Get Mystery Box with random crypto!

Consequentialism Vs Hedonism ምንጭ ፦ የፍልስፍና ትምህርት ቅፅ ፪ አርታኢና አዘ | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

Consequentialism Vs Hedonism

ምንጭ ፦ የፍልስፍና ትምህርት ቅፅ ፪
አርታኢና አዘጋጅ ፦ ብሩህ አለምነህ

እነዚህ ሁለቱ የሥነ ምግባር ፅንሰ ሐሳቦች ልዩነታቸው ትንሽ ያምታታል፡፡ አንድ የሚያደርጋቸው ሁለቱም ውጤት ተኮር መሆናቸው ሲሆን፤ ልዩነታቸው የሚመጣው የውጤቱ ዓይነት ሲመረመር ነው፡፡

•Consequentialism ውጤቱን ከላይ እንደገለጽነው በጥሩነትና በመጥፎነት ሲገልፀው ማለትም አንድ ድርጊት ትክክለኛ የሚባለው ጥሩ ውጤት ሲኖረው ነው በማለት የሚከራከር ሲሆን ጥሩና መጥፎ ማለት ደግሞ እንዳቀማመጣቸው ጠቃሚና ጎጂ፤ አስደሳችና አስከፊ፣ ገንቢና አፍራሽ፣ የሚያስቅና የሚያሳዝን፣ ጤናና በሽታ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

.Hedonism በበኩሉ በመሠረታዊ ባህሪው ጥሩ የሆነ ነገር አካላዊ/ጊዜያዊ እርካታ(Pleasure) ሲሆን መጥፎ የሆነው ደግሞ ህመም (Pain) ብቻ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡

Hedonism የሚመራበት መርህ pleasure principle ይባላል፡፡ ሄዶኔ (Hedone) ማለት በግሪክ እርካታ (Pleasure) ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ‹‹ሄዶኒስት ነው›› የሚባለው ግቡ አካላዊ እርካታ (Pleasure) ብቻ ሲሆን ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ በHappiness (ደስታ) እና በPleasure (እርካታ) መሐከል ያለው ልዩነት የHedonismን ትክክለኛ ሓሳብ ሲያወሳስበው ይታያል፡፡ ‹‹እርካታ›› ከአካላዊ ፍላጎቶች መሟላት (ምግብ፣ መጠጥ፣ ወሲብ) ጋር የተገናኘ ሲሆን (ለዚሀም ይመስላል አሪስቶትል ይህ ለእንስሳት እንጂ ለሰው ልጅ የሚሆን ግብ አይደለም በሚል የሚተቸው) ደስታ ግን ዘለቄታ ያለውና በራሱ የህይወት ግብ መሆን የሚችል ነው (Aristotlc 1996 10)፡፡

ከላይ ወደተነሳንበት የConsequentialism እና Hedonism ልዩነት ስንመለስ ለምሳሌ እኔ ‹‹እንቅስቃሴ የምሰራው ለጤናዬ ስለሚረዳኝ ነው›› ካልኩ ‹‹እንቅስቃሴ መስራቱ ጥሩ ነው›› የሚለው አመለካከቴ የእንቅስቃሴን ትክክለኛነት በውጤቱ መሆን ላይ የተንጠለጠለ ስለሚያደርገው Consequentialist ነኝ፤ ሆኖም ግን ሄዶኒስት አይደለሁም፡፡ ምክንያቱም፣ ግቤ እርካታ ሳይሆን ጤና ስለሆነ፡፡ ስለዚህ፣ Consequentialist የሆነ ሁሉ ሄዶኒስት ነው ማለት አይደለም፡፡

Consequentialist ሄዶኒስት የሚሆነው የሚፈለገው ውጤት እርካታ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ግን፣ እኛ የምንፈልጋቸው ውጤቶች በህይወታችን ውስጥ እርካታ ብቻ አይደለም፡፡ ልክ እንደ ጤና፣ ገንዘብ፣ እውቀትን እንዲሁም ስልጣንን ግብ አድርገን ልንነሳ እንችላለን፡፡ በዚህ ጊዜ Consequentialist ሆነን፣ ሄዶኒስት አልሆንንም ማለት ነው፡፡ ሆኖም ግን፣ አንድ ሰው፣ ‹‹የአንድ ድርጊት ውጤት ጥሩ ነው የሚባለው አርኪ ሲሆን ነው ብሎ የሚያምን ከሆነ ይሄ ሰው Consequentialist ብቻ ሳይሆን hedonistም ነው ማለት ነው፡፡

@zephilosophy
@zephilosophy