Get Mystery Box with random crypto!

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

የቴሌግራም ቻናል አርማ rodas9 — መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
የቴሌግራም ቻናል አርማ rodas9 — መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
የሰርጥ አድራሻ: @rodas9
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 37.96K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-05-10 20:19:22 Watch "የግእዝ ፊደል ከፍተኛ መንፈሳዊ ኃይል" on YouTube


4.5K views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 17:44:55
ለ2 ወራት ከ YouTube ርቄ ነበር አሁን ግን ዛሬ ረቡዕ በግንቦት 2 ከምሽቱ 2:22 ላይ ረቂቅ ምስጢርን ይዤላችሁ እቀርባለሁ። በየቀኑም ከ20 ላልበለጡ ደቂቃዎች ብርሃን የኾነውን ጥበብ በአምላክ ፈቃድ እለቅላችኋለሁ።
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
5.3K views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 17:50:18 ከዚያ የነበሩ አይሁድም በመደናገጥ “ሳሚናስ ምን አየኽ? ምን ትላለኽ?” አሉት፤ ርሱም “ከዚች ከሐና ማሕፀን የምትወለደው ሕፃን ሰማይ ምድርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ኹሉ ሲያመሰግኗት ሰማኋቸው፤ እኔንም ያነሣችኝ ርሷ ናት” አላቸው፤ እነርሱም ይኽነን በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔርን ከማመስገን ይልቅ በቅናትና በክፋት ተመልተው ሐና በማሕፀን ባለ ፅንሷ ካዳነች በኛ ላይ ልትሠለጥን አይደለምን? “ንዑ ንገሮሙ ለሐና ወለኢያቄም” ሳትወልድ አስቀድመን ሐናና ኢያቄምን በድንጋይ ወግረን እንግደላቸው ብለው ተነሣሡባቸው።

ያን ጊዜ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ሐናን ሊባኖስ ወደሚባል ተራራ እንዲወስዳት ነገረው፤ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ እመቤታችን በሊባኖስ ተራራ እንደምትወለድ ተገልጾለት፡-
“ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት” (ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነዪ ከሊባኖስ ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ) በማለት የተናገረው ትንቢት ሊፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች (ማሕ ፬፥፲)፡፡

ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ የነገረ ማርያም መጽሐፋቸው ላይም፦
“ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ
በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ
ማእከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ እንዘ እነቡ
እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዐጽ እሌቡ
ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ”

(ትንቢት ከተነገረለት ከአንበሳ ጉድጓድ፤ ድንግል ሙሽራ በተገኘሽ ጊዜ የንጉሦች ንጉሥ የሰሎሞን ልቡ እንደተደሰተ፤ ደስ ባላቸው በመላእክት አንድነት ፊት ታምርሽን እየተናገርኊ የሐና አበባ ማርያም እዘምርሻለኊ፤ ወተትን ጠብቶ እንደሚዘልል እንቦሳም ዝለል ዝለል ይለኛል) በማለት ሰሎሞን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን አግኝቶ ታላቅ ደስታን ለኹላችን እንደሰጠን አብራርተው ገልጠዋል፡፡

ይኽ የእመቤታችን ልደት ለሰማያውያን መላእክትና ለደቂቀ አዳም ደስታ ሲኾን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከርሷ ተወልዶ ዲያብሎስ ፭ሺሕ፭፻ ዘመን በሲኦል ያኖራቸውን ነፍሳት ወደ ገነት የሚያስገባቸው ነውና፤ ሰይጣን በተቃራኒው ልደቷ እንዳላስደሰተው ሲገልጹ፦

“ተፈሥሐት ምድር ወሰማይ አንፈርዐጸ
በዕለተ ጸገዩኪ አብላስ ወአውጽኡ ሠርጸ
ተአምረ ሕይወት ማርያም ዘአልብኪ ቢጸ
እስከ ፈርሀ መልአከ ሞት ወሰይጣን ደንገጸ
ዜና ልደትኪ ነጐድጓድ እስከ (ውስተ) ሲኦል ደምፀ”

(በለሶች (ኢያቄምና ሐና) ቡቃያ አንቺን ባስገኙሽ ጊዜ ምድር ደስ አላት ሰማይም ደስ አለው፤ ጓደኛ (ምሳሌ) የሌለሽ የድኅነት ምልክት ማርያም፤ መልአከ ሞት እስከ ፈራና ሰይጣንም እስከ ደነገጠ ድረስ የመወለድሽ ዜና እስከ ሲኦል ድረስ (በሲኦል) ተሰማ) በማለት አስተምረዋል፡፡

ጠቢቡ ሰሎሞን አስቀድሞ በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ በማሕልይ 6:10 ላይ “መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎሕ ሠናይት ከመ ወርኅ ወብርህት ከመ ፀሓይ” (ይኽቺ እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ እንደ ጨረቃ የተዋበች፤ እንደ ፀሓይም የጠራች ዐላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሰራዊት የምታስፈራ ማን ናት?) በማለት እንደ ፀሓይ የሞቀ እንደ ጨረቃ የደመቀ ንጽሕናዋና ቅድስናዋ የመልኳ ደም ግባት በነቢያት ትንቢት አስቀድሞ የተጐበኘላት የእውነት ፀሓይ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብርና ደም ግባቷን እንደተናገረ በሊባኖስ ተራራ በግንቦት ፩ በተወለደች ጊዜ ፊቷ በእጅጉ ያበራ ነበር፤ መዐዛዋም ከሽቱ ኹሉ ይበልጥ ነበር፡፡

የፈጣሪያችን እናት ቅድስት ድንግል የተወለደችበትን ግንቦት አንድን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን “ልደታ ለማርያም” በማለት ከጥንት ዠምሮ በታላቅ መንፈሳዊ ሐሤት በቅዳሴ፣ በማሕሌት የምታከብርላት ሲኾን፤ በተለያዩ ክፍላተ ዓለማት ያሉ ክርስቲያኖችም ይኽነን በዓል “The Nativity of the blessed Virgin Mary” (የተባረከችው የድንግል ማርያም ልደት (መወለድ)) በማለት ያስባሉ።

በጥንት ምሥራቃውያን (እንደ ቤዛንታይን ባሉ) ዘንድ ዐዲሱ ዓመት ልክ እንደኛ መስከረም ወር “September” ላይ ይውል ስለነበር መስከረም ፰ (September 8) ያከብሩት የነበረ እንደነበር ታሪክ ሲያስረዳ ይኽነን ይዘው በዚኽ ዕለትም የሚያከብሩት ብዙዎች የዓለማት ሀገራት አሉ፡፡
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
[ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፤ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል አንድ ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ]

እኔ ታናሽ አገልጋይሽም እመቤቴ ወላዲተ አምላክ ሆይ የፀሐይ መገኛ ሰማይ፤ የመና እናት መሶብ፤ የፍሕም እናት ማዕጠንት፤ የብርሃን እናት መቅረዝ፤ የጠል እናት ፀምር ተገኝተሻልና በልደትሽ ደስ ብሎናል። እናቴ ሆይ እንኳን ተወለድሽ እላለሁ።
6.6K views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 17:50:17 [የአምላክ እናት ልደት (ልደታ ለማርያም)]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መተርጒማን እንዳስተማሩንና አበው በነገረ ማርያም ላይ እንደጻፉልን ሐናና ኢያቄምንም “ወክልኤሆሙ ኄራን ወሥሙራን እሙንቱ ወየሐውሩ በሕገ እግዚአብሔር እስመ እግዚአብሔር ኀረዮሙ ወአፍቀሮሙ ትካት” ይላቸዋል እግዚአብሔርን የሚወድዱ በሕጉ የሚኖሩ ደጋጎችና አምላክም የመረጣቸው ነበሩ።

ሐና መካን በመኾኗ ምክንያት ኹለቱም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት በመኼድ ለዐይናቸው ማረፊያ ለልባቸው ተስፋ የሚኾን ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ እንደነበር፤ “Protoevangelium of James” (ፕሮቶቫንጊሊዩም ኦፍ ጀምስ) የሚለው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊዉ መጽሐፍ በስፋት ይገልጻል፡፡

ከዕለታት ባንደኛው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ሲመለሱ “ወርእዩ አርጋበ እንዘ ይትፌሥሑ ምስለ ውሉዶሙ” ይላል ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ደስ ብሏቸው ሲጫወቱ አይተው ሐና “አቤቱ ጌታዬ ግዕዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠኽ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሣኸኝ” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፤ ወዲያው ሱባዔ ይገባሉ፤ ኢያቄም ወደ በረሓ ኼዶ ሲጸልይ ሐና ደግሞ በቤቷ ዙሪያ ባለው የተክል ቦታ ሱባዔ ያዘች።

በሱባዔያቸው ፍጻሜ ኹለቱም ራእይ አይተው ተነጋግረዋል፡፡ “ይቤላ ኢያቄም ለሐና ብእሲቱ እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ” ይላል ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዎፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ብሎ የተገለጸለትን ለሐና ነግሯታል።

ይኸውም የራእዩ ምስጢር፡- ወፍ የተባለው አካላዊ ቃል ክርስቶስ ሲኾን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፤ ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ ሲያጠይቅ ሲኾን፤ ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ምልአቱ፣ ስፍሐቱ፣ ርቀቱ፣ ልዕልናው፣ ዕበዩ ናቸው፡፡

ሐናም ተገልጾላት “ትቤሎ ሐና ለኢያቄም ብእሲሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ” ይላል ለባሏ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ብላዋለች።

ይኽ የራእይ ምስጢር፡- ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትኾን፤ ነጭነቷ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፤ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ ወደ ዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በዦሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መኾኗን ሲያጠይቅ ነው፡፡

ኢያቄምና ሐናም ይኽነን ራእይ ሐምሌ ፴ ቀን ካዩ በኋላ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ይኾናል፤ ሴትም ብንወልድ ለቤተ እግዚአብሔር መጋረጃ ፈትላ ትኑር” ብለው ስእለት ከተሳሉ በኋላ ራእይ አየን ብለው ዕለቱን አልተገናኙም፤ አዳምንና ሔዋንን “ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት” ብሎ የተናገረው አምላክ ለእኛም ይግለጽልን ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ሰባት ቀን ድረስ እየብቻቸው ሰነበቱ።

ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን “ከሰው የበለጠች ከመላእክት ኹሉ የከበረች ልጅ ትወልዳላችኊ" ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለሐና ነግሯት በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን ነሐሴ ሰባት እሑድ ተፀንሳለች፤ በእናቷ ማሕፀን ሳለችም “መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሠ እማ” እንዲል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥንተ አብሶ ባመጣው መርገም እንዳትያዝ ጠብቋታል፡፡

ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም መፀነስ ከሊቃውንት መኻከል አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፦

“ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ
ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ
ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ
እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ
ወድኀኒተ ኲሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ”

(ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለኊ) በማለት ዓለምን ኹሉ በደሙ ፈሳሽነት ያዳነ ንጉሣችን፣ ፈጣሪያችን ክርስቶስን በድንቅ ተአምር ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ የወለደችልን ምክንያተ ድኂን ርግበ ሰሎሞን የተባለች የቅድስት ድንግልን የመፀነሷን ነገር በአድናቆት ገልጸዋል፡፡

“ወእምድኅረ ስድስቱ አውራኅ ተዐውቀ ፅንሳ ለሐና” ይላል፤ ከስድስት ወርም በኋላ የሐና ፅንሷ እየታወቀ ሲመጣ ጎረቤቶቿ መፅነሷን ይረዱ ዘንድ በአድናቆት ማሕፀኗን ይዳስሱ ነበር፤ በተለይም ዐይኗ የታወረ የሐና ዘመዷ የአርሳባን ልጅ የምትኾን አንዲት ሴት የሐናን ማሕፀን ዳስሳ ዐይኗን ብትነካው በርቶላት በታላቅ ደስታ ኾና “ብፅዓን ለኪ ኦ ሐና እስመ እም ፍጥረተ ዓለም አልቦ ዘከማኪ ዘይፌውስ በከርሡ አዕይንተ ዕውራን” (ሐና ሆይ ብፅዓን ይገባሻል ዓለም ከተፈጠረ ዠምሮ እንዳንቺ በማሕፀኑ የዕውራንን ዐይን የሚያበራ የለምና) በማለት አመስግናታለች፤ ከዚኽ በኋላ ዝናዋ በሀገሩ ኹሉ ተሰምቶ ሕሙማን ኹሉ ማሕፀኗን እየዳሰሱ ይፈወሱ ነበር፡፡

አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ይኽነን ሲገልጹ፦
“ጸግይየ ሣዕረ ዘኪሩቤል ልሳነ
ተአምረኪ በነጊር እመ ኢፈጸምኩ አነ
ባሕቱ አአኲት ማርያም ዘጾረተኪ ማሕፀነ
እንዘ ሀለወት ፀኒሳ ኪያኪ ርጢነ
ለለገሰስዋ ላቲ ትፌውስ ዱያነ”

(ሳርን የኾንኊ እኔ የኪሩቤል አንደበትን ገንዘብ አድርጌ ታምርሽን በመንገር በማስተማር ባልፈጽምም ነገር ግን ማርያም የተሸከመቺሽን ማሕፀን አመሰግናለኊ፤ መድኀኒት አንቺን ፀንሳ ሳለች ርሷን የዳሰሷትን ድዉያንን ኹሉ ትፈውስ ነበር) በማለት እመ መድኅነ ዓለም ገና ሳትወለድ የተሠራውን ድንቅ ተአምር አመስግነዋል፡፡

ይኽ የቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰት በዓል በመላው ዓለም የሚታወቅ ሲኾን ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት የኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን የአምላክ እናት የተፀነሰችበት ይኽነን በዓል ነሐሴ ፯ ቀን በታላቅ ድምቀት በማሕሌት፣ በቅዳሴ የምታስበው ሲኾን በዓሉም “ፅንሰታ ለማርያም” በመባል ይታወቃል።

በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ደግሞ በዓሉን “The conception of the Theotokos” (የአምላክ እናት መፀነስ) በማለት ሲያከብሩት ወሩን ግን የልደት በዓልን ለማክበር በሚዘጋጁበት በታኅሣሥ አድርገው በ፱ኛው ቀን “December 9” ላይ ያስቡታል ፡፡

በእጅጉ የሚደንቀው ደግሞ “ሳሚናስ ወልደ ጦሊቅ ዘይነብር ውስተ ቤተ ዶይቅ” ይላል ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጐቱ ቤት ኼዶ ሞተ፤ ሐናም በሀገራቸው ልማድ የአልጋውን ሸንኮር ይዛ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ፈጥኖ ተነሥቶ “ሰላም ለኪ ኦ ሐና እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ” (ሰማይና ምድርን ለፈጠረው አምላክ አያቱን የተባልሽ ሐና ሰላም ላንቺ ይኹን) አላት።
6.3K views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 12:39:41 ተወዳጆች ሆይ መልካም ልደት በማለት የፍቅር መልእክታችሁን ለላካችሁልኝ በሙሉ በእጅጉ የአክብሮት ምስጋናዬን እያቀረብኩ ልዑል እግዚአብሔር በምድራዊም በሰማያዊው ሀብት ያክብራችሁ በማለት ምኞቴን ለሁላችሁም ይድረስልኝ ብያለሁ።
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
6.0K views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 20:49:56
በ8ኛው ወር በሚያዝያ፤ በ22ኛው ቀን፤ ትንሣኤን የሚወክለውና ሰባቱን የፕሊዬዲስ ከዋክብት የሚመራው ሰውር (ታውረስ) ከፀሐይ ጋር በሚውልበት ዕለት ተወለድኩ።
በጌታ ቀኖት የተሰየመው የዚህ ሮዳስ DNA ሲመረመር "ያህዌህ" የሚለው ስመ አምላክ (10 - 5 - 6 - 5) ብቻ ነው።
ሁሉንም የምድር ወላጆቹን በመተው አባቱ ኢየሱስ ብቻ፤ እናቱ ማርያም ብቻ፤ ወዳጁ ጥበብ፤ ሀገሩም ሰማያዊ እንደሆነ በሚገባ ተረድቷል።
አልፋ ዖሜጋ ፈጣሪው በሰጠው ባለፈው ዓመቱ 888 የሚለውን 26ኛ መጽሐፉን አሳትሞ አስመርቆ ለአንባብያን ሰጥቷል።
የሚያበራ የንጋት ኮከብ፣ የይሁዳ አንበሳ ጌታው ክርስቶስ ብቻ በሚሰጠው በቀጣይ የ365 ዕለት ዑደታዊ ጉዞው በፈጣሪው ቸርነት 27ኛ መጽሐፉን ለትውልድ ያስቀምጣል።
መልካም ልደት በሉት፤ ባትሉትም አይከፋውም።
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
8.1K views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 17:43:29
"ከአንተ የሆነውን ድንቅና ስዉር ጥበብን አሳውቀኸኛልና ብርሃነ ብርሃናት፣ ጠቢበ ጠቢባን አባቴ እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሃለሁ"
(111 - 222 - 333 - 444 - 555 - 666 - 777 - 888 - 999)
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
10.3K views14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 21:41:40 "ሠዐሊ የሣለውን ሥዕል ስትቀድበት፣ ስታቃጥልበት እንደሚያዝን፤ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥዕሉ ሰው ነውና፤ በምላስህ አቃጥለኸው ብትገድለው ተጠያቂ ነህና አንደበትህን ተቆጣጠር"
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
12.1K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 20:57:49 "1 ምድር፤ 2 ተቃራኒ ጾታ፤ 3 የኖኅ ትውልዶች፤ 4 ባሕርያት፤ 5 የውጪ ሕዋሳት፤ 6 ኛው ዕለት የተፈጠረ ሰው ባለበት፤ 7 አህጉርና ውቅያኖስ በተነጠፉበት፤ 8 ቢሊየን አዳማዊ ሕዝቦች ባሉበት በዚህ ሰዓት ያለምክንያት አልተወለድክምና ብቃ ወይም ንቃ"
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
4.3K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 18:48:25 "ዝናቡን እንደ ወፍ በሠራኸው ጎጆ ወይም እንደ ንስር ከደመናው በላይ ኾነህ ዕለፈው። ጎርፉን ዋኝተህ ወይም በመርከብ ውስጥ ገብተህ ተሻገረው። ነፋሱን ወፍራም ጃኬት ለብሰህ ወይም ግንብ ሠርተህ አሳልፈው። ምርጫው የአንተ ነው። የተሻለውን ግን ምረጥ"
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ዘአንድሮሜዳዊ 888)
4.9K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ