጥቅም የሚጋፋ ስግብግብ ፍጥረት በዝቷል፡፡ ብልጠት እንጂ ብልህነት የሌለው ትውልድ በገፍ እያመረትን ነው፡፡

በዚህ ዘመን እውነቱንና እምነቱን በአፉ ብቻ የሚናገር ነው ምድሪቱን የሞላው፡፡ ለመናገር የፈጠነ፣ ለመስማትና ረጋ ብሎ ለማስተዋል የዘገየ ነው ዓለሙን ያጥለቀለቀው፡፡ በኑሮውና በሕይወቱ እውነቱንና እምነቱን በተግባር አጥብቆ የያዘ እምብዛም ነው፡፡ ሰውነቱን አሽቀንጥሮ የጣለ፣ ስብዕናው የተቃወሰ እልፍ ነው፡፡ ይሄ ሰልጥኛለሁ የሚለው ዘመነኛው ትውልድ ከህሊናው የተጣላ፤ ፍቃደ-ልቦናውን የዘነጋ፣ እፍረት የሌለው ፈጣጣ ትውልድ ስለመሆኑ ብዙ ማሳያዎቹን መዘርዘር ይቻላል፡፡ አዎ የዛሬው ሰው በገዛ ፍቃዱ በላዩ ላይ የባርነት ቀንበሩን አክብዷል፤ የሎሌነት ሸክሙን አብዝቷል፡፡ የሰለጠነ መስሎት ሠይጥኗል፡፡ ገንዘብ ገንዘብ ሲል ግንዛቤውን ጥሏል፣ ማስተዋሉን አጥቷል፡፡ ሰውነቱን ላይደርስበት አርቆ ሰቅሏል፡፡

ሰው እውነትን ሰቅሎ ኑሮውን አስወድዷል፡፡ የዋጋ ንረቱን ጭንቅላቱን አዙሮታል፡፡ ዘንድሮ ያልተሰቀለ ምን አለ? እውነት ተሰቅሏል፤ እምነት ተሰቅሏል፤ ኑሮ ተሰቅሏል፣ የእህልና የቁስ ዋጋ ተሰቅሏል፣ ሰውነት ላይደረስበት ተሰቅሏል፤ ደግነት ተወድዷል፤ ታማኝነት እንደብርቅዬ እንስሳ የሚታይ ሆኗል፡፡ አጃኢብ ነው መቼስ!

ወዳጄ ሆይ..... ያንተስ የአንተነትህ ፋሲካ መቼ ነው?? ያንተስ የሰውነት ትንሳኤህ ወዴት አለ?? ከቶ መቼ ይሆን ከሃሳብ ህመምህ፣ አስተሳሰብ ስቃይህ የምትገላገለው?? የሰው ልጆችስ ከወደቅንበት ስብዕናችን የምንነሳው መቼ ይሆን??

አዎ ወዳጄ! ከመንጋው ጋር አትጋፋ! በስሜት ከሚነጉደው ጋር አትንጎድ፡፡ የበዓሉን ምሳሌነት ተረዳ፡፡ የምታየውን፣ የምትሰማውን ሁሉ ከሕይወትህ ጋር እያገናኘህ አስበው፣ ተንትነው፣ አብሰልስለው፡፡ ከዛም የሚጠቅምህን ውሰድ፡፡ በጎ ነገርን ተለማመድ፡፡ በሚጠቅም አዲስ ሃሳብ ትለወጥ ዘንድ በርታ፡፡ በስቅለቱ በዓል የተሰቀለውን ክርስቶስ ህማሙን እያስታወስክ ዛሬም አንተን እያሰቃየህ ያለው የምኞት ዓለም እየመረመርክ፤ ራስህ አርቀህ የሰቀልከውን እውነት አውርድና ለእውነትና በእውነት ኑሮህን ጀምር፡፡ የትንሳኤውን በዓል ስታከብር አንተን የጣለህንና የአሸነፈህን ቀሽም አስተሳሰብ ድል ነስተህ በአዲስና በቀና አስተሳሰብ ተነስተህ ሕይወትህን አቅናው፡፡

ከራስህ አትሽሽ! ከእውነትህ ተፋጠጥ፤ የሰቀልከውን እውነት አውርድ - Face the reality!

‹‹ጥንት የተሠቀለችው እውነት
ለልብ አብነት ነች፣
ለሰው ምሣሌ ነች፤
በደምና በአጥንት፤ ታስራ የተገመደች፡፡
ውስጠኛዋን እውነት መላልሶ ለመስራት፣
የተሠቀለችውንም እውነት፤ ያሻል አለመርሳት፡፡››

....የትንሳኤውን በዓል ስታከብር አንተን የጣለህንና የአሸነፈህን ቀሽም አስተሳሰብ ድል ነስተህ በአዲስና በቀና አስተሳሰብ ተነስተህ ሕይወትህን አቅናው፡፡...

መልካም የትንሳኤ በዓል!

____
እሸቱ ብሩ
ይትባረክ

@EshetuBirruYitebarek
@Zephilosophy
@Zephilosophy
4.4K views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 20:49:46
How water is responding to the energy and vibrations.

This guy is talking about the experiment that proves how different words and emotions affect crystals in the water, which was previously frozen.

Water is an information and energy carrier, and your body is composed over 90% of primarily water. If your emotion & words affects your body directly ,you should be control ur emotion & words.

@Zephilosophy
@Zephilosophy
970 viewsedited  17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 11:14:36 በአርብ መሰረት የታነፀ ባህል
(ተስፋኣብ ተሾመ)

አርብ የስቅለት ቀን ነው።
በቀራኒዮ ብርቱ ሰቆቃ ሆኗል። አለማትን በቃሉ ደግፎ ያቆመው ራሱን ባዶ አድርጎ በገዛ ፈቃዱ ተዋርዷል።
አርብ ሐዘን ያጠላበት ነው።

መስቀል የክርስትና ማዕከላዊ አስተሳሰብ ነው። የእምነቱ መሰረት በመስቀሉ ላይ የቆመ ነው።

ባህላችን ክርስትና ያጠላበት ነው።
ከክርስትና መልኮች ሁሉ የስቅለቱ ቀን በባህላችን ከፍተኛ አሻራ አኑሯል።

መከራን የሚያገዝፍ ልማድ ተጣብቶናል። የመልካም እናትነት ተምሳሌቶች በችጋር የተገረፉ ናቸው። ራሳቸውን እስኪጥሉ ድረስ ሰቆቃ የገረፋቸው ሴቶች ልከኛ እናቶች ይመስሉናል። ራሳቸውን የጠበቁ፥ ደግሞም በምቾት የሚኖሩ እናቶች አረአያነት አይታየንም።

ችግር በቡጢ የነረታቸው ፥ የኑሮ መስቀል ላይ የተቸነከሩ ሁሉ መልካም ሰዎች እንደሆኑ የሚያምን ደመነፍስ አለን። እውነተኛ ፍቅር ከድህነት ወንዝ የሚቀዳ ይመስናል።

ክርስትና ማህበረሰባዊ አስተሳሰባችን ላይ አሻራ አኑሯል። ከክርስትና መልኮች ሁሉ ስቅለት ልማዳችን የታነፀበት መሰረት ነው። እሳቤያችን አርብ ላይ ቆሟል።

አርብ የመከራ ቀን ነው።
ከመራራው ሰቆቃ ማህፀን የፅድቅ ብርሃን እንደወጣ ስለምናውቅ ሁሉንም መከራ የፅድቅ ጥርጊያ አስመስለናል።

ድሃ የሆነ በደል ማድረግን የማያውቅ ፥ በሰቆቃ የሚያልፉ ሁሉ የፍቅር ሰዎች ፥ እንባ መንፈሳዊነት መስሎ ይታየን አይደል?

መከራን በሚያቀድስ መሰረት የታነፀ ልማድ ማስተካከያ ቢበጅለት ሸጋ ነው!

እሁድም የክርስትና ገፅ ነው። እሁድ ታላቅ ትንሳኤ ነው !

(ለክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የስቅለት መታሰቢያ)

@Tfanos
@Zephilosophy
1.5K views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 12:22:31 የትዝታ ክምር
ዴቪድ ሂውም

ከፊት ለፊትህ ባዶ የቲያትር መድረክ አለ፤ አሮጌ መጋረጃዎች ያሉት፤ መሬቱ ለብዙ ጊዜያት ባለመጠረጉም  አቧራ ለብሷል። ድንገትም ከጀርባ ወደ ቴያትር መድረኩ አንድ ሰው መጣ፡፡ እናትህ ነች፤ በሰባት አመትህ ሳለ ተረት ታነብልህ እንደነበረው አሁንም እያነበበች ነው፡፡ ድንገትም እናትህ ከመድረኩ ተሰወረች ፤ ሌላም ሰው መጣ። አንተን ይመስላል ፤ ይህንንም መጽሐፍ እያነበበ ነው፡፡ መመሳሰላችሁ ከፊትህ ያለን መስታወት የማየት ያህል ነው፡፡ ድንገት መድረኩን ብርሃን ወረሰው፤ ተመልሶም ባዶ ሆነ...

ዴቪድ ሂውም የሰው ማንነቱ ትዝታዎቹ ናቸው ይለናል። የምታስታውሳቸው ሃሳቦች፣ እናትህ የመከረችህ ምክሮች፣ ከጓደኞችህ ጋር የነበረህ ጨዋታ.... በሕይወትህ ያሳለፍከው ነገር ሁሉ አሁን ላይ ያለህን ማንነት ይቀርጸዋል። ወደ ምድር ስትመጣም ልክ እንደ ባዶ የቲያትር መድረክ ነበርክ፣ አሁን ግን በብዙ ትዝታዎች ተሞልተሃል።

“እኔ ማን ነኝ ለሚለው ጥያቄህም መልስ የሚሆነው ትዝታዎችህ ነህ ይሆናል። ልክ በድስት ውስጥ ያለ እና ሲንተከተክ እንደሚናወጥ ወጥ ነህ፡፡ በአእምሮ ውስጥ ያሉ ትውስታዎች እና ልማዶች ተደባልቀው ልክ እንደወጡ ሁሉ የሆነ ማንነት ይሰጡሃል። ይህ ወጥ በመጀመሪያ ሽንኩርት፣ ዘይት እና በርበሬ ብቻ ነበር... እየቆየ ሲሄድ ግን አይነቱ ይቀየራል፡፡ ምናልባትም መጨረሻው ስጋ ወጥ ወይም ሽሮ ወጥ መሆን ይሆናል፡፡ ሆኖም እያንዳንዱ ወደ ድስቱ የገባ ግብዓት የመጨረሻውን የወጥ ማንነት ይሰጠናል። ያንተም ማንነት እንደዚያው ነው፡፡ ቁጡነትህ፣ እርጋታህ፣ ፍቅርህ፣ ጥላቻህ፣ ችኮላህ፣ ትዕግስትህ፣ መወላወልህ፣ ቆራጥነትህ... ሁሉም ወደ አእምሮህ ከገቡ እና ካሳለፍካቸው ሁነቶች ይመነጫሉ፡

ለሂውም ሰዎች ሁሉ አንድ አይደሉም፡፡ ወጥ ሁሉ የተለያየ ቃና እንዳለው፣ ሁሉ ሰው የመጣበት መንገድ ይለያያል እና ፍጹም የተለያየ ማንነት ይኖረናል፡፡ ከሌላው ጋር አንድ የሚያደርገንም ነገር የለም፡፡ አንተ እራስህ የትውልድ ቦታህን ወይም የተወለድክበትን ጊዜ ቀይረህ ብትወለድ ፍጹም የተለየ ማንነትን ትይዛለህ፡፡ አዲስ በሌላ ጊዜ ወይም ቦታ ላይ የሚወለደው “አንተ” እና አሁን ላይ ያለኸው አንተ አንድ አይነት ሰው አትሆኑም።

እናም ሂውም አንተ የሃሳቦችህ እና የትዝታዎችህ ክምር ነህ ይልሃል። የእኔ ማንነትም የቱ ነው ካልክ፣ ወደ ባዶ የቲያትር መድረክ አፍጥጥ። አእምሮህ በምድር ላይ ያሳለፍከውን ሕይወት በዳግም ምልሰት ያስቃኝሃል፡፡ በአእምሮህ ከተቀረጹ ሃሳቦች ውጪ ማንነት የለህም። ማንነትህን እነርሱ ብቻ ይወስኑልሃል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.2K viewsedited  09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ