Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ውጪ መላክ የነበረበት 235 ሺ በላይ ሜትሪክ ቶን የጥራጥሬ እና የቅባት እህል በክምችት መኖሩ | TIKVAH-MAGAZINE

ወደ ውጪ መላክ የነበረበት 235 ሺ በላይ ሜትሪክ ቶን የጥራጥሬ እና የቅባት እህል በክምችት መኖሩ ተረጋገጠ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአራት ከተሞች በክምችት ተይዘው ያሉ የቅባትና ጥራጥሬ ሰብሎች በአይነትና በመጠን ለማጣራት ዳሰሳዊ ጥናት አካሂዷል።

በተደረገው የዳሰሳ ጥናትም፦

- በአዳማ ከተማ 6,610.18 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል፣ 55,485.75 ሜትሪክ ቶን የጥራጥሬ ሰብል፤

- በአቃቂ ቃሊቲ 3,325.95 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል፣2,400.22 የጥራጥሬ ሰብል፤

- በቡራዩ ከተማ 43,569.25 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል ፣116,844.99 ሜትሪክቶን የጥራጥሬ እህል፣

- በገላን 57,274.13 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል 177,514.82 ሜትሪክ ቶን የጥራጥሬ እህል እንዲሁም 502.06 ሜትሪክቶን ሌሎች ምርቶች በድምሩ 235,291.02 ቶን በክምችት መገኘቱ ተገልጿል።

በሚኒስትር መ/ቤቱ የግብርና ምርቶች መሠረት ልማት ቡድን መሪ አቶ ታረቀኝ ሽበሺ ወደፊት የምርቶቹ ዋጋ ይጨምራል በማለት ምርትን በወቅቱ ወደ ውጪ ገበያ ከመላክ ይልቅ በክምችት ይዞ ማቆየት የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ አካላት ከዚህ ህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበው ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ ሚኒስቴር መ/ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን ሲሉ መግለጻቸውን ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine