Get Mystery Box with random crypto!

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

የቴሌግራም ቻናል አርማ rodas9 — መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
የቴሌግራም ቻናል አርማ rodas9 — መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
የሰርጥ አድራሻ: @rodas9
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 37.92K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-03-07 03:04:57 ለኮምፒውተር ሳይንስ እስከ መጥቀም የሚያደርሱ በርካታ ቀመርን የያዙ የግእዝ ፊደላት በያዙት ጥበብ ላይ ከፍተኛ ጥናት ያጠኑ ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ላይ ያሉ ሳይንቲስቶች የሚሳተፉበት ሳይንሳዊ ጉባኤ (በሰሜን አሜሪካ)

Historians have recognized Ethiopia as an ancient civilization with the earliest known governance system but most of all for its unique and efficient writing system, the Ethiopic Scripts (aka, Geez Script).

We cordially invite you all to join us to the first conference series on Saturday, March 11, 2023 at 10:00 AM EST (6:00 PM Addis Ababa Time; በአዲስ አበባ አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰዓት)

Please register as soon as you possibly can to enable us to make the necessary adjustments with audience attendance protocols.

Please also find a conference flyer in the attachment. Thank you.

Here below is the link for registration:

HERE / https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_ZX1kAg12R82A3sa-1VYxrw
2.8K views00:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 03:04:55
2.7K views00:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 09:35:19

2.7K views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 09:04:11 በክተት ዐዋጅ ስሟን የጠሯት አፍጣኒተ ረድኤት የኾነችው የእመቤታችንን ታቦትና የፍጡነ ረድኤት የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት አስይዘው በመኼድ የካቲት 23 በ1888 ዓ.ም. የጣሊያንን ጦር በመደምሰስ እጅግ አስደናቂ ድልን በአህጉሪቱ በአፍሪካ በማስመዝገብ ለመላው የአፍሪካ ሕዝቦች የነጻነት ጮራ ዋና ወጊ በመኾን፤ መላው አፍሪካ የተጫነበትን የቅኝ ግዛት ቀንበርንና የነጮችን የበላይነት ሰባብሮ እንዲጥል መርህ ኾነውታል፤ በእውነት ስሟን የጠሯት ወላዲተ አምላክ አላሳፈረቻቸውም፤ ይኽ ፍቅራቸው በልጃቸው በንግሥተ ንግሥታት ዘውዲቱ ዐልፎ በአታ ለማርያምንና ሌሎች የእመቤታችንን መቅደስ አሠርተው፤ በሚያልፍ ዘመን የማያልፍ ሥራ ሠርተው ወደ ልዑል እግዚአብሔር ተጠርተው ኼደዋል፨

[በመጨረሻም ጽሑፌን ዐጼ ምኒልክን በቃል ኪዳኗ የተራዳችውን እመቤታችንን፤ በፈጣን ተራዳኢነቱ ያልተለያቸው ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን አስቀድሞ በ530 ዓ.ም. ባመሰገነው በቅዱስ ያሬድ ቃል አበቃለሁ፦
"ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወላዕሌነ ይኩን ምሕረት በጸሎተ ጊዮርጊስ ዐቢይ ሰማዕት ወማርያም ወላዲተ አምላክ" [በሰማያት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን በታላቁ ሰማዕት በጊዮርጊስና አምላክን በወለደች በእመቤታችን ጸሎት የእግዚአብሔር ምሕረት በእኛ ላይ ይኹን] [ቅዱስ ያሬድ]
ከሌሊቱ 6 ሰዓት የካቲት 23 በሞባይሌ ላይ ለበረከት ያኽል በጥቂቱ ጻፍኩት [መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ] [በድጋሚ ፓስት አረኩት]
4.5K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 09:04:11 [እግዝእትነ ማርያምን ለዚኽ አማላጅ የለኝም ዐጼ ምኒልክ በአምላክ እናት ስም ያደረጉት የክተት ዐዋጅና ቀደምት ነገሥታት ለአምላክ እናት ያላቸው ፍቅር]
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ [በየካቲት 23፤ 2010 ዓ.ም. ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተጽፎ በድጋሚ ፓስት የተደረገ]
በምንኖርበት ምድር ካሉ ሀገራት ሁሉ ስናወዳድር ለእመቤታችን ጥልቅ ፍቅር የነበራቸው ሕዝቦችና ነገሥታት የነበሩባት ታላቋ ሀገር ኢትዮጵያን በቀዳሚነት እናገኛታለን፨

ከ3000 ዓመት በፊት የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችው ታቦተ ጽዮን ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል እንድትመጣ ጌታችን ስለፈቀደልን፤ የእናቱ ምሳሌዋን አስቀድሞ በኢትዮጵያ ሀገር ላይ አስቀመጠ፨

ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም አምላካችን ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ ይዘው እመቤታችንን ከልጇ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በዐይናቸው ካዩ ነገሥታት ውስጥ ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ እነ ዳዊት፣ እነ ኢሳይያስ በትንቢት ሲናገሩ ብዙ የታሪክና የነገረ መለኮት ሊቃውንት ጽፈዋል፨

ሄሮድስ ጌታን ሊገድል በፈለገ ጊዜም በእናቱ ጀርባ ታዝሎ ወደ ምድረ ግብጽ በተሰደደ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ሀገሪቱን ባርኮ ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም ሕዝቦቿን ዐሥራት አድርጎ እንደሰጣት በከበረ ተአምሯ ላይ ስናነብ በጣና ቂርቆስ ገዳም የእግሯ አሻራ እና የሀገሪቱን ቅርጽ ዓለት ላይ ዐትሞ እንዳሳያት ዛሬ ድረስ በዐይን ኼዶ ማየት ይቻላል፨

ይኽ የቃል ኪዳኗ በረከት በዚች ሀገር ላይ አለና በኢትዮጵያ ሀገራችን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በንጉሠ ነገሥት በአብርሃ እና በአጽብሐ ከ1680 ዓመት በፊት በ330 ዓ.ም. ላይ በአክሱም የተሠራችው በእመቤታችን ስም ሲኾን ባለ 12 መቅደስ ኾና በወርቅና በዕንቁ ያጌጠች ነበረች፨

ከ515-529 ዓ.ም. የነገሠው ዐጼ ገብረ መስቀል ሲኾን በርሱ ጊዜ የነበሩት ከ9ኙ ቅዱሳን አንዱ አቡነ አረጋዊና ሊቁ ማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሲኾኑ ንጉሡ ደብረ ዳሞ ድረስ በመውጣት ለእመቤታችን ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ በተራራዋ ላይ እጅግ የምታስደንቅ የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያንን ያሠራ ሲኾን ቅዱስ ያሬድም ይኽችን የእመቤታችን ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ተመልክቶ "ዖድክዋ ዖድክዋ ወርኢኩ ሥነ ሕንጺሃ" (ዞርኳት ዟርኳት ያማረ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኗን ውበት አየሁ) እያለ ዘምሯል፨

እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ያፈቅሩ ከነበሩት ነገሥታት መኻከል አንዱ ከቋጥኝ ደንጊያ ከዐለት ዓለም የሚደነቅባቸውን አብያተ ክርስቲያንን ያነጸው ከ1157-1197 ዓ.ም. ለ40 ዓመታት የነገሠው ዐጼ ላሊበላ ሲኾን ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ ከሌሎች ኹሉ አስበልጦ የእመቤታችንን መቅደስ እጅግ ውብ አድርጎ በብሩህ ቀለማት በቅዱሳት ሥዕላት አስጊጦ በ12 ዐምዶች ያነጻት ሲኾን በውበቷ ተወዳዳሪ የላትም፨

እመቤታችንን ይወዱ ከነበሩ ቀደምት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከ1365-1395 ዓ.ም. የነገሡት ዐጼ ዳዊት በጣም የሚታወቁ ሲኾን ለቅድስት ድንግል ማርያም ካላቸው ጥልቅ ፍቅር በመነሣት የእመቤታችንን ተአምር ከዐረብኛ ወደ ግእዝ ቋንቋ ካስተረጎሙ በኋላ በወርቅ ቀለም እንዲጻፍ አድርገዋል፨

ንጉሥ ዳዊት የእመቤታችን ፍቅር ውስጣቸው ድረስ ጠልቆ በመግባቱ ተአምሯ በወርቅ ቀለም በሚጻፍ ጊዜ ንጉሠ ነገሥት ዐጼ ዳዊት ዕንባቸውን ከቀለሙ ጋር እንዲቀላቀል በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ዕንባቸውን ከቀለሙ ጋር ጨምረው የእመቤታችን ተአምርን ያጻፉ የምድራችን የመጀመሪያው ንጉሥ ነበሩ፨

የእመቤታችን ፍቅር በእጅጉ የበዛላቸው ሌላው ንጉሥ የዐጼ ዳዊት ልጅ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ሲኾኑ በግብጽ የምትገኘው የእመቤታችን የደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን በግብጹ ንጉሥ ባርስባይ በግፍ መፍረሷን የግብጽ ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ ፲፩ኛ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ለእመቤታችን ያለውን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቁ ለርሳቸው ደብዳቤን በጻፉ ጊዜ ዐዝነው ካይሮ በፈረሰችው በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ስም ተጒለት ውስጥ አሠሩ፤ ከዚኽ ተነሥተው ዛሬ ድረስ በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ማርያም እመቤታችንን "የዘርዐ ያዕቆብ እመቤት" ይሏታል።

ብሔራውያን ሊቃውንት አባታቸው ዐጼ ዳዊት እመቤታችንን ከመውደድ የተነሣ መልክአ ማርያምን “ለዝክረ ስምኪ” ከሚለው ዠምሮ “ለገቦኪ” እስከሚለው እስከ ኹለተኛው ቤት “በከመ ዳዊት ይዜኑ” እስከሚለው ደርሰው ሲያቆሙ ፤ ልጃቸው ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ ደግሞ “ማርያም ድንግል ለያዕቆብ ሞገሰ ሥኑ” በማለት ቀጥለው እስከ መጨረሻው እንደፈጸሙት ይናገራሉ ፡፡ ንጉሡ ዐጼ ናዖድም እንደጻፈላት የሚገልጹ መምህራን አሉ፨

በአምላክ እናት ፍቅር ልባቸው በመቃጠሉ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ በኹሉም አብያተ ክርስቲያናትን በእሑድ እና በበዓላት የእመቤታችን ተአምር እንዲነበብ ሲያደርጉ፤ ልክ እንደ አባታቸው እንደ ዐጼ ዳዊት የእመቤታችንን የተአምር መጽሐፍ ለተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ሲያጽፉ ዕንባቸው ከመጻፊያው ቀለም ጋር እንዲደባለቅላቸው ለጸሐፊዎቹ በመንገር ዕንባቸውን በማፍሰስ ታማልዳቸው ዘንድ ይማፀኗት ነበር፨

ከ1500-1532 ዓ.ም. የነገሡት ዐጼ ልብነ ድንግል የቀደሙት ነገሥታትን አሠር በመከተል ለቅድስት ድንግል ማርያም ካላቸው ጥልቅ ፍቅር በመነሣት በመጽሐፈ ሰዓታት ላይ የሚገኘውን "ለኖኅ ሐመሩና ስብሐተ ፍቁር ዘማርያም የሚለውን ድንቅ የምስጋና ድርሰት ለእመቤታችን ደርሰውላታል።

ሌላዋ በጣም የእመቤታችን ፍቅር በልባቸው ያደረባቸው ከ1723-1748 ዓ.ም. የነገሡት የዐጼ በካፋ ሚስት እቴጌ ምንትዋብ ሲኾኑ የእመቤታችን የስደቷና ቁስቋም የመቀመጧን ነገር ኹሌ የሚያስቡ ንግሥት ነበሩ፤ እመቤቴ ልጇን ይዛ ከሀገሯ ወጣ ብላ ቁስቋም እንደቆየች እኔም ከከተማው ወጣ ብዬ መቀመጥ እሻለሁ ብለው 5ት ኪሎ ሜትር ከከተማ ርቀው በአንድ ሺሕ የኢትዮጵያ የግንባታ ጠበብት የእመቤታችን የቁስቋም ቤተ ክርስቲያንን ሲያሠሩ 500ው ቆመው ስሕተቶችን በመንገር ያስገነቡ ነበር።

ንግሥት ምንትዋብ የእመቤታችንን ስደት በማሰብ ዕንባቸውን ያፈሱ የነበሩ ንግሥት ሲኾኑ የእመቤታችን ስደቷን አስበው የፈቃድ ጾም የኾነውን ጾመ ጽጌን መጾም የጀመሩ ንግሥት ርሳቸው እንደነበሩ ሊቁ ዶክተር ሥርግው ይገልጻሉ።

እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ይወዱ የነበሩት ታላቁ ንጉሥ ዐጼ ምኒልክ ሲኾኑ በእመቤታችን ፍቅር እንጦጦ ማርያምን ካሠሩ በኋላ ለቅዳሴ ቤቷ ወደ 5000 የሚጠጉ ሰንጋዎችን ያሳረዱ ሲኾን ጠጁ በገንዳ እንዲመላ በማድረግ ፍቅራቸውን የገለጡ ሲኾን በበዓሉ ሰማዩ ጠቁሮ ሊዘንብ ሲል እመቤታችን ከልጇ እንድታማልዳቸው "ይድረስ ለድንግል ማርያም" የሚል ደብዳቤ ጽፈው የእመቤታችን መንበር ላይ እንዲቀመጥ ሲያደርጉ ወዲያው ዝናብን የቋጠረው ደመና ተበትኖ ፀሐይ በመውጣት ድንቅ ተአምር እንደተደረገ እነ ጳውሎስ ኞኞና ሌሎችም የታሪክ ምሁራን ይመሰክራሉ።

ኢትዮጵያን ለመውረር ወራሪው ጣሊያን ወደ ሀገራችን በከባድ መሣሪያ ታግዞ በዕብሪት ሲመጣ ንጉሡ የክተት ዐዋጅን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያውጁ የዐዋጃቸው ማተሚያ ኹሌም በፍቅር የሚወዷት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ኹሉ ከልብ የሚወዷት እመቤታችንን በመጥቀስ እግዝእትነ ማርያምን ለዚኽ አማላጅ የለኝም በማለት ነበር ክተት ያወጁት።
4.6K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 00:12:41 "ረቂቁን ብርሃን የሰጠኸን አቤቱ ኤልሻዳይ ሆይ በዚኽ ታላቅ ጾም ዐይኖቼን፣ ጆሮዎቼን፣ አንደበቴን፣ ሕዋሳቴን ኹሉ የአንተን ለአንተ ብቻ ሰጥቻለሁ፤ ከአንተ ውጪ ማንም እንዳይማርከው በብርቱ ክንድህ ጠብቅልኝ"
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
[ውስጣችንን ራሳችንን የምናይበት ሱባኤ ይኹንልን]
3.6K views21:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 19:24:30 https://www.youtube.com/live/Dkq5w42hZpo?feature=share
2.8K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 20:18:14 https://www.youtube.com/live/lXrmNOe2YR4?feature=share
4.7K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 18:19:40 ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 1:11 ላይ በዚኽ ሳምንት በመላው ዓለም ኹሉ መነጋገሪያ ስለኾኑት UFO የቀጥታ ሥርጭት በ Dr Rodas Tadese YouTube channel ላይ ይቀርባል።
5.9K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 06:09:12
7.9K views03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ