Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የቴሌግራም ቻናል አርማ zephilosophy — ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
የሰርጥ አድራሻ: @zephilosophy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.37K
የሰርጥ መግለጫ

ፍልስፍና  እውነትን በመፈለግ- ሀሳዊ እምነቶችን በማጋለጥ እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል።
በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤  ሀይሞኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-07 21:38:39 የእስረኞቹ እንቆቅልሽ

አንተ እና ጓደኛህ በአንድ ወንጀል ተጠርጥራችሁ ታሰራችሁ፡፡ ሆኖም መርማሪ ፖሊሶቹ ምንም አይነት ማስረጃ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ እናም ሁለታችሁም በተለያየ ክፍል እንድትሆኑ ተደረገ። መርማሪዎቹም ለየብቻችሁ ያሉትን አማራጮች አቀረቡላችሁ።


አማራጭ አንድ - አንተ ከተባበርክ እና ወንጀላችሁን ከተናዘዝክ ነገር ግን ጓደኛህ ዝም ካለ አንተን በነጻ እንለቅሃለን እርሱ ግን
አስራ አምስት አመታት ይታሰራል፡፡

አማራጭ ሁለት - ጓደኛህ ወንጀላችሁን ከተናዘዘ ነገር ግን አንተ ዝም ካልክ፣ እርሱ በነጻ ይለቀቃል... አንተ አስራ አምስት አመታትን ትታሰራለህ።

አማራጭ ሶስት- ጓደኛህም አንተም ከተባበራችሁን ሁለታችሁም አምስት አመታትን ትታሰራላችሁ፡፡

አማራጭ አራት- አንተም ጓደኛህም ካልተናዘዛችሁ፤ ሁለታችሁም ቀላል የሆነ የአንድ አመት እስራት ትታሰራላችሁ።

በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ብትሆን ምን ታደርጋለህ?
መናዘዝህ የተሻለ ውጤትን የሚያስገኝ ይመስላል፤ ጓደኛህን ብትከዳውና ብትናዘዝ  የሚገጥምህ በነጻ የመለቀቅ ዕድል ነው᎓᎓በተቃራኒው ዝም ብትልና ባትናዘዝ፣ የአንድ አመት ወይም የአስራ አምስት አመት እስራት ይጠብቅሃል።

ሆኖም አንተ ነጻ ሁነህ ጓደኛህ አስራ አምስት አመታትን በእስር ቤት ሲማቅቅ ማየት ምን አይነት ስሜት ይፈጥርብሃል?

እናም ይህ እንቆቅልሽ የሚያስነሳው መሰረታዊ ጥያቄ “እንደ ማህበረሰብ ማሰብ” ወይስ “እንደ ግለሰብ ማሰብ” የሚል ይሆናል። ለሁላችንም የተሻለ አማራጭ የሚሆነው እንደ ማህበረሰብ ማሰብ ነው፤ ሆኖም ሌላኛው ሰው ምን እንደሚያስብ አናውቅምና ለራሳችን
መልካም የሚሆነውን ለማድረግ ስንል ራስ ወዳድ እንሆናለን፡፡ እኔ እንኳ ባልስርቅ ሌላው ይሰርቃል የሚል ሃሳብ ይፈጠራል። ይህ አስተሳሰብም በድሃ አገራት ላለው የሙስና እና ስርዓት አልበኝነት አንዱ ምክንያት ነው፡፡

ለምሳሌ ያህል፣ አንድ አሳ የሚሰገርበት ሃይቅ አለ ብለን እናስብ። አሳ አስጋሪዎች በዚህ ሃይቅ ውስጥ ያሉት አሳዎች በራስ ወዳድነት ያለ ልክ የሚያጠምዱ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር ተመናምኖ በአንድ አመት ውስጥ ሃይቁ አሳ አልባ ይሆናል። ሆኖም ግን አግባብ ባለው ሁኔታ በልክ እና በመጠን የሚያሰግሩ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር አይመናመንም፤ እንዲያውም ከአመት ወደ አመት የሚያገኙት የአሳ ቁጥር እየጨመረ ይመጣል።

እዚህ ላይ ዋነኛ ጥያቄው መተማመን የሚለው ነው፡፡ አሳ አስጋሪዎቹ በመጠን ሊያሰግሩ ቢስማሙም አንዳቸው ሌላኛውን እስካላመኑ ድረስ ስምምነታቸው ዋጋ አይኖረውም፡፡ ልክ በሁለት ክፍሎች ውስጥ ለብቻቸው ተቀምጠው እንዳሉ እስረኞችም ይሆናሉ፡፡

ምንጭ- ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት-ፍሉይ አለም

@Zephilosophy
@Zephilosophy
2.2K viewsedited  18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 07:12:34 "መላው ተፈጥሮ በአንድ ቀላል ምክንያት ውድድር ባልመረዘው ጥልቅ ሰላም ውስጥ ነው ። ከናካቴው ምንም ውድድር የለም ፤ ታላቁ አዘርሊባሎስ ዛፍ ስለ ትልቅነቱ "እኔ ከሌሎች ትልቅ ነኝ" የሚል እኔነት የለውም ። ይህ ልክ አንዲት የፅጌሬዳ ቁጥቋጦ "እኔ ትንሽ ነኝ" በሚል አስተሳሰብ የዝቅተኝነት ስሜት እንደማይሰማት ነገር ነው ። ምንም የበላይነት ምንም የበታችነት የለም ። ግን እያንዳንዱ ነገር የተለየ ነው ። ይህ ደደብነት በሰው ልጅ ንቃተ-ህሊና ብቻ ነው ስተት ያለው - የሰው ልጅ ንቃተ -ህሊና ብቻ ነው በዚህ የበላይነት እና የበታችነት አባዜ የተገራው።"

ኦሾ ፦ የመጨረሻው ህግ (THE DHAMMAPADA)
ትርጉም ፦ በዩሐንስ አደም
813 views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 18:40:42 መከራ ውስጥ ያለ ሕዝብ ተስፋኛ ነው። አንድ ቀን የተጫነበት የመከራ ቀንበር እንደሚሰበር ተስፋ ያደርጋል። በተስፈኝነቱ የተነሳ አማኝ ይሆናል።
'ከመከራ አወጣኻለሁ፥ መብትህን አስከብረዋለሁ' የሚልን ወሽካታ አምኖ ለመከተል አያመነታም።

መከራ ወለድ ተስፈኛነት ተንኮለኞችን አምኖ እንዲከተል ያደርጋል

ህዝባችን በስቃይ የሚልፍ ፥ በመከራ የሚፈተን ፥ ሰቆቃ ደጋግሞ የሚግበኘው ነው።
"አንድ ቀን ከዚህ መከራ አርነት እወጣለሁ" የሚል ተስፋ የመኖር ሃይልን ይሰጣል። ይኽ መልካም ቢሆንም በህዝቡ ተስፈኛነት የሚያተርፉ ነጋዴዎች ተፈጥረዋል። "ካላችሁባት ሰቆቃ ነፃ አወጣችኋለሁ" የሚሉ ጮሌዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው መንበር ላይ ወጥተዋል፥ ሃብትንም አጋብሰዋል።

የድሆች ችጋር ብልጣብልጦችን አበልፅጓል፥ የህሙማን ደዌ የቅንጦት መንገድን የጠረገላቸው አሉ፥ የሚስኪኖችን ረሃብ ታከው ለቁንጣን የተዳረጉ ጥቂት አይደሉም።

ለዚህ ሁሉ የሚዳርገው "አንድ ቀን ያልፍልኛል" የሚል ተስፈኝነት ነው።

የህዝቡ የችጋር ቀንበር ካልሰበረ በቀር መነገጃ መሆን አይቀርም።

እውቀት ወለድ ነፃነት የመጀሪያው የአርነት መንገድ ነው!

ተስፋበዓብ ተሾመ
@Tfanos
@Tfanos
890 viewsedited  15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 19:12:48 From OShO Views:

በመጀመርያ ወላጆህ ፣ አስተማሪዎችህ፣ ጐረቤቶችህ ፣ህብረተሰቡ  አንተን እንደ አንተነትህ ተቀብለውህ አያወቁም። እያንዳንዱ ሰው አንተን ሊያስተካክልህ፣ የተሻለ ሊያደርግህ ነው የሚሞክረው። ሁሉም ሰው ጣቱን የሚቀስረው እንከን፣ ስህተት ፣ ግድፈት።  ድክመት፣ አቅመቢስነት ላይ ነው፡፡

በነዚህ ደግሞ እያንዳንዱ ሰው ይንበረከካል፡፡ የትኛውም ሰው ውበትህን አይናገርም፣ ችሎታህን አይገልጽም፡፡ ታላቅነትህን አያጎላም፡፡

በሕይወት መገኘትህ ብቻ በራሱ ትልቅ ፀጋ ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው ለዚህ ህልውናህ አመስጋኝ እንድትሆን አይነግርህም፡፡ በተቃራኒው ግን እያንዳንዱ አጕረምራሚና አቤቱተኛ ነው።

ገና ከመጀመሪያው ስትፈጠር አንስቶ፣ በሕይወትህ ዙሪያ ያሉ ሁሉ አንተ መሆን እንደነበረብህ አለመሆንክን ይጠቁማሉ፣ ልትከተላቸው የሚገቡህንና መምሰል ያለብህን ታላላቅ ፍጹማን ይነግሩሃል፡፡

ያንተ ራስህን መሆን መቻል ግን አይመሰገንም፡፡ ገና ወደፊት የምትመስለው ስብዕና ነው የሚመሰገነው፡፡ የተከበርክ፣ ሀያል፣ ባለፀጋ፣ ምሁር መሆን እንደነበረብህ አለመሆንክን በማንኛውም መልኩ ዝነኛ መሆን ከቻልክ ትመሰገናለህ፤ አንድ ሌላ ፣ተራ ሰው መሆንህ ግን ቦታ አይኖረውም፡፡

ያለማቋረጥ ሌላን ሰው እንድትሆን ግፊት መደረጉ አንተ
ውስጥ ምናብ ይፈጥራል።«ያሁን እኔነቴ በቂ አይደለም። የሚጐድለኝ ነገር አለ፡፡ ስለዚህም መሆን ያለብኝ በዚህ ሳይሆን አንድ ሌላ ደረጃ ላይ ነው፡፡ መገኘት ያለብኝ ቦታ ላይ አይደለሁም ያለሁት፡፡

መሆን ያለብኝ ከዚህ ከፍ ያለ ቦታ፣ ከፍተኛ ስልጣን ያለው፣ ዋና ገዢ፣ እጅግም የተከበርኩ፣ ታዋቂ መሆን ነው» ትላለህ። ይህ  ደግሞ አስነዋሪና ተጨባጭ ያልሆነ ጐዶሎ ታሪክ ነው። ሰዎች እንዴት ያሉ እናቶች መሆን እንዳለባቸው፣ እንዴትስ ያሉ አባቶች እንዳለባቸው፣ እንዴት ያሉ መምህራንም መሆን እንዳለባቸው በጥቂቱም እንኮን እውቀቱን ቢይዙ ይህ ጎደሎ አስተሳሰብ በቀላሉ ሊወገድ በቻለ ነበር።

ልጅ ወልደህ ለገዛ ራሱ አክብሮት እንዲኖረውና ራሱን
በርሱነቱ እንዲቀበለው ታግዘዋለህ እንጂ አታበላሸውም፡፡ ማንነቱ እንዳይጐልበት ታደርገዋለህ እንጂ፡፡ በተቃራኒው ግን ለዕድገቱ እንቅፋት ሆነሃል። ይኸ አስከፊ ገጽታ ነው፡፡ ነገር ግን አዳጋችም አይደለም። መወገድ ይችላል። ምክንያቱም ለሆንከው መወገድ ማንነትህ ኃላፊነት እንደሌለብህ መመልከት ቀላልና ምክንያታዊ ነው፡፡ ተፈጥሮ አንተን ያበጃጀችህ አሁን ባለህበት ሁኔታ አይደለም፡፡


ያለ አንዳች ያለፈ ታሪክ መኖር ትችላላችሁ ካለፈ ታሪክ ጋር መኖር በእስር ቤት ተከርችሞብን እንደ መኖር ነው፡፡
:
ያለፈ ታሪካችሁ በበዛ መጠንም በታሪካችሁ የተነሳ የሚመጣባችሁ ሽክምም አብሮ ይበዛል፡፡ ያለፈ ታሪካችሁ በበዛ መጠን አሁን ላይ የመኖር አቅማችሁን እያጣችሁ ትመጣላችሁ አሁን ያላችሁበት ጊዜ ቃል ብቻ ነው።

ልታደርጉት አይቻላችሁም፡፡ እውነታም ሁልጊዜም ያለው በአሁን ላይ ነው፡፡ ያለፈ ነገር ትውስታ ብቻ የወደፊቱም ሐሳብ ብቻ ነው፡፡
══════••━━━••══════
ኦሾ/Osho

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.8K viewsedited  16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:26:06 አንድ ሰው ማሃቪራን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡-

እውነተኛ ቅዱስ ማን ነው?
እና ማን ነው ጥፋተኛ?

ምናልባት ጠያቂው በሃይማኖታዊ ጽሑፎች ውስጥ የሚሰጠውን ዝግጁ የሆነ መልስ ፈልጎ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን እንደ ማሃቪራ ያሉ ሰዎች ከራሳቸው ነባራዊ ግንዛቤ ነው የሚናገሩት። የተናገረው ነገር በጣም ያምራል። የሰጠው ፍቺ ልዩ ነው። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ምንም ተመሳሳይነት የለውም።

ማሃቪራ እንዲህ ብሏል፦
የነቃ ቅዱስ ነው።
የሚተኛው ኃጢአተኛ ነው።

ቀላል ፣ ግን በጣም አስፈላጊ…
"ንቃት" ያለው ብቸኛው ቅድስና ነው።እና ፤ንቃተ-ህሊና ማጣት ብቸኛው ኃጢአት ነው. ሌሎች ኃጢአቶች የሚመነጩት ከዚህ ካለማወቅ ነው። ሥሩን ይቁረጡ፤ ሥሩን ራሱ ይምቱ! ቅጠሉን አይቁረጡ።

ኦሾ
@Zephilosophy
@Zephilosophy
924 viewsedited  16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 00:20:40 ንቃት ከፍቅር የበለጠ ዋጋ አለውን?

ምንጭ ፦ የንቃት ጥበብ (ኦሾ)
ትርጉም ፦ ዳዊት መላኩ

የመጨረሻው ከፍታ ላይ መድረስ የሚቻለው ሁሉም ዋጋ የምንሰጣቸው ነገሮች እንደ እውነት፣ ፍቅር፣ ንቃት፣ ምሉዕነት የመሣሠሉት በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ሆነው ፀጥ ሲሉ ነው፡፡ የመጨረሻው ጥግ ላይ ስትደርሱ አንዱ ከአንዱ ሊበላለጡና ሊለያዩ አይችሉም፡፡ የተለያዩ መስለው የሚታዩን ባለመንቃት ውስጥ በሚገኘው የጨለማ ሸለቆ ወስጥ ስንገኝ ብቻ ነው፡፡ ሊለያዩ የሚችሉትም ከሌሎች ነገሮች ጋር ተቀይጠው ሲመረዙ ብቻ ነው፡፡ ያልተመረዙና የጠሩ ከሆኑ ግን አንድ ይሆናሉ፡፡ እጅግ በጣም እየጠሩ በመጡ ቁጥር ደግሞ እርስ በራሣቸው የተጠበቁና የማይነጣጠሉ ይሆናሉ፡፡ ለምሣሌ በርካታ የሆኑ ዋጋ የምንሰጣቸው ነገሮች በየደረጃው ተከፋፍለው ይገኛሉ። እያንዳንዳቸው ማህበረሰቡ ለሚያስቀምጥልን ከፍተኛው ደርጀ እንደመወጣጫ መሠላል በመሆን ያገለግላሉ፡፡ ፍቅር ማለት ሴሰኝነት ብቻ ሲሆን ዝቅተኛውን ዋጋ ይይዝና እስከ ገሃነም የሚለውን ደረጃ ያገኛል፡፡ ነገር ግን ፍቅር ፀሎት ሲሆን ከፍተኛውን የክብር ቦታ ያገኝና እስከ ገነት ጥግ ይደርሣል፡፡ ነገር ግን በእነዚህ በሁለቱ መካከል በርካታ የሆኑና በቀላሉ ሊታዩ የማይችሉ እርከኖች አሉ፡፡

ፍቅር ሴሰኝነት በሚሆን ጊዜ አንድ መቶኛውን ክፍል ሲይዝ ቀሪውን ዘጠና ዘጠኝ ከመቶውን የሚይዙት ምቀኝ ስጋዊ ፍላጎት የኩራት ስሜት፣ እንደግል ንብረት መቁጠር ፣ ብስጭት የመሣሠሉት ሌሎች ነገሮች ይሆናሉ፡፡ ይህ በይበልጥ አካላዊና ስሜታዊ እንጂ ከዚህ ባለፈ የሚሰማን ነገር የለውም። እንደውም ቆዳን ዘልቆ የማይገባና የታይታ ብቻ ነው ፡፡ ከፍ እያላችሁ ስትሄዱ ግን ነገሮች ጥልቀት እያገኙና አዲስ ገፅታን እያገኙ ይመጣሉ። ቁስአካላዊ ገፅታ የነበራችሁ ስነ-ልቦናዊ ገፅታ ይይዛሉ። ሥነ-ፍጥረታዊ ብቻ የነበሩት ነገሮች ወደ ስነ- ልቦናዊነት ይቀየራሉ፡፡ ስነ-ፍጥረትን ከሌሎች እንስሣት ጋር የምንጋራው ነገር ሲሆን ስነ-ልቦናዊት ግን ለሠዎች ብቻ የተሰጠ
ፀጋ ነው፡፡

ፍቅር ከፍ ወደአለ ደረጃ እያደገ ወይም ጥልቅ እየሆነ ሲመጣ መንፈሣዊ ይዘትን እየተላበሰና እየጎመራ ይመጣል፡፡ የእውነት አንዱ አካል ይሆናል ይህን ዓይነቱን እጅግ የጠራ ፍቅር የሚረዱት እንደ ቡድሃ፣ ክርሽና፣ እየሱስ መሆን የቻሉት ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ፍቅር መቶ በመቶ የጠራ ሲሆን ብቃትና በፍቅር፣ መካከል ምንም ልዩነት ልታወጡላቸው አትችሉም ሁለት ነገሮች መሆናቸው ያበቃለታል። በፍቅር እና በእግዚአብሔር መካከልም ምንም ልዩነት ልታገኙ አትችሉም ሁለትነት የሚባል ነገርም ስለማይኖራቸው አንድ ይሆናሉ፡፡ ‹እየሱስም እግዘአብሔር ፍቅር ነው› ያለው ለዚህ ነው፡፡ ሁለቱንም እንደ አንድ አድርጎ ነው ያስቀመጣቸው ይህ ንግግሩ ከጥልቅ አመለካከት የመነጨ ነው፡፡ ላይ ላዩን ሲመለከቱት ሁሉም ነገር ከሌላው የተነጠለና ለብቻው ያለ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ወደ መሃል እየገባችሁ ስትሄዱ ይህ ብዙነቱ እየቀለጠ፣ እየሟሸሸ ይመጣና አንድ ብቻ ሆኖ ይመጣል። በዚህ በመሃሉ ላይም ሁሉም ነገር አንድ ብቻ ሆኖ ይወጣል። በዚህ በመሃከሉ ላይም ሁሉም ነገር አንድ ነው፡፡ ስለዚህም ቪራንድራ የጠየከው ጥያቄ ልክ ሊሆን የሚችለው የፍቅርንና የንቃትን ከፍተኛ የጠራ ደረጃ ካልተረዳኸው ብቻ ነው፡፡ እንደ ኤቨረስት ተራራ ጫፍ ከላይ ያለውን የመጨረሻ ጥጉን በከፊል እንኳን ብታየው ኖሮ ይህ ጥያቄህ ፍፁም አላስፈላጊ በሆነብህ ነበር፡፡

ንቃት ከፍቅር የበለጠ ከፍተኛ ዋጋ አለው ወይ? ብለህ ጠይቀሃል ከፍተኛ እንዲሁም ዝቅተኛ የሚባልና የሆነ ነገር ጨርሶ የለም፡፡ እውነቱን ለመናገር ሁለት ዋጋ ያላቸው ነገሮች አብረው አይኖሩም፡፡ ያሉት ሁለት ጫፍ የሚያደርሱ ናቸው፡፡

የመጀመሪያው የንቃትና የተመስጦ መንገድ ሲሆን አሁን የዜን መንገድ እያልን የምንጠራው ማለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ የፍቅር መንገድ ነው፡፡ ይህኛው እራሱንና ጊዜውን ለፍቅር ለሚሰዋ የተሰጠና የበካቲስና የሱሬዎች መንገድ ነው። ስትጀምራቸው  አካባቢ እነዚህ ሁለት መንገዶች ይለያያሉ። መምረጥ ያለባችሁ እናንተ ናችሁ፡፡ ነገር ግን የትኛውንም መንገድ ይዛችሁ ብትጓዙ የሚያደርሷችሁ ከፍተኛ ቦታ ተመሣሣይ ነው፡፡ ከዚህ የመጨረሻው ከፍተኛ ቦታ ላይ ለመድረስ ስትቃረቡ ደግሞ ሌላውን መንገድ ተከትለው የመጡት ተጓዦች ወደ እናንተ በጣም እየቀረቡ ስለሚመጡ ያስደንቃችኋል፡፡ ቀስ በቀስም እነዚህ ሁለት የነበሩ መንገዶች እርስ በርስ መደራረብ ይጀምራሉ፡፡ ከዚያ በኋላ የመጨረሻው እውነት ላይ አንድ ላይ በመሆን ይደርሳሉ፡፡

የንቃትን መንገድ ተከትሎ የሄደ ሰው በንቃቱ አማኝነት ፍቅርን ያገኛል። ይህ ከንቃቱ እንደሚገኝ ተረፈ ምርት ይሆናል፡፡ ፍቅር ጥላ ሆኖ ይከተለዋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የፍቅርን መንገድ ተከትሎ የተጓዘ ሰው በፍቅር አማካኝነት ንቃት ያገኛል፡፡ ይህኛውም ለእሱ በፍቅር አማካኝነት የሚያገኘው ተጨማሪ ነገር በመሆን ፍቅርን እንደጥላ ተከትሎ የሚመጣ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁለቱ የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው፡፡

ማስታወስ ያለባችሁ ንቃታችሁ ፍቅር አልባ ከሆነ አሁንም ገና ያልጠራ መሆኑን ነው 100% የጥራት ደረጃው ላይ ገና አልደረሰም ማለት ነው፡፡ እውነት ለመናገር ይህ ንቃት ሊባል አይችልም፡፡ ምናልባትም በውስጡ ያለመንቃት ሣይቀየጥበት አይቀርም፡፡የጠራ ብርሃን ስለሌለው በውስጣችሁ የተወሠኑ የጨለማ ኪሶች ፈጥራል። እነዚህም አሁንም ድረስ እየተንቀሳቀሱ፣ ተፅዕኖ እያደረጉባችሁ እየጨቆኗችሁ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ይህ ፍቅር እንደ ፀሎት ከፍ ያለ ሣይሆን እጅግ የዘቀጠና ለሥጋዊ ስሜት ያደላ ነው፡፡

ስለዚህ መሥፈርት የምታስቀምጡ ከሆነ የንቃትን መንገድ በምትከተሉ ጊዜ መስፈርታችሁ ፍቅር ይሁን ይህ ንቃታችሁ በድንገት ፍቅር በመሆን ሲጎመራና ሲያብብ በትክክልም ንቃትን የተላበሳችሁ ትሆናላችሁ፡፡ ሣማዲንም አሣካችሁ ማለት ነው፡፡

በተመሣሣይ መንገድ የፍቅርን መንገድ ተከትላችሁ ስትጓዙ መሥፈርታችሁን ንቃትን በማግኘት ላይ አድርጉት ሰረ መሰረታችሁ አድርጋችሁ ያዙት፡፡ እናም በድንገት ከየት እንደመጣ የማታውቁት የመንቃት፣ የማወቅ ነበልባል ፍቅራችሁን ማዕከል አድርጎ ሲንቀለቀል ትሰሙታላችሁ፡፡ ይህን በደንብ እወቁት፣ ተረዱት....ተደሰቱበት። ምክንያቱም ቤታችሁ ደርሳችኋልና።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
290 views21:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 20:57:32 ሁሉንም ጠይቅ - ሶቅራጠስ

ስለሆነ ነገር ጠይቀህ ምላሽ ሳታገኝ ስትቀር ምን ይሰማሃል? ሌሎች ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ለማወቅ ፈልገህ ታውቃለህ? ለጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስለማግኘትህ ትጨነቃለህ? በቀን ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ እንደ ቂል “አላውቅም” ብለህ ትመልሳለህ?
ለሶቅራጥስ “አለማወቅን ማወቅ” የፍልስፍና መጀመሪያ ነው፡፡ አለማወቃችንን ሳናውቅ የእውቀትን መንገድ መጀመር አንችልም፡፡

በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ “አላውቅም” ማለት የመሃይም ምልክት ሆኖ ቆይቷል። ልክ ኃጢአትን እንደሰራ ሰውም ትቆጠራለህ፤ ችግር እንዳለብህም ይታሰባል። መድኃኒትን ፍለጋም ወደ መምህራን ወይም አዋቂ ወደተባሉ ሰዎች እንድትሄድ ይነገርሃል። ለማህበረሰቡ አለማወቅህን በአደባባይ በኩራት የምትለፍፈው ሳይሆን፣ መሞላት እንዳለበት ጉድለትህ ነው፡፡

ሆኖም ሁሉም አለማወቆች መጥፎ አይደሉም፡፡ አንድ ሰውም ሁሉን ነገር ማወቅ እንደማይችል እናውቃለን፡፡ ብዙ ቋንቋ የሚናገር ሰው ስንመለከት ይደንቀናል፤ ብዙ ሺ መጽሐፍትን ያነበበ ሰውም ይገርመናል። ሆኖም አስር ቋንቋ ብትናገር፣ መቶ ሺ መጽሐፍትን ብታነብ እንኳ፣ ይህ ሁሉ ከዓለም የእውቀት ባህር ውስጥ ጠብታን ብቻ የመቅመስ ያህል ነው፡፡ ሁላችንም በሆነ መንገድ የማናውቅ መኃይማን ነን። ዶክተሩ አይሮፕላን አያበርም፤ መሐንዲሱ ዋሽንት መንፋት አይችልም... እናም አለማወቅ በሽታ አይደለም፡፡

ለሶቅራጥስ አለማወቅ እንደ ሰይጣን ከእኛ የምናርቀው መጥፎ ነገር ብቻ አይደለም፤ ይልቁኑ በስርዓት ከተጠቀምንበት ወደ እውነት እና ጥበብ የመድረሻ መንገድ ነው ይለናል፡፡ ዛሬ ላይም ይህ ፍልስፍና ሶቅራጥሳዊ አላዋቂነት (Socratic ignorance) ተብሎ ይጠራል።

ለሶቅራጥስ ሁለት አይነት አላዋቂነቶች አሉ።

1.#አለማወቅን_አለማወቅ።
ይህ በሕይወትህ ላይ ምን እንደማታውቅ ሳታውቅ መኖር ማለት ነው። እነዚህ ራሳቸውን አይጠይቁም አውቃለሁ አላውቅም ብለውም አይመረምሩም፡፡ ሕይወታቸውንም በእንቅልፍ ውስጥ እንዳለ ሰው፣ ሁሉንም አውቃለሁ እያሉ ይኖራሉ፡፡ ሃሳባቸውን ለመመርመር ቆም ብለው አያስቡም፡፡

2.ሶቅራጥሳዊ አለማወቅ ።
ይህ ከእንቅልፋችን ነቅተን እና አይናችንን ገልጠን መጠየቅ ስንጀምር ያለውን ጊዜ ያመለክታል። የምናውቀውን ሁሉ እንጠረጥራለን፡፡ የአቴና ሰዎች ሶቅራጥስን ከብቶችን በሚነድፍ ዝንብ ይወክሉታል። (እሸሽ... ቢሉትም ተመልሶ ሊናከስ የሚመጣ ዝንብ፡፡) በአቴና ጎዳናዎች ላይ እየዞረ ያገኘውን ሰው ሁሉ በጥያቄ ያጣድፋል፡፡ ቀኑን ሙሉም እንደ ዝንብ ዝዝዝዝዝ... ሲል ይውላል። ለዚህም ይሆናል የአቴና ሰዎች ሊገድሉት የተጣደፉት፡፡

ሁለተኛውን አለማወቅ ሶቅራጥስ የተቀደሰ አለማወቅ ይለዋል፡፡ ይህ ነው ሁሉም ፈላስፋዎች፣ ሁሉም መልካም ሰዎች ሊጓዙበት የሚገባው መንገድ፡፡ በዚህ መንገድ መመርመር እና መጠየቅ እንጂ እርግጠኛነት የለም፤ እኔም አንተም ማንም ምንም አያውቅም። ይህ ወደ እውነት መዳረሻ መንገድ እንጂ እውቀት ራሱ አይደለም፡፡ የምናውቃት ጥቂት ናት፤ ከምናውቀውም የሆነ ጊዜ፣ የሆነ ቦታ ላይ ስህተት መኖሩን እንረዳለን፡፡
ሶቅራጥስ በዚህ አባባሉ ይታወቃል፤ “Unexamined life is not worth living' (ያልተመረመር ሕይወት ሊኖሩት ያልተገባ ነው።)


ምንጭ ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት - ፍሉይ አለም

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.1K viewsedited  17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 00:21:58 ከስጋዊ ወደ ተፈጥሯዊ

ምንጭ ፦ የህይወት ኬሚስትሪ (ሳድጉሩ)
ትርጉም ፦ ሀኒም ኤልያስ

ባዮሎጂን ቅዱስም ሆነ ቆሻሻ ማድረግ የለብህም፣ እርሱ የሕይወት መሳሪያ ነው፡፡

ህልውና በማይገለጥ እና በተገለጠው መካከል ያለ ጭፈራ ነው። በሚገለጥበት ቅጽበት ሁለትነት፣ በማይገለጥበት ጊዜ ደግሞ አንድነት አለ። ምንም እንኳን አንድነት የፍጥረት መሠረታዊ ነገር ቢሆንም፣ ሁለትነት ገጽታን፣ ዲዛይንና ቀለምን ያመጣል፡፡ ዛሬ እንደ ሕይወት የምትመለከታቸው የተለያዩ መገለጫዎች በመሠረታዊነት በሁለትነት ውስጥ የተተከሉ ናቸው። ሁለት ስለሆኑ ብዙ መገለጫዎች አሏቸው- ብርሃንና ጨለማ፣ ወንድና ሴት፣ ሕይወትና ሞት... ወዘተ። አንድ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ ህልውና ብቻ ይሆን ነበር። ሁለት ከሆኑ በኋላ የሕይወት ጨዋታ ይጀምራል።

አንድ ጊዜ ሁለትነት ሲጀምር፣ ወሲብ ይጀምራል። ወሲብ ብለን የምንጠራው አንድ ለመሆን የሚጥሩትን የዚህን ሁለትነት ሁለት ክፍሎች ነው:: በእነዚህ የሁለትዮሽ ግንኙነት ሂደት ውስጥ፣ ተፈጥሮ ልታሟላቸው የምትፈልጋቸው እንደ መራባትና የዝርያ መቀጠል ያሉ ተግባራትም አሉ፡፡

የአካል አንድነትን በተመለከተ ምንም ብታደርግ ሥጋዊ አካላት ሁልጊዜ ሁለት ሆነው እንደሚቀሩ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ሁለት ሰዎች በአንድነት ስሜት የሚመጡት ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ከዚያ ይለያያሉ፡፡ ፍቺ ካልለያቸው፣ ሞት ይለያቸዋል፤ ይህ ደግሞ መከሰቱ
አይቀርም፡፡

ወሲብ ብለን የምንጠቅሰው ጉዳይ አጠቃላይ ሂደት ሁለት ተቃራኒዎች አንድ ለመሆን የሚሞክሩበት ነው᎓᎓ የአንተ ግለሰባዊ ማንነት ማለት በአንተ አእምሯዊ ማዕቀፍ ውስጥ በአንተ መውደድና አለመውደድ፣ ማፍቀርና መጥላት ወዘተ መልክ ያስቀመጥከው የውሸት ድንበር ብቻ ሳይሆን፣ በራስህ አካላዊ ሰውነት ድንበር ውስጥም መታሰር ማለት ነው፡፡ ሆን ብለህ ላታውቀው ትችላለህ፤ ነገር ግን በአንተ ውስጥ ያለው ሕይወት ነፃ ለመውጣትና ከእነዚህ ድንበሮች ባሻገር ለመሄድ የሚጓጓ ነው፡፡ የአእምሮ ድንበሮችህን ለማቋረጥ ስትፈልግ ግን፣ ኮስተር ያለ ውይይት ለማድረግ ወይም መጽሐፍ ለማንበብ፣ አልኮል ለመጠጣት፣ አደንዛዥ እጽ ለመውሰድ ወይም አንድ አስፈሪ ነገር ለማድረግ ልትናፍቅ ትችላለህ፡፡ አካላዊ ድንበሮችን ለማቋረጥ ደግሞ ራስህን መበሳት ወይም መነቀስ፣ ፀጉርህን ማቅለም ወይም የድሮውን የወሲብ መንገድ መጠቀም ትፈልግ ይሆናል።

የወሲብ ፍላጎት በጣም ጥሩ ቢሆንም ሰዎችን አንድ የማድረግ ዘዴው ግን ተስፋ የለሽ ነው፡፡ ወሲብ ደስታ ስላለበት፣ ሰዎች እርስ በርስ እንዲሳሳቡ ያነሳሳል እንጂ በፍጹም አንድነትን አያመጣም:: ለምሳሌ “ተመሳሳይ ነገሮችን እንወዳለን፣ አንድ አይነት አይስክሬም እንወዳለን፣ ሁለታችንም ቆንጆዎች ነን፣ ሁለታችንም ፊልም እንወዳለንና ሁለታችንም አንድ አይነት መጽሐፍ እንወዳለን” ወዘተ የሚሉ አይነት የጋራ አቋም ለማግኘት ትሞክራለህ፡፡ እንደዚህ ስታደርግ እርስ በርስ ለመሳሳብና ለመገናኘት የምትሞክረው በሌሎች የስሜታዊነትና የማሰብ ዘርፎች ስለሚሆን መቼም ቢሆን አንድነትን አያመጣም፡፡ አንድ መሆን እንደማትችል እስካልተረዳህ ድረስ ደግሞ መደሰትን አትማርም፡፡

በሰው ዘር ውስጥ 'ወንድ' እና 'ሴት' ብለን የምንጠራቸው እነዚህ ሁለት ኃይሎች ሁልጊዜ አንድ ላይ ለመሆን ከመናፈቅ በስተቀር ተቃራኒዎች ናቸው። እነርሱ በአንድ ጊዜ ወዳጆችም፣ ጠላቶችም ናቸው። የሚያመሳስሏቸውን ነገሮች የሚፈልጉ ከሆነ፣ ያላቸው የጋራ ነገር በጣም ትንሽ ይመስላል፤ የተቃራኒዎች መሳሳብ ግን ሁልጊዜም አለ፡፡ ወሲብ ተፈጥሯዊና በሰውነት ውስጥ ያለ ነው፡፡ ወሲባዊነት ግን አንተ የፈጠርከውና ስነ ልቦናዊ ነው። ወሲብ በአካል ውስጥ ከሆነ፣ መልካም ነው፤ ቆንጆ ነው፡፡ ወደ አእምሮህ ‌ በገባ ቅጽበት ጠማማ ይሆናል፤ ምክንያቱም ከአእምሮህ ጋር ምንም ሥራ የለውም። ወሲብ የአንተ ትንሽ ገፅታ ቢሆንም፣ ግን ዛሬ በጣም ትልቅ ሆኗል። ለብዙዎች እንዲያውም- እሱ ራሱ ሕይወት ሆኗል፡፡

ዘመናዊ ማህበረሰቦችን ብትመለከት፣ ምናልባት ዘጠና በመቶው የሰው ጉልበት የሚውለው ወሲብን ለመከታተል ወይም ለማስወገድ ነው፡፡ ወሲብ ተፈጥሮ ለመራባት የፈጠረችው ዘዴ ነው᎓᎓ እኛ ግን ይህንን አካላዊ ሂደት ብዙ ያልሆነውን ነገር ልናደርገው እየሞከርን ነው፡፡ ይህ የተቃራኒዎች መሳሳብ ባይኖር ኖሮ ዝርያ ይጠፋ ነበር። አሁን ግን ወንድና ሴት ሁለት የተለያዩ ዝርያዎች እንደሆኑ አድርገን ለይተናል። በፕላኔታችን ላይ እንደ ሰው ከወሲብ ጋር በተገናኘ እንደዚህ አይነት ችግር ያለበት ሌላ ፍጡር የለም:: እንስሳትን በተመለከተ፣ በሆነ ጊዜ ፍላጎቱ በአካላቸው ውስጥ ይከሰታል፤ አለበለዚያ ከእርሱ ነፃ ናቸው፡፡ ሰዎችን በተመለከተ ግን ሁልጊዜ በአእምሮአቸው ላይ ነው። ይህ የሆነበት አንዱ ምክንያት ቀደም ባሉት ጊዜያት ብዙ እምነቶች ቀለል ያለ አካላዊ ሂደት የሆነውን ይህንን ፍላጎት እጅግ አስቀያሚ እንደሆነ እስኪቆጠር ድረስ መካዳቸው ነው፡፡ የሰውን ልጅ ባዮሎጂ እንኳን መቀበል ስላልቻልን ከሥነ ሕይወታዊ ሂደት ውሱንነት ባሻገር ከመመልከት ይልቅ ለመካድ ሞክረናል።

ኃይማኖት ማለት ነፃነት ማለት ነው፣ አይደል? ታዲያ ባዮሎጂን እንኳን መቀበል ካልቻልን እንዴት ነፃነት ሊኖር ይችላል? በባዮሎጂ ላይ ችግር ባይኖረን ኖሮ፣ ሁሉም ሰው ያለው ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ ያውቅ ነበር:: አንድ ሰው ወንድ ሆነ ሴት ችግሩ ምንድን ነው? የሴቶች አጠቃላይ ጭቆና የሚጀምረው በወንድና በሴት መካከል ያለውን አካላዊ ልዩነት መቀበል በማትችልበት ጊዜ ነው፡፡

ባዮሎጂ አንተ የተፈጠርክበት የሕይወት መሳሪያ በመሆኑ እርሱን ቅዱስም ሆነ ቆሻሻ ማድረግ የለብህም፡፡ ባዮሎጂን ሳታጋጊጠው ወይም አስቀያሚ ሳታደርገው እንዴት እንደምትኖር ካወቅክ፣ የራሱ የሆነ ውበት ያለው ነው፡፡

አሁን ራስህን ሰው' ብለህ ለይተህ የምታስብ ከሆነ፣ ሃሳብህና ስሜትህ ሁሉ ከዚያ ማንነት የሚመነጭ ይሆናል። ወይም ራስህን በዜግነትህ ወይም በዘርህ ከለየህ፣ ሀሳብህና ስሜትህ ሁሉ ከእነዚያ ማንነቶች የሚፈስስ ይሆናል፡፡ ምንም አይነት ሀሳቦችና ስሜቶች ቢኖሩህ፣ እነርሱ የሆነ ጭፍን ጥላቻን የሚወክሉ ናቸው፡፡ አእምሮህ ራሱ የተወሰነ የጭፍን ጥላቻ አይነት ነው:: ራስህን በምንም ነገር የለየህ ሁን፣ ሞት በመጣ ጊዜ ሁሉም ይጠፋል፡፡ አእምሮ ካለህ አሁን ትማራለህ፤ አሁን ካልተማርክ ሞት ያስተምርሃል፤ ስለዚያ አትጠራጠር፡፡ አንድ ሰው ራሱን እንደ ወንድ ወይም እንደ ሴት ካልተመለከተ፣ የማሰብ ችሎታውን በማናቸውም መለያዎች ማለትም በአካል፣ በቤተሰብ፣ በችሎታ፣ በማህበረሰብ፣ በጎሳ፣ በእምነት፣ በዘር፣ በብሔር፣ ዝርያና ሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ማንነቶች ካልለየ፣ ወደ መጨረሻ ተፈጥሮው ይሄዳል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.2K views21:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 00:41:49 .... ካለፈው የቀጠለ

ስለዚህ ራሳቸውን ከሚያጠፉ ሰዎች መካከል 20 በመቶ የሚሆኑት ሕይወት በሆነ መንገድ ጨካኝ ስለነበረባቸውና በዚህ ዓለም ላይ እየተሰቃዩ የነበሩ በመሆናቸው ሊታዘንላቸው ይገባል፡፡ ካለምንም ምክንያት ሕይወታቸውን በዚህ መንገድ ማጥፋት የሚፈልጉ ሰዎች በመቶኛ የሚቆጠሩ ጥቂት ሰዎችም አሉ። ዛሬ ሌላ የሚሠሩት ነገር ስለሌላቸው ሕይወታቸውን ሊያቆሙት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ፡፡ እንደዚህ ያሉ ሰዎች ምንም ዓይነት ስቃይ፣ ችግር ወይም ድብርት የለባቸውም፤ ግን በቃ ዛሬ የመሞት ስሜት ይሰማቸዋል። ከ2-5 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች እንደዚህ አይነት ዝንባሌ እንዳላቸው በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ:: በመንፈሳዊ መንገድ ላይ ያሉና መንገዱን ማቆም እንዳለባቸው የሚያስቡ ሰዎች ደግሞ አሉ። አንድ ሰው በመንፈሳዊ እድገት ላይ በሚሆንበት ጊዜ፣ የማሰብ ችሎታው በእርሱ ላይ እየተከሰተ ያለውን የተሞክሮ ጥልቀት መረዳት ስለማይችል፣ እንደዚህ ያለ ቅጽበት ይመጣል፡፡

ከአካላዊ ሰውነት ባሻገር ላሉት ጥቂት ተሞክሮዎች፣ አእምሮህ “ለመሞት ዝግጁ ነኝ' ማለት ሊጀምር ይችላል። ግን ለመሞት ዝግጁ አይደለህም፡፡ ከአካላዊነት በላይ በሆነ የተሞክሮ ልኬት ሞት ነው ብለህ ታስባለህ᎓᎓ ነገር ግን አጠቃላይ የህልውና ስፋት እንዳለና ይህም ከአካላዊ ሰውነት በላይ፣ ለሙታን ሳይሆን ለህያዋን እንደሆነ አልገባህም፡፡ ሆኖም “እንደ አለመታደል ሆኖ ወደዚያ ግዛት የሚገቡት አብዛኞቹ በሞት ብቻ መሆኑ የተለየ ጉዳይ ነው:: የሰው ልጅ የማሰብ ባህሪይ “ይህ ሕይወት ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል? ሞት መሆን አለበት፡፡” የሚል ስለሆነ እነዚህ ሰዎች ሞት እንደሚገባቸው ያስባሉ፡፡

ሕይወት ለአንተ በቂ ትርጉም ከሌለው፣ አንተ በቂ ስሜት ስለሌለህ መሆኑን ማወቅ አለብህ። ነገር ግን በሕይወት ትርጉም አጣሁ የሚለውን ከማየት ይልቅ ሕይወት ትርጉም እንደሌለው ለማሳየት መሞከር አይገባም፡፡

ራስን የማጥፋት ዝንባሌ ስላላቸው ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ደግሞ አሉ። እነዚህ ሰዎች፣ ይህንን ለማድረግ ምንም ውጫዊ ማነቃቂያዎች ባይኖሩም ሕይወትን ማቋረጥ ይፈልጋሉ፡፡ ካስተዋልክ ሁልጊዜም ምንም ብታደርግ ራሳቸውን ከማጥፋት የማይመለሱ ጥቂት ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች የቱንም ያህል ብትመክራቸው ወይም ማንኛውንም ዓይነት ህክምና ብታደርግላቸው ደጋግመው ራሳቸውን ለማጥፋት ወደ ማሰብ መመለሳቸው አይቀርም፡፡

ለተቀሩት ሰዎች ደግሞ የራሳቸውን ፍላጎታቸው በመሠረታዊነት የመነጨው ‌ ከድንቁርና ነው። ብዙውን ሕይወት የማጥፋት ጊዜ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በጣም የሚታገሉ ሰዎች ራሳቸውን አያጠፉም፡፡ እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳ ሺ ነገሮች እነርሱ በሚፈልጉት መንገድ ባይሄዱላቸውም፣ የበለጠ ጠንክረው ይሰራሉ እንጂ ራሳቸውን አያጠፉም:: አንድ ቦታ ላይ ተቀምጠው ሕይወት እነርሱ በሚፈልጉት መንገድ እየሄደ እንዳልሆነ የሚያስቡ ሰዎች ግን የሚያስቡት ይህንን ብቻ በመሆኑ ራሳቸውን ያጠፋሉ። አንተ ግን ምናልባት በሕይወትህ ውስጥ ነገሮች እንደምትፈልገው ባይሄዱልህም፣ በዚያ ውስጥ አትኑር፤ ምክንያቱም የምትሰራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ነገሮች አሉ፡፡ በአንድ ክፍል ውስጥ ብቻህን ተቀምጠህ ነገሮች ምን ያህል በአንተ መንገድ እንዳልሆኑ ማሰብ ከቀጠልክ ግን፣ ሕይወትህን ማጥፋት መፈለግህ አይቀርም፡፡

ሆኖም አብዛኛዎቹ ሰዎች ሕይወታቸውን ለማጥፋት የሚፈልጉበት ነገር ድራማ ነው:: ሁልጊዜ ራስን የመግደል ስሜት የሚሰማህ ሕይወት አንተ በምትፈልገው መንገድ ስላልሄደ ብቻ ነው፡፡ ዛሬ ሕይወት አንተ በምትፈልገው መንገድ ካልሄደች ሕይወትህን ማጥፋት ትፈልጋለህ። ነገ ጠዋት ነገሮች ትንሽ የተሻሉ ከሆኑ ደግሞ ለወደፊት እቅድ ማውጣት ትጀምራለህ:: ነገ ጠዋት የሆነ ነገር በትክክል እየሄደ ከሆነ፣ መኖር ትፈልጋለህ፤ ሶስተኛውን ልጅህን ለመውለድና ረጅም ጊዜ ለመኖር ትፈልጋለህ። ሁሉም ነገር መጥፎ በሚመስልበት ጊዜ ደግሞ ራስህን ስለ ማጥፋት ታስባለህ። ይህ የህልውና መሰረት የሌለው፣ በአእምሮህ ውስጥ እየተጫወትክ ያለኸው ራስን የሚያጠፋ መጥፎ ጨዋታ ነው፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy
357 views21:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 00:09:12 ራስን ማጥፋት

ምንጭ ፦ የህይወት ኬሚስትሪ (ሳድጉሩ)
ትርጉም ፦ ሀኒም ኤልያስ

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የእኛ ትውልድ ከእኛ ቀድመው ከነበሩት ትውልዶች የበለጠ ምቾት ያለው ቢሆንም እንኳ፣ ራስን ማጥፋት እያደገ የመጣ የዘመናችን ወረርሽኝ የሆነ አንዱ የሞት ምድብ ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከፍተኛ · ቁጥር ያለው ህዝብ በሕይወቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ ራስን ስለማጥፋት ያስባል። ከእነዚህም መካከል በመቶኛ ሲሰላ ትንሽ የማይባሉ ሰዎች ቢያንስ አንድ ጊዜ ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረዋል። በአሁኑ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በየዓመቱ በነፍስ ግድያ ወንጀልና በጦርነት ከሚገደሉት ሰዎች ይልቅ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር ይበልጣል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመኪና አደጋ ከሚሞቱት ሰዎች ራሳቸውን በማጥፋት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ይበልጣል:: ይህ በሰው ልጅ ላይ የተሳሳተ ከባድ ነገር መኖሩን አመላካች ነው::

ራስን ለማጥፋት ምንም ጥሩ ወይም መጥፎ ምክንያት የለም፡፡ የሚያስፈልገው ምክንያት ብቻ ነው:: አንተ ከፈለግክ ማንኛውንም ምክንያት ራስን ለማጥፋት በበቂ ሁኔታ ጥሩ ማድረግ ትችላለህ። ከፈለግክ ዛሬ ከጠዋት እስከ ማታ ብታስብ፣ ለምን መኖር እንደሌለብህ መቶ ምክንያቶች ማግኘት ትችላለህ። እዚህ ላይ ምክንያቱ ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ የመሆኑ ጥያቄ ሳይሆን፣ ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ ምክንያት በማግኘታቸው ብቻ ያንን እንዲያደርጉ በበቂ ሁኔታ የሚገፋፋቸው ነገር መኖሩ ነው:: ለአብዛኛዎቹ ሰዎች ራስን የማጥፋት ስሜት የሚሰማቸው ሕይወት በሚፈልጉት መንገድ እየሄደ ባለመሆኑ ነው፡፡ ከህክምና ምክንያቶች በስተቀር የተቀረው ራስን የማጥፋት ስሜት የሚመጣው ከእውነታው በራቁ ተስፋዎች ምክንያት ነው። በዚህ ተፈጥሮ ውስጥ አንተ በጣም ትንሽ ነጥብ ነህ።

ራስህን ከአጠቃላይ ፍጥረት አኳያ ብትመለከት ምንም ነህ። ምንም መሆንህን ከተረዳህ ደግሞ ነገሮች አሁን ባሉበት ሁኔታ እየተከሰቱ በመሆናቸው ማድረግ ያለብህ መደሰት ብቻ እንደሆነ ታውቃለህ፡፡ ምንም ባለመሆንህ፣ አንዱን ነገር ከሌላው ለይተህ የማታውቅ በመሆንህ፣ በዚች ፕላኔት ላይ በመሆንህ፣ በዚህ ግዙፍ ህልውና ውስጥ ቢያንስ የምትተነፍስ፣ ልብህ የሚመታ፣ የምትኖር በመሆንህና ሁሉም ነገር በሚገባ እየሄደ በመሆኑ እጅግ ትደሰታለህ። ምንም ነገር አታውቅም፣ ልትቆጣጠረውም አትችልም፣ ልታስተዳድረውም አትችልም... ግን በትክክል እየሄደ ነው፡፡ ስለዚህ የሕይወትን እውነተኛ አገባብ ከተረዳህ፣ በሕይወት በመኖርህ ብቻ እጅግ ትደሰታለህ።

በአንድ ወቅት አንድ የሽያጭ ሰራተኛ የሚያስተዋውቀውን ምርት ገና እየተገነቡ ላሉ አዳዲስ ቤቶች ለመሸጥ ወሰነ፡፡ ገና አዲስ መንደር በመሆኑ ሌላ የሽያጭ ሰራተኛ ወደዚያ እንዳልሄደ ስላሰበ የመጀመሪያ በመሆኑ በጣም ተደስቷል፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ ወደተመለከተው ቤት ተጠግቶ በሩን ሲያንኳኳ አንዲት ሴት ከፈተችለት፡፡ ሰውዬው፣ ለሴትየዋ የመናገር እድል እንኳን ሳይሰጣት፣ ወደ ቤቷ ገባና ከቦርሳው ውስጥ የከብቶች ፍግ አውጥቶ ሙሉ በሙሉ ሴትየዋ ባነጠፈችው አዲስ ምንጣፍ ላይ በተነ፤ ከዚያ “እነሆ እጅግ አስደናቂ በኤሌክትሪክ የሚሰራ የምንጣፍ ማጽጃ አለኝ፡፡ አንዲት ቅንጣት ቆሻሻም ሆነ ሽታ ሳይኖረው ምንጣፍሽን በዚህ መሳሪያ አጸዳልሻለሁ፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻልኩ፣ እያንዳንዱን ቅንጣት ቆሻሻ ራሴ እበላዋለሁ፡፡” አላት፡፡ ሴትየዋም በመገረም እየተመለከተችው፣ “እንደዚያ ከሆነ የምትበላበት የቲማቲም ስጎ ላምጣልህ፣ ምክንያቱም ቤታችን ውስጥ ገና ኤሌክትሪክ አልተገጠመልንም፡፡” አለችው፡፡

በሕይወትህ ውስጥ መጥፎ ግንኙነት እንዳለህ ከተሰማህና በዚያ ምክንያት ራስህን ለማጥፋት ከወሰንክ፣ የሚያስፈልግህ የቲማቲም ስጎ ብቻ ነው፡፡ ፍግ መብላት ብቻ የመሞት ያህል ይሰማሀል። ስለዚህ በቲማቲም ስጎ ሲሆን ደግሞ የተሻለ ጣዕም ይኖረዋል፤ እና ለመኖር ድንገት ትፈልጋለህ። ህይወት በሚፈልጉት መንገድ ያልሄደችላቸው ብዙ ሰዎች አሉ፤ ነገር ግን ነገ ነገሮች የተሻሉ ይሆናሉ ብለው ተስፋ ስለሚያደርጉ ራሳቸውን ስለማጥፋት አያስቡም፡፡ በመንገድ ላይ የሚኖር አንድ ምስኪን፣ የሎተሪ ቲኬት ገዝቶ ዕጣው እስኪወጣ ቢያንስ አንድ ወር መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ ሎተሪውን ሲያሸንፍ እንደ ንጉስ ለመኖር ተስፋ ያደርጋል፡፡ ዕጣው ሳይወጣለት ይቀርና ቀጣዩን ሎተሪ ደግሞ ተስፋ ያደርጋል፡፡ በዚህ መንገድ ይቀጥላል እንጂ ራሱን ለማጥፋት አያስብም፡፡ ለሀብታም ሰው ግን ሎተሪው የወጣለት በመሆኑ፣ ምንም ልዩነት የለውም፡፡ ስለዚህ ጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ይሰማዋል፡፡ አንድ ሰው ሆነ ብሎ ራስን ማጥፋት አይፈልግም፣ ስለሞት የሚያስበው የሕይወት ተሞክሮው ደስ የማያሰኝ ሲሆንበት ነው፡፡ የሕይወት ተሞክሮህን ጣፋጭ እንዲሆን ካላደረግክ፣ ስለ ሕይወት ሳይሆን ስለ ሞት የምታስብ ትሆናለህ፡፡

በመሠረቱ ሰዎች በሆነ መንገድ ሕይወትን እንዴት እንደሚይዙ ባለማወቃቸው ራሳቸውን ማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ደግሞ በሕይወት ውስጥ ላለ ጊዜያዊ ሁኔታ ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት እንደመፈለግ ነው:: ይህ ማለት ሰዎች ስሜታቸውን፣ ሀሳባቸውን፣ የአካል ጉዳታቸውን፣ የገንዘብ ወይም የቤተሰብ ሁኔታቸውን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው አያውቁም ወይም አንድ ሌላ የማያውቁት ነገር አለ ማለት ነው፡፡ በእንደዚያ አይነት ሁኔታ ውስጥ ስትታሰር በአንተ ግንዛቤ የዓለም ፍጻሜ የሆነ ሊመስልህ ይችላል። በመሰረቱ ችግሩ የሕይወትህን የተወሰነ ገጽታ እንዴት መያዝ እንዳለብህ አለማወቅህ ሲሆን፣ ምርጥ የሆነው እርምጃ ሕይወትህን ማጥፋት ይመስልሃል። ይህ ግን ስለ ሕይወት ተፈጥሮ አለማወቅ ነው::

በእኔ እይታ 5 ከመቶ ያህሉ ሰዎች ራሳቸውን የሚያጠፉት፣ እንዴት እንደሚይዙት በማያውቁት በማይድን በሽታ በመያዛቸው ምክንያት ሲሆን፤ ህመሙ በጣም የሚያሰቃይና አሰቃቂ ስለሆነ መሞት የተሻለ እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ ሌሎቹ ከ2-3 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ራሳቸውን የሚያጠፉት፣ በአስፈሪ ሁኔታዎች ውስጥ በመያዛቸው ነው፤ በጦርነት ቀጠና ውስጥ ወይም በጠላት እጅ ወይም ከመጠን በላይ በሚበዘብዙበት ቦታ ላይ በመሆናቸውና ከዚያ ለመውጣት ምንም መንገድ ስለሌላቸው ነው፡፡ በገንዘብ በሚመራ ማህበረሰብ ውስጥ እንደታሰሩ ስለሚሰማቸው፣ በገንዘብ ምክንያት ራሳቸውን የሚያጠፉ ከ10-15 በመቶ የሚሆኑ ሌሎች ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ቤተሰብ ሊኖራቸው ይችላል፤ ከዚያ ገንዘባቸውን ሲያጡና መጨረሻቸው ጎዳና ላይ በአሰቃቂ ሕይወት መኖር ሲሆን፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም። ለምግብና ለኑሮ የሚለምን ቤት አልባ ሰው የመሆናቸውን ውርደት መሸከም ስለማይችሉ ራሳቸውን ያጠፋሉ፡፡

ይቀጥላል

@Zephilosophy
@Zephilosophy
434 viewsedited  21:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ