Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Freeseminar
Cloudbridge
Traininginstitute
Cryptocurrency
Аирдроп
Tikvahtechteam
Techdailly
Attention
Cbdc
Cryptocurrencies
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.51K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 266

2022-05-13 16:01:01
የመጀመሪያ መኪናችሁን ይሁን አስረኛ መኪናችሁንም ቢሆን ለመግዛት ያሰቡት፤ ያገለገሉ መኪና መሸጫ ቻናሎች የመኪና ዋጋ ማጣራት እና መግዛት ሂደቱን ያቀለዋል። ነገር ግን የመኪና መሸጫ ቻናሎች መኪና መግዛት የሚፈልጉትን ብቻ ሳይሆን የሚጠቅመው ለመኪና ባለቤቶችም መኪናቸውን ለመሸጥ ሲያስቡ ገዢ እንዲያገኙ ይጠቅማል።

ለገዢዎች የሚፈልጉትን መኪና በማቅረብ ለሻጭ ደግሞ ገዢ(ብዙ ጊዜ በዛ ያሉ ገዢዎችን) በማምጣት ደግሞ @mekina በ online ገቢያው ላይ ጥሩ ስም አለው።

@mekina በመቀላቀል ለራስዎ ያረጋግጡ።
5.1K views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 14:01:22
በኬሌ ከተማ በተከሰተው የእሳት አደጋ ቤቶች መቃጠላቸው ተገለጸ

በአማሮ ልዩ ወረዳ በኬሌ ከተማ አስተዳደር በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ አንድ ምግብ ቤት ሙሉ ለሙሉ እና 3 ቤቶች ደግሞ በከፊል መውደማቸውን የከተማው ፖሊስ አስታውቋል።

የኬሌ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኢንስፔክተር ጌታነህ ተስፋዬ ትላንት በግምት ከቀኑ 4:30 በንግድ ባንክ አካባቢ አቶ ባይሳ ካሌብ በተባለ ግለሰብ ሱቅ ቤንዚል ሲቀዳ ከሙቀት ጋር ተያይዞ ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንደተነሳ አስረድተዋል፡፡

ተመሳሳይ አደጋ ሲከሰት ይህ ለ3ኛ ጊዜ እንደሆነ ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰባቸውን የወረዳው ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethmagazine
12.1K viewsedited  11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 12:33:38
ህጻን አግቶ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ የአይከል ከተማ ነዋሪ የሆነውን 15 ዓመት ታዳጊ ህጻን ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ከመኖሪያ ቤቱ አፍኖ በመውሰድ ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በእስራት ተቀጥቷል።

ግለሰቡ ለህጻኑ ወላጆች ስልክ በመደወል 100 ሺህ ብር ከፍለው ልጃቸውን እንዲወስዱ ብሩን ካልከፈሉ ግን ህጻኑን እንደሚገድለው ሲዝት እንደነበር የፍርድ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወይዘሮ ማስተዋል ወርቁ ተናግረዋል።

በዛተውም መሰረት ህጻኑን በወረዳው ፋይና ገብ ተብሎ በሚጠራው ገደል ውስጥ በመክተት ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን በሰውና በህክምና ማስረጃ መረጋገጡን ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ክስ ከሰማ በኋላ ተከሳሹ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠይቅ ወንጀሉን አልፈጸምኩም በማለት ክዶ ተከራክሯል፡፡

ተከሳሽ በአቃቢ ህግ የቀረበበትን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ- ሥርዓት የህግ ቁጥር 149/1/ መሰረት ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡

ግለሰቡ የቤተሰብ አስተዳዳሪና ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ፈርዶበታል። (ENA)

@tikvahethmagazine
4.9K viewsedited  09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 12:22:03
ወደ ውጪ መላክ የነበረበት 235 ሺ በላይ ሜትሪክ ቶን የጥራጥሬ እና የቅባት እህል በክምችት መኖሩ ተረጋገጠ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአራት ከተሞች በክምችት ተይዘው ያሉ የቅባትና ጥራጥሬ ሰብሎች በአይነትና በመጠን ለማጣራት ዳሰሳዊ ጥናት አካሂዷል።

በተደረገው የዳሰሳ ጥናትም፦

- በአዳማ ከተማ 6,610.18 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል፣ 55,485.75 ሜትሪክ ቶን የጥራጥሬ ሰብል፤

- በአቃቂ ቃሊቲ 3,325.95 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል፣2,400.22 የጥራጥሬ ሰብል፤

- በቡራዩ ከተማ 43,569.25 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል ፣116,844.99 ሜትሪክቶን የጥራጥሬ እህል፣

- በገላን 57,274.13 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል 177,514.82 ሜትሪክ ቶን የጥራጥሬ እህል እንዲሁም 502.06 ሜትሪክቶን ሌሎች ምርቶች በድምሩ 235,291.02 ቶን በክምችት መገኘቱ ተገልጿል።

በሚኒስትር መ/ቤቱ የግብርና ምርቶች መሠረት ልማት ቡድን መሪ አቶ ታረቀኝ ሽበሺ ወደፊት የምርቶቹ ዋጋ ይጨምራል በማለት ምርትን በወቅቱ ወደ ውጪ ገበያ ከመላክ ይልቅ በክምችት ይዞ ማቆየት የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ አካላት ከዚህ ህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበው ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ ሚኒስቴር መ/ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን ሲሉ መግለጻቸውን ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine
5.8K viewsedited  09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 11:03:36
በቀጣይ 5 ዓመት 60 በመቶ የሚሆነውን የመድሀኒትና የህክምና ግብዓት በሀገር ውስጥ ምርት ይሟላል ተባለ።

በቀጣይ አምስት አመታት 60 በመቶ የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓትን በሃገር ውስጥ ምርት እናሟላለን ሲሉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍን በአዲስ ምዕራፍ ለማጠናከር ከፋርማሲዩቲካል አምራቾች እና ባለድርሻ አካላት ጋር እየተደረገ ባለው ምክክር መድረክ ነው።

@tikvahethmagazine
10.2K viewsedited  08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 10:47:08
ብሔራዊ ደም ባንክ የደም ክምችት እጥረት በማጋጠሙ ኀብረተሰቡ ደም በመለገስ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ አቀረበ።

አሁን ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ የመደበኛና የዕለት ተዕለት የደም ለጋሾች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በቂ የደም ክምችት እንዲኖር የመደበኛ ደም ለጋሾች ቁጥር መጨመር እንዳለበት ጠቅሰው፤ ለዚህ ደግሞ የደም ልገሳ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሊጎለብት ይገባል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ አኳያ ህብረተሰቡ በየ ሶስት ወሩ በቋሚነት ደም እንዲለግስ ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡ መደበኛ የደም ለጋሾች ቁጥርን ለማሳደግ ከተለያዩ ከትምህርት ቤቶች ፤ክበባት እና ከሌሎች ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም በአሁኑ ወቅት የደም ክምችት እጥረት መከሰቱን ጠቅሰው፤ እጥረቱ በተለይ በ “ኦ ኔጌቲቭ” የደም አይነት ላይ የጎላ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተለይ በክርስቲያንና ሙስሊም ጾም ወቅት የለጋሾች ቁጥር በመቀነሱ ምክንያት ከፍተኛ የደም እጥረት መከሰቱን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ኀብረተሰቡ በስፋት ደም በመለገስ እጥረቱን ለመቅረፍ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሀብታሙ ጥሪ ያቀረቡት፡፡

በኢትዮጵያ ከአንድ ሺህ ሰዎች መካከል ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ብቻ ደም እንደሚለግሱ መረጃዎች ያሳያሉ ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

@tikvahethmagazine
11.0K viewsedited  07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 10:47:00
ከአሜሪካ እና ከካናዳ የምናስመጣቸውን ኦሪጂናል ምርቶችን በመጠቀም ውበትውን በቀላሉ ይጠብቁ:: የቆዳውን ውበት ወደ ተፈጥሯዊ ይዘቱ ይመልሱ::
100% ኦሪጅናል
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ. https://t.me/kiyacosmo

Call 0910832000/ 0913473086
Contact @mekemeku or @kikkud
9.9K views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 10:46:59
Sejoy Blood pressure

0911284606
    ሀኪሞን በእጆ , ጤናዎትን በየግዜዉ ሳይጨነቁ በፈለጉበት ቦታ ና ግዜ ይወቁ
የደም መጠን ሚለካ 
የልብ ምት መጠንን ሚለካ
ሰለደም ግፊት አጠቃላይ መረጃ ሚሰጥ
ዋጋ- 1900  birr
Bole medanialem
10.0K views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 23:12:00
#FireAlert

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ኢንዱስትሪ መንደር ከፍተኛ የእሳት አደጋ የተነሣ ሲሆን ቃጠሎው ተባብሶ በርካታ ሼዶችንና መጋዘኖችን ሙሉ በሙሉ አጥፍቷል።

የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ መኪኖችና አባላት በቦታው የተገኙ ቢሆንም ቦታው አመቺ ባለመሆኑ አደጋውን መቀነስ ባይቻልም ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በመተባበር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛሉ።

የወረዳው ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጽ/ቤት እንደገለጸው እሳቱ አሁንም ድረስ ያልጠፋ ሲሆን አሁን ባለው መረጃ ከሦስት በላይ ሼዶች ተቃጥለዋል።

@tikvahethmagazine
9.8K viewsedited  20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 17:53:20
በህገ- ወጥ መንገድ 7 ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ከካፋ ዞን ጨና ወረዳ ባላ ሻሻ ቀበሌ ከአስር ዓመት በታች የሆኑ ሰባት ሕፃናቶችን ከሚኖሩበት ቤተሰብ ከብቶችን ትጠብቃላችሁ በማለት አታሎ 7 ሕፃናቶችን በህገ- ወጥ መንገድ ሊያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ ህጻናቶቹን ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ጉፍቃ ቀበሌ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 በተሽከርካሪ ህፃናቶቹን ይዞ በመጓዝ ላይ እንዳለ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@tikvahethmagazine
21.2K viewsedited  14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ