Get Mystery Box with random crypto!

ህጻን አግቶ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። በማዕከላዊ ጎን | TIKVAH-MAGAZINE

ህጻን አግቶ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ የአይከል ከተማ ነዋሪ የሆነውን 15 ዓመት ታዳጊ ህጻን ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ከመኖሪያ ቤቱ አፍኖ በመውሰድ ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በእስራት ተቀጥቷል።

ግለሰቡ ለህጻኑ ወላጆች ስልክ በመደወል 100 ሺህ ብር ከፍለው ልጃቸውን እንዲወስዱ ብሩን ካልከፈሉ ግን ህጻኑን እንደሚገድለው ሲዝት እንደነበር የፍርድ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወይዘሮ ማስተዋል ወርቁ ተናግረዋል።

በዛተውም መሰረት ህጻኑን በወረዳው ፋይና ገብ ተብሎ በሚጠራው ገደል ውስጥ በመክተት ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን በሰውና በህክምና ማስረጃ መረጋገጡን ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ክስ ከሰማ በኋላ ተከሳሹ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠይቅ ወንጀሉን አልፈጸምኩም በማለት ክዶ ተከራክሯል፡፡

ተከሳሽ በአቃቢ ህግ የቀረበበትን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ- ሥርዓት የህግ ቁጥር 149/1/ መሰረት ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡

ግለሰቡ የቤተሰብ አስተዳዳሪና ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ፈርዶበታል። (ENA)

@tikvahethmagazine