Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የቴሌግራም ቻናል አርማ zephilosophy — ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
የሰርጥ አድራሻ: @zephilosophy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.37K
የሰርጥ መግለጫ

ፍልስፍና  እውነትን በመፈለግ- ሀሳዊ እምነቶችን በማጋለጥ እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል።
በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤  ሀይሞኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 18

2022-06-28 20:55:29 የሰው መሆን ጸሀይ ሲጠልም፣.....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
..

ሰውነትን ልንረዳው ጥልቅ ነው፣ ወደ ውስጣችን የገባ ከፍ ያለ ድብታ አለ። ድብታውን በጠነከረ ስክነት ብቻ ነው የምንፈታው። ስሜትን የሚፈትን እንቃታ ውስጥ ይሚከት ህመም ውስጥ ነን። ከ እስከ ብለን የማንቋጨው ቀውስ ገብቶብናል።

እንደሰው ከማይቆጥረን ዘመናዊነት ተረክ ተበልተን ማደጋችን በራሱ ያላየነው ስውር ቁስላችን ነው። ወዳላየናቸው መሪር ገሀዶች እንሰባሰብ፣ እዛ ላይ ብዙ ቁስላችን ይታከማል። ካልሆነ የክብ ዙር ልፋት ነው ትርፋችን፣ የዛሬው ስብራት ነገም በሌላ አቅጣጫ እንዳይመጣን ማስተዋል ላይ እንበርታ...።

......

እንደማለፊያ ምሳሌ
።።።።።።።።።።።።።።።።።

ዩጀኒክስ…. ከነጮች ውጪ ያለን የሰው ዘር ለማክሰም የተቀመረ የጥቂት ሳይንቲስቶችና ጥቂት ቱጃሮች ሴራ ነው። ከጋልተን የመጽሃፍ ህትመት ጀምሮ (1883) እስከ 1956 ድረስ በተከታታይ በመላው አለም ሳይቀር እንደእሳት ሰደድ የተስፋፋ ንቅናቄ የፈጠረ ታሪክ አለው። ግን ትምህርት ቤት ርዕሱን የሰማ አለ? ለምን ከእውቀት ሰፈር እንዲሸሽ ሆነ?

ምክኒያቱም በግልጽ የጄኖሳይድ ሳይንስ ስለሆነ ነው። ህዝብን መርጦ የማክሰም እውነታ ስላለው። በመሪዎች ጭምር ድጋፍ ያገኘ የዘረኝነት አመለካከትን ሳይንሳዊ ለማድረግ የሚጥር አስተሳሰብ በመሆኑ ነው። ዊንስተን ቸርችል፣ ቲዎዶር ሩዝቬልት፣ ዊድሮው ዊልሰንና ኒክሶን ያሉ ታላላቅ መሪዎች ያሞካሹት ድብቅ ገመና ነው።

ያደገ የዝግመተ ለውጥ ስነ-ልቦና አካል ነው። አፍሪካዊ የሆነ ሁሉ በጥልቀት አጥንቶ ለኋላ ቀርነቱ ከሚያስባቸው ብዙ ምክኒያቶች አንዱ ስለሆነው የዩጀኒክስ እንቅስቃሴ ብዙ ማንበብ አለበት። ቃሉ መጀመሪያ የታወቀው ሰር ፍራንሲስ ጋልተን በተባለ ሳይንቲስት ነው። የተሻሉ የሰው ዝርያዎችን የመፍጠር ሀሳብ ነው።

ከሰዎች መሃል ለስልጣኔ የቀረቡ፣ የተሻለ ማሰብ የሚችሉና ቀጣዩን ስልጣኔ ለማቆየት የሚችሉ ብቁ ሰዎችን መርጦ ማስቀረት የሚያችል ዘዴ ነው። ፍራንሲስ ጋልተን ስራዎቹን ስታጠኑ ብዙ ያወቀና በባዮሎጂ መስክ ክብር ከሚሰጣቸው በኩራን አንዱ ሆኖ ታገኙታላችሁ።

የአፍሪካ ጥቁሮች ላይ የነበረውን አሉታ አስተሳሰብ ጨምሮ በተለያዩ ጎሳዎች ላይ ኢ-ምግባራዊ ሀሳቦችን አንጸባርቋል። በአሜሪካ ታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈውን በጥቁሮች ላይ የደረሰ ሳይንሳዊ የማጥፋት እንቅስቃሴ እጁ እንዳለበት ስትረዱም አዋቂነትን ጥያቄ ውስጥ ትከታላችሁ።

ለእኛ ፍንትው ብሎ እንዲገባን ዩጀኒክስ ባጭሩ ጀኖሳይድን ሳይንሳዊ ለማድረግ የሞከረ የዘረኝነት እንቅስቃሴ ነው። በትምህርት ቤቶቻችን በግልጽ እንድናዉቀው መደረግ ያለበት ግን ከታሪክ እውነት ጀርባ ያለ መራራ እውነት ነው።

የመሲሆች እድር
ቡርሀን አዲስ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
5.1K viewsedited  17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 20:52:54 የትንፋሽ ሜዲቴሽን ሁለት አይነት የሙሉ እዕምሮ አተነፋፈስ ሜዲቴሽን አለ።አንዱ በቀን ውስጥ የተወሰነ ጊዜ መድበን ሲሆን ፤ሌላ ስራችንን ሁሉ አቁመን የምናደርገው ሲሆን ፤ተቀምጠን ወይም አልጋ ላይ ጋለል ብለን ወይም ራስችንን እንደተመቸን አስቀምጠን ሙሉ በሙሉ ትኩረታችን ትንፋሻችን መግባትና መውጣት ላይ ይሆናል ማለት ነው ። ይሄን በየጊዜው አዘውትርን ያለማቁዋረጥ የምናድረግ ከሆነ በዚህ በራስችን ላይ…
3.9K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 12:45:41
አወዛጋቢው መፅሀፍ በገበያ ላይ ነው!! ገዝታችሁ እንድታነቡት ጋብዣለሁ!!

የተጠላው እንዳልተጠላ
ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
6.4K viewsedited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 21:20:36 ባለፀግነት ስትወለዱ ጀምሮ የተሰጣችሁ መብት ነው!

ምንጭ፦ ንቃተ ህሊና (ኦሾ)
ትርጉም ፦ አና ፍራንክ

ሕይወት ማለት በሁሉም ነገር መብዛት፣ መበልፀግ ነው። ህልውናን (ተፈጥሮን) ተመልከቱ። ድሃ ይመስላችኋል? ጥዑም መዓዛ ያላቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አበቦች ተመልከቷቸው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ከዋክብት ተመልከቷቸው፤ የሰው ልጅ ሊቆጥራቸው እንኳን አልቻለም፣ ይቆጥራቸዋል ብዬም አላስብም። በአይናችሁ ብሌን ቢበዛ ሶስት ሺ ከዋክብትን ማየት ብትችሉ ነው፤ ይህ ደግሞ ምንም አይደለም። እነዚህ ከዋክብት እየሰፉ ነው። አንድ አበባ ፈክቶ ቅጠሎቹ እንደሚዘረጋጉ ዩኒቨርስም በከፍተኛ ፍጥነት እየሰፋ፣ እያበበ፣ እየተከፈተ ነው። ከዋክብቱ ከመሃል እየራቁ ነው። መሃሉ በትክክል የት እንደሚገኝ አናውቅም፥ አንድ ነገር ግን እርግጥ ነው መላው ዩኒቨርስ በፍጥነት እየተንቀሳቀሰ፣ ህያው እየሆነ ነው።

ይህን አካባቢ ሊጎበኙ የሚመጡ ሰዎች ህይወት ምን እንደሆነ አያውቁም። እኒህ ሰዎች ህይወትን ፍፁም አልኖሩም። አዎ፣ ተወልደዋል፤ ነገር ግን ህያው ለመሆን መወለድ ብቻውን በቂ አይደለም። እየበሰበሱ እየኖርን ነው ይላሉ። ምንም ሳይኖሩ አንድ ቀን ይሞታሉ። በዓለም ዙሪያ እንዲህ አይነት ተዓምራት ይከሰታሉ፤ ሰዎች ሳይኖሩ ይሞታሉ. . . ፍፁም የማይቻል ነገር! ሆኖም ይህ ነገር ሁልጊዜ ይከሰታል። ብዙዎች ይህ ነገር የሚገባቸው ከሞት አፋፍ ሲደርሱ ነው፤ ከሞት በራፍ ላይ ቆመው አስገራሚ ነገር ነው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ህይወትን እንዳልኖርኳት አሁን ገባኝ» ይላሉ።

በዚህ ሁኔታ የምትኖሩ ከሆነ ለምንድነው የምትኖሩት? ለፍቅር፣ ለደስታ፣ ለፍስሃ. .. ካልሆነ ለምን ትኖራላችሁ? «ብልፅግና» ምንድነው? ብልፅግና ህይወትን የበለጠ አስደሳች፣ የበለጠ ተወዳጅ፣ የበለጠ ምቹ፣ የበለጠ የሚደላ ማድረግ ነው።

ታላቁን የሙዚቃ ዓለም የማያውቅ ሰው ድሃ ነው፤ ይህ የጐደለው ሰው ከህይወት ታላላቅ ምቾቶች አንዱን አጥቷል። በፒካሶ፣ በቫን ጉህ ስራ ያልተደሰተ ስለ ቀለማት ምንም አያውቅም፤ በፀሃይ ውጣትና ግባት ካልተደሰተ እንዴት በሊኦናርዶ ዳ ቪንቺ ስራ ሊደሰት ይችላል? በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለቅፅበት እንኳን ቆም ብለው ፀሃይዋ ስትወጣ ስትገባ፣ ከሰማዩ ጀርባ ቀለሟን ስታፈስ ሳይመለከቱ ኖረው ይሞታሉ።

መኖር ማለት ህይወትን በምሉዕነት ማሳለፍ ነው - ሙዚቃውን፣ ግጥሙን፣ ስዕሉን፣ ቅርፃ ቅርፁን ማጣጣም። እኔ የድህነት አምላኪ አይደለሁም - የድሎት እንጂ። ህልውና ደግሞ የተረፈው፣ የተትረፈረፈው ነው። አንድ አበባ በቂ ሆኖ ሳለ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አበቦች ያብባሉ። ህልውና ምስጢር ሆኖባችሁ አያውቅም? የከዋክብት መብዛት ለምን አስፈለገ?

ይህን ጥያቄ ያቀረቡት እነዚህ ቂሎች የሚያምኑበትን ፈጣሪ ቢያገኙት «የከዋክብቱ መብዛት ለምን አስፈለገ? ይህ ሁሉ ምቾት ምንድነው? ጥቂት ነገሮች አይበቁም ነበር? ብዙ አዕዋፍ፣ እንስሳት ሰብአዊ ፍጡራን መኖራቸው ለምን አስፈለገ?» ብለው በጠየቁት ነበር።

ሳይንቲስቶች በቅርቡ ይፋ እንዳደረጉት ቢያንስ ሃምሳ ሺ የሚሆኑ ፕላኔቶች አሉ። ምን አይነት ቀለም፣ ምን አይነት ቅርፅ፣ ምን አይነት ውበት እንዳላቸው አናውቅም፡፡ አንድ ነገር እርግጥ ነው ህልውና የተትረፈረፈ መሆኑ። ሁሉም ነገር የምቾት ነው። ህልውና ድሃ አይደለም። ድህነትን የፈጠረው ሰው ነው።

መንደራችንን ለማየት እዚህ የሚመጡት ሰዎች እዚህ ሲመጡ በአዕምሯቸው አንድ ነገር ይዘው መሆን አለበት። ምናልባትም «ጋንዲ» የሚለውን ፊልም አይተው ይሆናል፤ ስለ ምስራቃውያን ምናኔም ሰምተው ይሆናል። እኔ መናኝ አይደለሁም። እኔ ያን ያህል ደደብ አይደለሁም። እኔ ማህተማ ጋንዲ አይደለሁም። እሱን አጥብቄ ነው የምቃወመው። በዓለም ላይ ለሚታየው ድህነት ተጠያቂዎቹ እንደ ማህተማ ጋንዲ ያሉ ሰዎች ናቸው።

አዎ በጋንዲ መንደር ውስጥ እንዲህ አይነት ጥያቄ የሚጠይቅ አይኖርም። ወደዚያ መንደር ብትሄዱ ሃዘን ይሰማችኋል። የጋንዲ ልጅ ራምዳስ እኔን ለማግኘት በጣም ፈልጐ ስለነበር አንድ ቀን ጋበዘኝ። ወደዚያ የሄድኩት ጋንዲ ከሞተ በኋላ ነበር። በግቢው ውስጥ ሰላሳ፣ ሰላሳ አምስት ሰዎች አሉ፤ ሁሉም ከጋንዲ ጋር ነበር የሚኖሩት። እናም ራምዳስን «እነዚህን ሰዎች ለምን ታሰቃዮዋቸዋላችሁ? በድህነት፣ በተራ ኑሮ ስም እነዚህን ሰዎች ከህይወት አውጥታችኋቸዋል» አልኩት። የሚበሉት ነገር በሙሉ አይጣፍጥም። ህንድ ውስጥ አንድ ሃይማኖተኛ የሆነ ሰው ሊያስወግድ ከሚገቡት ነገሮች አንዱ ጣዕም ነው። ማር አምስት ታላላቅ መርሆች አሉት፡ አንዱ የጣዕም አልባነት መርህ ነዉ እነዚያ ታላላቅ የሚባሉት አምስት መርሆች እውነት፣ ሰላማዊነት፣ ንብረት አልባነት፣ አለመስረቅና ጣዕም አልባነት ናቸው።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
4.4K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ