Get Mystery Box with random crypto!

በ8ኛው ወር በሚያዝያ፤ በ22ኛው ቀን፤ ትንሣኤን የሚወክለውና ሰባቱን የፕሊዬዲስ ከዋክብት የሚመራው | መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

በ8ኛው ወር በሚያዝያ፤ በ22ኛው ቀን፤ ትንሣኤን የሚወክለውና ሰባቱን የፕሊዬዲስ ከዋክብት የሚመራው ሰውር (ታውረስ) ከፀሐይ ጋር በሚውልበት ዕለት ተወለድኩ።
በጌታ ቀኖት የተሰየመው የዚህ ሮዳስ DNA ሲመረመር "ያህዌህ" የሚለው ስመ አምላክ (10 - 5 - 6 - 5) ብቻ ነው።
ሁሉንም የምድር ወላጆቹን በመተው አባቱ ኢየሱስ ብቻ፤ እናቱ ማርያም ብቻ፤ ወዳጁ ጥበብ፤ ሀገሩም ሰማያዊ እንደሆነ በሚገባ ተረድቷል።
አልፋ ዖሜጋ ፈጣሪው በሰጠው ባለፈው ዓመቱ 888 የሚለውን 26ኛ መጽሐፉን አሳትሞ አስመርቆ ለአንባብያን ሰጥቷል።
የሚያበራ የንጋት ኮከብ፣ የይሁዳ አንበሳ ጌታው ክርስቶስ ብቻ በሚሰጠው በቀጣይ የ365 ዕለት ዑደታዊ ጉዞው በፈጣሪው ቸርነት 27ኛ መጽሐፉን ለትውልድ ያስቀምጣል።
መልካም ልደት በሉት፤ ባትሉትም አይከፋውም።
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)