Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 175.28K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 388

2022-05-19 22:29:59
"#ፑቲን እባክዎትን የሚራራ ልብ ካለዎት ወደቦቹን ይክፈቱና ደሃዎችን እንመግብ አስከፊውን ርሃብም እናስቁመው" :- የአለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሌይ

ምእራብያውያን ፑቲንን መለማመጥ ጀምረዋል።

ፑቲን የዩክሬን ወደቦችን ለእህል ጭነት ክፍት እንዲያደርጉ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ጠይቋዋል። ጉዳዩ ብዙዎችን ለርሃብ ከመዳረግም በላይ አለመረጋጋቶችን ሊያስከትልና የህገ ወጥ ስደተኞን ቁጥር ሊያንር እንደሚችል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ፕሮግራሙ ወደቦቹ ካልተከፈቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለከፋ ርሃብ ሊጋለጡ ይላሉ ብሏል፡፡ ይህን አለመፍቀድ በዓለም የምግብ ዋስትና ላይ "የታወጀ ጦርነት" ተደርጎ ይወሰዳልም ብሏል ፕሮግራሙ።እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ዩክሬን ብቻዋን 4 መቶ ሚሊዮን ያህል ሰዎችን ለመመገብ የሚያስችል አቅም አላት ብለዋል።
15.2K views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 22:26:49 ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ስልጣናቸውን በመጠቀም የሕወሓትን አላማ ማስፈጸማቸውን እንዲያቆሙ ተጠየቀ

#Ethiopia : የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ስልጣናቸውን በመጠቀም የሕወሓትን አላማ ለማስፈጸም የሚያከናውኑትን ተግባር እንዲያቆሙ ዘጠኝ ተቋማት ለዳይሬክተሩ በጋራ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ጠየቁ።

ደብዳቤውን የጻፉት የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር፣ የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር፣ ’አሜሪካን ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቴ’(ኤፓክ)፣ ’ኢትዮጵያን ዳያስፖራ ሃይ ሌቭል አድቫይዘሪ ካውንስል ኦን ኮቪድ-19’፣ ’ኢትዮጵያን ስኮላርስ ኢን ኖርዲክ ካንትሪስ’፣ የደቡብ አፍሪካ የሕክምና ማህበር፣ የሌሴቶ ሕክምና ማህበር እና ‘ፒፕል ቱ ፒፕል’ የተሰኙ ተቋማት ናቸው።

በሰሜን ኢትዮጵያ ባለፈው 18 ወር በነበረው ግጭት የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ፖለቲካዊና ግልጽ ወገንተኝነት ያለው አካሄድን መከተላቸውን ተቋማቱ ገልጸዋል።

በንግግርና በድርጊታቸውም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ የተሳሳተና የተዛባ አቋም እንዲይዙ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በሚሰጧቸው መግለጫዎች፣ በሚጽፏቸው ጽሁፎችና በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች ሕወሓት በአማራና አፋር ክልሎች በፈጸመው ድርጊትና በሕዝብ ላይ ባደረሰው መከራ ላይ ዝምታን መርጠዋል ብለዋል።

ሕወሓት በፈጸመው ወረራ በርካታ የጤና ተቋማትን ማውደሙንና መዝረፉን አስታውሰው፤ ቡድኑ ንጹሃንን በመግደልና አስገድዶ በመድፈር ወንጀሎችን መፈጸሙን አመልክተዋል።

ዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ ሕወሓት በክልሎቹ የፈጸመውን ድርጊት በሚያወጡት ሪፖርት እየገለጹ በሚገኙበት ወቅት ዶክተር ቴድሮስ በጉዳዩ ላይ ያሉት ነገር አለመኖር አድሎአዊነታቸው ለአንድ አካል የሚያሳይ እንደሆነ ነው ተቋማቱ በደብዳቤው ላይ የገለጹት።

ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር እንዲሰሩ በተደጋጋሚ ጊዜ ለሚቀርብላቸው ጥሪ ምላሽ አለመስጠታቸው የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል።

ሕወሓት ወደ ትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ እየተደረገ ያለውን ጥረት እያደናቀፈ እንደሚገኝ የጠቀሰው ግልጽ ደብዳቤው፤ ዶክተር ቴድሮስ በአሜሪካ በነበራቸው ጉብኝት ከባለስልጣናትና ከሕግ አውጪ ምክር ቤት አባላት ጋር ያደረጉት ውይይት አላማው በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ለመጎትጎት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ጉብኝቱ የ’ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ሕጎች እንዲጸድቁ ግፊት ለማድረግ መሆኑን እንረዳለን ነው ያሉት ተቋማቱ።

ዶክተር ቴድሮስ የዓለምን ሕዝብ ጤና ለመጠበቅ የተሰጣቸውን ኃላፊነት የሕወሓትን አላማ ለማስፈጸም እየተጠቀሙበት ነው፤ ከዚህም ድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል።

አፍራሽ የፖለቲካ እንቅስቃሴና የዘር ውግንናቸውን በመተው በሁሉም ኢትዮጵያውያን ጤና መጠበቅ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ተቋማቱ ጠይቀዋል።

ዘጠኙ ተቋማት በአማራና አፋር ክልሎች በሕወሓት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ በማቋቋምና ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በሥነ ምግባር ጥሰት እንዲጠየቁ በጥር ወር 2014 ዓ.ም ለድርጅቱ የበላይ ጠባቂ ቦርድ የቅሬታ ማመልከቻ ማስገባቱ ይታወሳል።

በማመልከቻው ላይ የኢትዮጵያ መንግስት በዋና ዳይሬክተሩ ላይ የሕግ እና የሙያዊ ሥነ ምግባር እንዲሁም የሞራል ጥያቄዎች እንዳሉት ገልጿል።

ዶክተር ቴድሮስ ለአንድ ወገን የያዙት አድሏዊ አቋም ከፍተኛ ኃላፊነት በያዙበት ቦታ ያላቸውን ሙያዊ ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚከተው በማመልከቻው ላይ ተጠቅሷል።

በኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበውን ቅሬታ አስመልክቶ የዓለም ጤና ድርጅት እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም።
15.7K views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 22:13:29

16.2K views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 19:39:52 ለሚመለከተው ክፍል ጥቆማ

አቶ ናትናኤል ሰላም ለአንተ ይሁን ዛሬ ለአንተ ለማድረስ የፈለግኩት ጉዳይ ከሳርቤት (ፑሽኪን አደባባይ)ወደ ጎተራ ማሳለጫ የሚወስደው መንገድ ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለምዶ ከጎፋማዞሪያ ወደ መብራትኃይል እንዲሁም ከጎፋማዞሪያ ወደ ጨርቆስ እየተሰራ ያለው መንገድም በከፊል እየተጠናቀቀ ይገኛል ነገርግን የተሰራው ስራ ጥሩ ቢሆንም በቀጣይ የመንገዱን እድሜ የሚያሳጥር አካባቢውንም ወደፊት በጎርፍ እንዲጥለቀለቅ የሚያደርግ ስራ እየተከናወነ ነው ይህም የመንገዱን ስራ የሚቆጣጠር ሃላፊ የሌለ በሚመስል መልክ አዲስ የተሰሩ የፍሳሽ መስመሮች (ፖሴቲዎች)ከአፍ እስከ ገደፋቸው ድረስ (ሙሉበሙሉ) በኮረትና በድንጋይ እንደተሞላ ክዳን እየተገጠመላቸው ነው ። በአካባቢው በቅርብ ርቀት ላይ ያሉ የወረዳ አመራሮች ሳያዩ ቀርተው ነው ብዬ ለማመን ይቸግረኛል ባለቤቱ ማነው አቶ ናትናኤል ባንተ በኩል መድረስ ከቻለ ክረምት ከመግባቱ በፊት እንዲስተካከል ቢደረግ ። እንደለመደብን ጨረስን ብለን በማግስቱ ወደ ቁፋሮ እንዳንገባ በህዝብና በመንግሥት ገንዘብ መቀለድም እንዳይሆን ብዬ ነው ።
30.5K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 17:39:20
የዚምባብዌው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቸው ኮ/ል መንግስቱ ሀይለማርያምን ለኢትዮጵያ አሳልፋ ልትሰጥ እንደምትችል ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ላይ ገልጸዋል:: "የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት የዚምባብዌ መንግስትን ቀርቦ ጥያቄ ካቀረበ አስፈላጊው እርምጃ ተወስዶ ተገቢው ጥያቄ መልስ ያገኛል" ነው ያሉት የዚምባብዌው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ኮረኔል መንግስቱ ሆይ የዚምባቤ መንግስት ለኢትዮጵያ አሳልፋ እስኪሰጥህ አትጠብቅ በገዛ ፍቃድህ ወደ ምትወዳት ሀገርህ ከነቤተሰብህ በመግባት ቀሪ እድሜህን በሀገርህ ላይ አሳልፍ
35.0K views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 15:07:13 ‘’አዳዲስ አስተሳሰብና አሰራሮችን በመተግበር መከላከያ ሰራዊቱን በሁለገብ መልኩ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡’’ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር አብርሀም በላይ

#Ethiopia : የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ለሰራዊቱና ለሲቭል ሰራተኞቹ ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንት የዕጣ ማውጣትና የርክክብ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የመከላከያ ሚንስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ የመከላከያ ሰራዊታችንን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት ወደተግባር መገባቱን አረጋግጠዋል፡፡

ሀገርን በመስዋዕትነቱ እያስከበረ የሚገኘው ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችንን ተጠቃሚ ለማድረግ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ሚንስትሩ በጦርነት ውስጥ ሆነን ገንብተን ያጠናቀቅነውን የመኖሪያ ቤት ተቋሙን ላገለገሉ አባላት መተላለፉ አንዱ የለውጥ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜ/ጄ ኩምሳ ሻንቆ ፋውንዴሽኑ በኢንዱስትሪና በእርሻ ከመሰማራቱ በተጨማሪ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ውስጥ በስምንት ሳይቶች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት የሰራዊቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

በሰሚት ሁለት የጋራ መኖሪያ አፓርታማ ስለደረሳቸው መደሰታቸውን የገለጹት ሌ/ኮ ዘላለም ማሞ በቀሪ ዘመናቸው ሀገራቸውን ለማገልገል የበለጠ ተነሳሽነት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡

ሌላው ያነጋገርናቸው በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ለረጅም አመት አገልግገለው በጡረታ ላይ በመሆን በቤት ክራይ ይኖሩ የነበሩትና የእድሉ ተካፋይ የሆኑት ሻምበል መክብብ መኮንን ለረጅም ዘመን ያገለገልኩት ተቋም የቤት ባለቤት ስላደረገኝ ደስ ብሎኛል ብለዋል፡፡

በዕለቱ ሙሉ እድሳታቸው የተጠናቀቁ 529 ከባለአንድ እስከ ባለኣራት መኝታ ቤቶች ዕጣ ለወጣላቸው የሰራዊት አባላትና የሲቭል ሰራተኞች ተላልፏል፡፡
37.3K views12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 15:07:03
ናሽ የጥርስ እና የዓይን ህክምና ክሊኒክ
        Nash Dental and Optometry Clinic
 
ናሽ የጥርስ እና የዓይን ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስና የአይን ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢  
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
 
➢ የረዥም እርቀት፤ የአጭር እርቀት እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የቅርብ እይታ መቀነስ ምርመራ እና ህክምና
➢ ሁለት ዓይኖች ተቀናጅተው ያለመስራት ችግር ምርመራ እና ህክምና
➢ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት የእይታ መቀነስ ችግርን ምርመራና ህክምና
➢ የህፃናት የአይን ምርመራና ህክምና
➢ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የአይን መነጽሮች የሎው ቪዥን ድጋፍ መስጫ የቪዥን ቴራፒ መሳሪያዎች መለካት ማስተካከል እና ማዘዝ
 
 
በሁሉም የህክምና አይነቶች ቅናሽ አድርገናል
      አድራሻ: ቁጥር 1 ሜክሲኮ ገነት ሆቴል ፊት ለፊት ካሳ ግራንድ ሞል 4ኛ ፎቅ
                       ቁጥር 2 ሰሚት ሳፋሪ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ገሊላ ፕላዛ
                       Tel: 0905262626, 0913858561
32.3K views12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 13:50:12

31.7K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 13:32:37
መልክት ከአዲስ አበባ ሞተረኞች

ናቲ በመጀመሪያ አመሰግናለሁ አዲስ አበባ መንገድ ትራንስፓርት ከሁለት አመት በፊት ሙሉ ለሙሉ እንዳንቀሳቀስ ክልክሎን ነበር ግን እነሱ ያወጡት ህግ ትክክል እናደልሆነና እኞን የሚጎዳ በዚህ የስራ ዘርፍ አብዛኞቻችን ቤተሰብ አስተዳዳሪ እንደሁንን ቅሬታ አቅርበን ወደ ስራ እንድንገባ ህግ አውጥተው አርገውን ነበር

ለምሳሌ ከህጎች ውስጥ

1 ሞተሮቹ ጂፒኤስ እንዲገጥሙ
2 ኮድ 2 የሆንቱ ሞተረች ኮድ 3 እንዲሆኑ
3 ለቁጥጥር እንዱያመች በማህበር እንዲሆኑ ሌሎችም ህጉ አሉ እነዚህን መስፈርቶች አሟልተን ወደስ ስራ ገባን ግን በተደጋጋሚ ያስቆሙናል አህን ደግሞ ጭራሽ ሰው ጭነን እንዳንሰራ አርገውናል ናቲ ቤተሰብ አለን ግብር እንክፍላለን ለጂፒኤስ በአመት 3000-4000ብር ለቁጥጥር እንክፍላክለን ትናንት ፋና ሄደን ነበር የሄድነውም ቅሬታችንን ለሚመለክተው አካል እንዲያደርሱልን መፍቴሄ እንዲሰጠን ነውና መፍትሄ እንድሰጡን ድምጻችንን አሰማልን::
31.9K views10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 12:56:41 የአያት መንደር ነዋሪዎች ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ እየፈረሰ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍል ከተማ አያት መንደር የዞን 8 ነዋሪዎች ሕጋዊ ካርታ አውጥተው ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ ያለ ምንም ማስጠንቀቂና ሕጋዊ ማስረጃ በትራክተር እየታረሰ መሆኑን ፓርኩን ያለሙት የመንደሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ ከሆነ ከ15 ዓመት በላይ ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ ወይም ፓርክ ከነዋሪዎች በተዋጣ ገንዘብ በአረንጓዴ ልማት የተሸፈነ ነው፡፡

ይሁን እንጅ ዛሬ ማለዳ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘን ነው የመጣነው ያሉ ፖሊሶች ከ20 እስከ 30 የሚደርሱ ሰራተኞችና አንድ ትራክተር አሰማርተው ፓርኩን እያፈረሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ሕጋዊ ካርታ አውጥተው ከ15 በላይ በመናፈሻነት የተጠቀሙት ፓርክ እንደሚፈርስ ምን አይነት ማስጠንቀቂያም ይሁን መረጃ እንዳልተሰጣቸውም ጭምር ነው የተናገሩት፡፡

የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘን ነው የምናፈርሰው ያሉት የመንግሥት አካላት ማዘዣውን ለፓርኩ ባለቤት ለሆኑት ነዋሪዎች እንዲሳዩ ቢጠየቁም የፍርድ ቤት ማዘዣ ማሳየት አልቻሉም ተብሏል፡፡

Via Addis Maleda
31.0K views09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ