Get Mystery Box with random crypto!

.... ካለፈው የቀጠለ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ያለን ነገር ወስደህ ለራስህ ማዳበሪያ መጠቀም ግን | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

.... ካለፈው የቀጠለ

በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ያለን ነገር ወስደህ ለራስህ ማዳበሪያ መጠቀም ግን ትችላለህ፡፡ ወይም ደግሞ በቆሻሻ መጣያው ውስጥ በትግል መኖር ትችላለህ፡፡ ያለህ ምርጫ ይህ ነው፡፡ በስሜት ህዋሳትህ የተገነዘብከው ሁሉ ወደ ውስጥህ ስለሚገባ የምትቀበለውን ነገር በተመለከተ መምረጥ ባትችልም፣ የትኛውን እንደምትጠቀምና የትኛውን እንደማትጠቀም የማስተዋል ኃይል ግን አለህ፡፡ ራስህን በመመልከት ሕይወትህ ምን ያህሉ አስገዳጅ፣ ምን ያህሉ ደግሞ በማወቅ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ተመልከት፡፡ አብዛኛው ክፍል አስገዳጅ እንደሆነ ታያለህ፡፡ በአስገዳጅነት የተከሰትክ ከሆነ፣ ራስህ እንድትሆን በፈለግከው መንገድ አይደለህም ማለት ነው፡፡ በሕይወትህ ያለብህ አንድ ችግር፣ ሕይወት ሊሆን ይገባዋል ብለህ በምታስበው መንገድ የሚሆን አለመሆኑ ነው፡፡ በፈጣሪ የምታምን ከሆነ፣ አንድ ነገር በአንተ መንገድ ካልሄደ፣ በእርሱ መንገድ ሄዷል ማለት ነው። በፈጣሪ መንገድ የሄደ በመሆኑ ደስ ሊልህ ይገባል፡፡ ያ ግን እውነታ አይደለም፡፡ ችግሩ ዓለም በአንተ መንገድ አለመሄዱ ሳይሆን አንተ በራስህ መንገድ አለመሄድህ ነው።

በዓለም ላይ ማንም በአንተ መንገድ አይከሰትም፡፡ በዙሪያህ ያለ ማንኛውም ሰው መቶ በመቶ በአንተ መንገድ አይመጣም፡፡ አንተ ግን በራስህ መንገድ መሆን አለብህ፡፡ በራስህ መንገድ የማትሆን ከሆነ ግን አሳዛኝ ትሆናለህ፡፡ ሰው የመሆን አሳዛኝ ነገር ይህ ነው፡፡ ዓለም በአንተ መንገድ አለመሆኗ ችግር አይደለም፣ ችግሩ አንተ በራስህ መንገድ አለመሆንህ ነው፡፡ ውስጣዊ ነገሮችህን ካላስተካከልክ፣ በአጋጣሚ ለመኖር እየሞከርክ ነው ማለት ነው፡፡ ከአንድ ነገር ነፃ መሆንና አንድን ነገር አለማወቅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ የዓለምን መንገዶች ካላወቅክ፣ ዛሬ ወይም ነገ ልትጋጭ ትችላለህ፡፡ የዓለምን ተንኮለኛ  መንገዶች የምታውቅ ከሆነ ግን ወደዚህ ውስጥ አትገባም፡፡ ስለዚህ ስቃይ በማወቅ የሚመጣ አይደለም፡፡ ማንም ሰው አውቆ ራሱ ላይ ስቃይ አይፈጥርም፡፡ በሆነ መንገድ እየተሰቃየህ ከሆነ፣ ያ እየተሰቃየህበት ያለው ክፍል አያውቅም ማለት ነው፡፡ የተለያዩ ደረጃዎች ያሉት ስቃይ እየተከሰተ ከሆነ፣ በውስጥህ የተለያየ ደረጃ ያለው አለማወቅ አለ ማለት ነው፡፡

በውስጥህ ንቁ የሆነው የትኛውንም ነገር በምትፈልገው መንገድ ትጠብቀዋለህ፡፡ የማይታወቀውን የትኛውንም ነገር ደግሞ በምትፈልገው መንገድ ልትጠብቀው አትችልም፡፡ ስለዚህ በሕይወትህ ልታደርገው የሚያስፈልግህ ነገር ቢኖር ራስህን በበለጠ ሁኔታ ንቁ ማድረግ ነው፡፡ ሁሉም ነገር ሙሉ በሙሉ ንቁ እንዲሆን ጥረት የምታደርግ ከሆነ፣ አንተነትህ መቶ በመቶ በምትፈልገው መንገድ ይሆናል፡፡ ይህ አንድ ሽራፊ ሕይወት ልክ አንተ በምትፈልገው መንገድ ይሆናል፡፡ ያ በሚሆንበት ጊዜ ያለጥርጥር ራስህን እጅግ ደስተኛ ሰው እንደምታደርግ ጥያቄ የለውም፡፡

ምንጭ ፦ የህይወት ኬሚስትሪ (ሳድጉሩ)
ትርጉም ፦ ሀኒም ኤልያስ

@Zephilosophy
@Zephilosophy