Get Mystery Box with random crypto!

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™
የሰርጥ አድራሻ: @mentalcounsel
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.06K
የሰርጥ መግለጫ

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-06-03 07:20:55
2.7K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 20:36:02 ቁልፉ አንተ ጋር ነው!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
ታዋቂው የማርሻል አርት ባለሙያ ብሩስ ሊ (Bruce Lee) የሚታወቅበት አንድ ድንቅ አባባል አለው። "ለነገሮች ዋጋ እየሰጠን በሄድን ቁጥር የእራሳችንን ዋጋ እናጣለን። ሌሎችን በተደገፍን ቁጥን ለእራሳችን መሆን ያቅተናል።" ለምንም ነገር ዋጋ ለመስጠት የእኛ ዋጋ እጅግ ወሳኝ ነው። በሌሎች ዘንድ ዋጋ እንዲኖርህ ከፈለክ ያለምንም ቅድመሁኔታ ለእራስህ ዋጋ ልትሰጥ ይገባል። ብዙ ነገሮች የሚመጡት የሚሔዱት አንተ ስላለህ ነው። ሁኔታዎችን አንተ ትፈጥራቸዋለህ እንጂ እነርሱ አይፈጥሩህም፤ ከሁኔታው በላይ እንደሆንክ ለማሳየት ስልጣንህን ማሳየት ግድ ይልሃል። ከማንም ምንም አለመጠበቅ ሊከብድህ ይችላል፤ ነገር ግን በጥቂቱም ቢሆን ያንን የምትጠብቀውን ነገር ለእራስህ ማድረግ እንደምትችል ማወቅ ይኖርብሃል። እንዲወዱህ ከፈለክ አስቀድመህ እራስህን ውደድ፤ ትኩረት መሳብ ከፈለክ እስቀድመህ እራስህ ላይ ትኩረት አድርግ።

አዎ! ጀግናዬ..! ቁልፉ አንተ ጋር ነው! የጫወታውን አቅጣጫ በፈለከው መንገድ መቀየር ትችላለህ። ከሰዎች አገኘዋለሁ፣ ቁስ ውስጥ አለ፣ ሁኔታዎች ያመቻቹልኛለህ ብለህ የምታስበው ነገር መነሻው ያንተ አስተሳሰብና አቋም እንደሆነ እወቅ። ትኩረትን ፍለጋ ብዙዎች ላይ ታተኩራለህ፤ ብዙዎችን ጥብቃ ብዙ ትጠብቃለህ፤ ማረጋገጫ ፍለጋ ብዙዎችን ደጅ ትጠናለህ። በቁስ መከበብ፣ በሰዎች መደነቅና መሞገስ የዘወትር መሻትህ ከሆነ በፍፁም ብቸኝነትህን ልትወደው አትችልም። እራስህ ለእራስህ የምትሰጠውን ዋጋ ካልጨመርክ የማንንም አይን ልትሞላ አትችልም፤ ለእራስህ የሚገባህን ክብር ካልሰጠሀው ከማንም የምትፈልገውን ክብር አታገኝም፤ ለእራስህ ውስጣዊ ሰላም፣ ለእራስህ መረጋጋት፣ ለእራስህ ጤና ቅድሚያ ካልሰጠህ እንዴትም በእራስህ ልትደሰት አትችልም። ለእራስህ የምትሰጠው ቦታ በሌሎች ዘንድ የሚሰጥህን ስፍራ የመወሰን ትልቅ ሃይል አለው።

አዎ! ማንም ምንም ስለሆነ በስሜትህ መጫወት አይችልም። ዋናው ቁብነገር ባንተ ዘንድ የሚሰጠው ስፍራ ነው። አብዝተህ ቦታ ከሰጠሀው፣ ካልተንከባከብኩህ፣ አብሬህ ካልሆንኩ፣ ካልተደገፍኩህ ካልክ ስህተቱ የእራስህ ነው። አምኖ መከዳት አዲስ አይደለም፤ ተደግፎ መሰበር የተለመደ ነው። የክህደቱ ባለቤት ሌላ አካል ቢሆንም ከዛ ቦሃላ የሚመጣውን ጉዳት ለመቀበል ግን እራስን ብቁ ማድረግ ይገባል። ከሃጂው ሊጨንቀው ሲገባ በመከዳትህ በእራስህ ካዘንክ በፍቃድህ ዋጋህን እያሳነስክ ነው። የተደገፍከው ነገር ተሰባሪ እንደሆነ ካወክ እራስህን ችለህ መቆም ለምርጫ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። እራስህን ቻል፤ እራስህን አስከብር።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.4K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 13:18:36 በየቀኑ በማዳመጥ አስደሳች፣ የተረጋጋና ሰላማዊ ቀንን አሳልፉ! 

በአዎንዊ አስተሳሰብ እራሳችሁን አድሱ
ውጤታማ ልማድን አዳብሩ
ለህይወታችሁ ትርጉም ስጡት

LIKE COMMENT SUBSCRIBE SHARE




3.3K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 07:26:17 እንቆቅልሾችህን ፍታ!
፨፨፨፨//////////፨፨፨፨
ሩቅ መጓዝ፣ ተዓምር መስራት፣ ድንቅ ማድረግ ከፈለክ ምርጫ በሌለው አማራጭ እንቆቅልሾችህን ፍታ፤ አስጨናቂዎችህን አስወግድ፤ መሰናክሎችህን ተሻገር፤ ከእንቅፋቶችህ ራቅ። ፍረሃት፣ ጭንቀት፣ አሉታዊነት፣ ሰበበኝነትና መጥፎ ልማዶች ዋንኞቹ እንቆቅልሾችህ ናቸው። ፈሪ ተዓምር ሲሰራ ያያል እንጂ ተዓር መስራት አይችልም፤ የሚጨነቅ ሰው ድንቅ ሲደረግ ይመለከታል እንጂ ድንቅ የሚያደርግ ማንነት አይኖረውም፤ ሰበበኛ እንቅፋቶቹን ይቆጥራል እንጂ በረከቶቹን አይመለከትም። በእንቆቅልሾችህ ተከበህ ተዓምረኛ ሳይሆን መደበኛውን ህይወትም ለመምራት ልትቸገር ትችላለህ። ሩቅ መጓዝ የሚፈልግ ሰው የመንገዱ ምቾት ሊያሳስበው ይገባል፤ ትልቅ ህልም ያለው ሰው በማንነቱ ላይ የሰለጠኑ ባህሪያትን ለይቶ ማወቅ ይጠበቅበታል፤ በተዓምረኛነቱ የሚተማመን ሰው መሰናክሎቹን ለማስወገድ ደፋርና ቁርጠኛ መሆን ይኖርበታል።

አዎ! ጀግናዬ..! እንቆቅልሾችህን ፍታ! በውስጥህ የያዝከውን ሸክም ልቀቅ፤ ከሚረብሹህ አስተሳሰቦች ተላቀቅ፤ ወደኋላ ከሚያስቀሩህ እሳቤዎች ነፃ ውጣ። በጨለማ መጓዝ አትችልምና ብረሃንህን ፈልገህ አግኘው፤ ከአሉታዊ ሰዎች ጋር ግብህን አትመታምና ከአዎንታዊዎቹ ጋር ተወዳጅ፤ የሚደግፉህንና የሚያበረታቱህን ምረጥ። መጥፎ ልማዶችህ ሳይቀየሩ ህይወትህን ስለመቀየር ብታስብ ከጭንቀትና መብሰልሰል በቀር የምታተርፈው ነገር የለም። ካንተ ብዙ ከሚጠብቁብህ፣ ዘወትር እጅ እጅህን ከሚያዩ፣ ከሚበዘብዙህ፣ ለእኔ ብቻ እንጂ ላንተን ከማያውቁ ሰዎች ጋር ሆነህ ለእራስህ ልትተርፍ አትችልም።

አዎ! ሩቅ አሳቢ ለትናንሾቹ ተግባሮቹ ትኩረት ይሰጣል፤ ጥቃቅን ክፍተቶቹን በጥንቃቄ ይሞላል፤ ላልተመቸው ጉዳይ በጊዜ መፍትሔ ይሰጣል፤ ከማይረዱትና ከማይደግፉት ሰዎች ለመነጠል ጊዜ አያጠፋም። ለእራስህ መሆን ካልቻልክ እንዲሁ እንደ ሸንኮራ ታኝከህ ትተፋለህ፤ እራስህን ካላስከበርክ መሳቂያ መሳለቂያ ትሆናለህ፤ ለህልምህ ዘብ ካልቆምክ በተራነትህ መዘባበቻና መሳለቂያ ትደረጋለህ። ልዩ ሃሳብ እንዳለው፣ ባለትልቅ ህልም ባለቤት እንደሆነ፣ ከፊቱ ትልቅ ስኬት እንደሚጠብቀው፣ ለራዕይው ከማንም በላይ እንደሚያስፈልገው ሰው ኑር። ቁጥብነትህ ሳቅ ጫወታን ጠልተህ አይደለም፤ ጥንቃቄህ አደጋዎችህ በዝተው አይደለም፤ ህልምን የመኖርን መንገድ ቀላልና የተደላደለ ለማድረግ በማሰብ ነው። እንቆቅልሾችህን ፍታ፤ በፍጥነት ወደ መዳረሻህ ተጓዝ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.4K views04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 07:25:14
2.9K views04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 20:33:01 ... አንተም አትኖርም!
፨፨፨፨//////////፨፨፨፨
ሰዎች ከታሪካቸው ይቀዳሉና ታሪክህ ባይኖር አንተም አትኖርም፤ ያሳለፍከው መጥፎም ሆነ ጥሩ ነገር ባይኖር የዛሬው አንተም ባልነበርክ ነበር። ብዙዎች ብዙ የሚያልፍ የማይመስል ስቃይን አሳልፈዋል፤ ዛሬ በዛው አስከፊ ህመም ውስጥም ያሉ ሰዎች ይኖራሉ። ነገር ግን የሁኔታው ክብደትና ፋታ መንሳት ከማለፍ አይከለክለውም። ሁሉም በጊዜው ይታለፋል፤ ታሪክ ይሆናል። ትናትህን ባታልፍ ዛሬህን ባለየህ ነበር፣ ዛሬንም ካላለፍክ ነገን ልታየው አትችልም። ዛሬ ምንም ሊገጥምህ ይችላል፣ አሁን በየትኛውም አስከፊና አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ልትሆን ትችላለህ። አንድ ነገር ግን አስታውስ:- ከዚህ ከባድ ጊዜና ሁኔታ በተሻለ ሊሰራህና ብቁ ሊያደርግህ የሚችል አጋጣሚ የለም። መከዳትን፣ መገፋትን፣ መጠላትን የሚወድ የለም፤ ባይወደውም ግን ሊያልፍበት ግድ ነው። በመንገዱም መሰራቱ የግድ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! መሆን የሚገባህን ሰው እስክትሆን መሰራት ያለበት ስራ ይሰራል። አንቺን የምትመጥንሽ ሴት እስክትፈጠር ስቃዩ ይቀጥላ፤ ለቅሶሽ አያበቃም፤ ህመምሽ አይድንም። መልቀቅ ሲገባሽ አጥብቀሽ የያዝሽው እሾህ እስክትለቂው ድረስ እጅሽን መውጋቱንና ማድማቱን አያቆምም። እሾሁን ይዘሽ ለህመምሽ ሌላ ተወቃሽ አትፈልጊ። ድህነትሽ በእጅሽ እንደሆነ አስተውይ። ነገር ግን እርሱም ቢሆን በበቂ ሁኔታ ካላስተማረሽና ብቁ ካላደረገሽ በፍፁም አይተውሽም። ተዓምር የሚመስል ታሪክ አሳልፈሽ ተራ ህይወት አትኖሪም፤ ከባዱን ትናንት አልፈሽ መደበኛ ህይወት አትኖሪም። የጣለሽ መሰናክል የውድቀትን ህመምና ዳግም የመነሳትን ክብደት በሚገባ ያስተምርሻል፤ መከዳትሽ፣ በሌላ መተካትሽ የሰዎችን ለስሜታቸው መገዛትን ያስገነዝብሻል። ታሪክሽም ሆነ አሁንሽ አስተማሪ ነውና የተሻለችውን አንቺ ፍጠሪበት።

አዎ! ትናንትህ፣ የቀደመ ታሪክህ፣ ያለፈ ስቃይና ብሶትህ ባይኖሩ አንተም አትኖርም። አንተ ማነህ? የሚጨበጥ የሚዳሰሰው፣ አይን አፍንጫ አፍ እግር እጅ ያለው አካልህ አይደለህም። አንተ መንፈስህን ነህ፤ ስሜትህን ነህ፤ ማንነትህን ነህ፤ ስብዕናህን ነው። አካልህ ቢገድብ አስተሳሰብህ አይገደብም፤ ሰውነትህ ቢታሰር አዕምሮህ አይታሰርም፤ እጅ እግርህ ቢጎዳ ማመዛዘን አታቆምም። ይህን ገደብ አልባው ማንነት ደግሞ አንተ ነህ። በታሪኮችህ ተሰርተሃል፤ በውጣውረዶችህ ተገንብተሃል፤ በከፈልከው ዋጋ ለዚህ በቅተሃል። አሁን ከሁለት አንዱ ሰው መሆንህ አይቀርም። አንድ ታሪክህ የሰራህ፣ ሁለት ታሪክ እየተሰራብህ ያለህ። ሁለቱም በጊዜያቸው እጅጉን በጣም አስተማሪና የሚያንፁ ናቸው። ታሪክህ ቢሰራህ ዳግም የቀድሞ ስህተትና ስቃይ ውስጥ የመግባት እድልህ ይቀንሳል፤ ታሪክ ቢሰራብህ አዲስ ማንነት እየተሰራ እንደሆነ አስበህ ሁኔታዎቹን አምነህ መቀበልና ከእነርሱ መማር ይኖርብሃል።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.5K views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 16:08:38 ከምንጊዜውም በላይ የብቸኝነታችሁን ሃይል መጠቀም ያለባችሁ አሁን ነው! ለእርሱም ይህ ቪድዮ ይጠቅማችኋል!

ብቻችሁን ተዓምር ፍጠሩ
በእራሳችሁ ቀለም ድመቁ
ለሆናችሁት ማንነት ማንንም ይቅርታ አትጠይቁ

LIKE COMMENT SUBSCRIBE SHARE




3.4K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 20:27:01 ሁሉም ይቀራል!
፨፨፨///////፨፨፨
የማይታለፈውን ለማለፍ ምንም ታደርጋለህ፤ የትምህ ትገባለህ፤ ምንም ትሰራለህ። ልፋትህ ቀን ቆጥሮ የሚከፍልህ ጊዜም ሩቅ አይሆንም። ጠንካራው አልማዝ በእሳት ይፈተናል፣ ከእራሱ ከአልማዝ በቀር የሚቆርጠው እንደሌለ አድርጎም ይጠነክራል። ህይወትም በዚሁ አሳቤ ብዙ ትፈትንሃለች። ብቻህን ስትሆን ሁሉንም ታስታውሳለህ። ከሰው ጋር ቀልድ እንደምታበዛው፣ እንደምትስቀው፣ እንደምትጫወተው አይደለም። እያንዳንዱን ነገር እንደ ቁብነገር ትመለከተዋለህ፤ ትጨነቃለህ፤ ትሰቃያለህ፣ ትሳቀቃለህ። ነገር ግን መቼ፣ እንዴት ይህን ምድር እንደምትለይ አታውቅም። ስትለፋለት የነበረው ቤት ይቀራል፤ ሲያስጨንቅህ የነበረው ጉዳይ ይቀራል፤ እንቅልፍ የነሳህ ነገር ይተዋል። ብዙ ነገር እንደሚያልፍ፣ ህይወትህም እንደሚሻሻልና የሚገባህን ነገር እንደምታገኝ ብታስብም አንተ ልትቀድመው ትችላለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉም ይቀራል፤ አንተ ከሌለህ የሚኖር ነገር የለም፤ አንተ ካልኖርክ የምትጓጓላቸው፣ የምትናፍቃቸው፣ የምትመኛቸው፣ የምትታገልላቸው ነገሮች በሙሉ ምንም ናቸው። እግዚአብሔር ሲፈቅድ ሁሉም ይሆናል፤ ፈጣሪ ባለው መንገድ ሁሉም ይከናወናል። እነሆ ዘላለም እንደሚኖር፤ ዘወትር በምድር ላይ እንደሚመላለስ ሰው አትኑር። ህይወት አጭር ነች። ጊዜህ ሲደርስ አምላክ ይጠራሃል። እያየህ ስንቶች ጥለውህ ሔዱ፣ ስንት አስከፊ መርዶ ሰማህ፣ ስንቱስ ለስራ በወጣበት ቀረ። ይህም ከማዘን በላይ ሌላ ምርጫ እንዳይኖርህ ቢያደርግህም ነገር ግን በሚገባ ያስተምርሃል፤ እራስህን መጠበቅ እንዳለብህ ያስገነዝብሃል፤ ለመኖር ሌላ እድል እንደሌለህ ያሳውቅሃል።

አዎ! በህይወት እስካለህ ብዙ ያልጠበከው ነገር ይደርስብሃል፤ የማትጠብቀውን ሰው ታጣለህ፤ ባላሰብከው ሰዓት ብቻህን ትቀራለህ። ነገር ግን ያንተ መኖር እጅግ በጣም ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ እወቅ። ወንድም እህቶችህ ቢለዩህ ያንተ በሀይወት መኖር ዋጋ አይተመንለትም። መኖርን ቀልድ አታድርገው፤ ጤናህን ዋጋ አታሳጣው፤ በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባትን አታቅልለው። ተመስገን ማለት የአባት ነው፤ ባለህ መደሰት፣ በተስፋ መኖር፣ በአምላክ ፍቃድ መመራት ትልቅ ነገር ነው። ከህልም፣ ከራዕይ፣ ከአላማ፣ ከስራ፣ ከምግብ በፊት ያንተ መኖር ዋጋ እንዳለው እወቅ። ውድ ነገር እያለ ውድነቱ አይታወቅም ሲጠፋና ስታጣው ግን ይገለጥልሃል። ህይወት ግን ከውድም በላይ ነችና ይህን እድልም አትሰጥህም። እያለህ በሚገባ ኑራት።

መታሰቢያነቱ፡ ዛሬ 12/09/2015 ዓ.ም በትራፊክ አደጋ ለተለዩን የመደወላቡ ዩኒቨርሲቱ ውድ መምህርን
ለቤተሰቦቻቸውና ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።
ነፍስ ይማር!
የሰላም ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
1.2K views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 20:26:43
1.1K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 07:49:35 ሁሉም አለው!
፨፨፨/////፨፨፨
ሁሉም ሰው የሚያፍርበት ታሪክ አለው፤ ሁሉም የሚያስጨንቀው፣ የሚያሳምመው ጉዳይ አለው። እንዲ ለብሶ ዘንጦ ሲታይ ምንም ችግር የሌለበት ይመስላል፤ ሰው ላይ ጣቱን ለመቀሰርና ለመፍረድ ሲፈጥን እርሱ ንፁና ነውር የሌለበት ይመስላል። ነገር ግን ችግሩን እርሱና አምላኩ ያውቁታል። ሰው ፊት ጨዋና ምንም የማያውቁ ይመስላሉ ነገር ግን ልባቸው ሌላ ነው፤ ውስጣቸው የተለየ ነው። በማስመሰል ድግግሞሽ ስንተ የሚሰቃይ ሰው አለ። አንተ ብቻ ሰነፍ እንደሆንክ፣ እንደማትችል፣ ትልቅ ቦታ እንደማትደርስ ይነግሩሃል እራሳቸው ግን ካንተ በታች መሆናቸው አይገነዘቡትም። አብዛኛው ሰው ያንተን ድክመትና ችግር አጉልቶ በማውራት የእራሱን ድክመትና ችግር ለመሸፈን ይሞክራል። ነገር ግን ህይወት እንደዚህ አትገፋም። ሁሉም ሰው የገዛ ሸክም አለው፤ አንተም አንዱ የእራስህ ሸክም ያለብህ ሰው ነህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉም አለው! የትም ብትሔድ ከችግር የፀዳ፣ ድክመት የሌለበት፣ ክፍተት የማይታይበት ሰው የለም። የልቡን በልቡ ይዞ፣ ጭንቀቱን በጉያው ሸክፎ ያንተን ችግር ለማጉላት ቢሞክር አትገረም። አንተን እያየ ባንተ ለመፅናናት በሚያደርገው ጥረት ካንተ ተወዳድሮ አንድ ቀን መውደቁ አይቀርም። የእራሱን እሾህ ትቶ በባልንጀራው ላይ ያለውን ጉድፍ የሚመለከት ሰው ከማንም በላይ እራሱን ጠልፎ ለመጣል የተዘጋጀ ሰው ነው። ለእራስህ መሰናክል ካልሆንክ እንቅፋቶችህን ማስወገድ አይከብድህም፤ እራስህን ካወክ፣ ያለህበትን ከተረዳህ መዳረሻህ አይጠፋህም። ሸክምህን ለማውረድ፣ ችግርህን ለመቅረፍ፤ ክፍተትህን ለመሙላት በምታደርገው ማንኛውም ጥረት ምክንያት በሚደርስብህ ተፅዕኖ እንዳትሰበር፤ አንገትህን እንዳትደፋ።

አዎ! ይህን ያክል ውስብስብ አይደለም። ውድቀትህን ስለፈለጉ ብቻ አይጥሉህም፤ ዘወትር ችግርህን ደጋግመው ስላወሩ ብቻ ችጋራም አያደርጉህም፤ ተከታትለው ክፍተትህን ብቻ ስለነገሩህ ጠንካራ ጎንህን አያጠፉትም። እራስን በማወቅ አለም ውስጥ ከሚሉህ በተሻለ የሆንከውን ተቀበል፤ ከሚለጠፍብህ አሉታዊ ስም ባሻገር የሚገልፅህን አዎንታዊ ማንነት አጉልተህ አሳይ። እንደ ማነፃፃሪያና እንደ ሚዛን ስለተወሰድክ ብቻ ከደረጃህ ወርደህ፣ ቀለህ አትገኝ። ብቻህን ፈተና እንደተደራረበብህ፣ መፈናፈኛ እንዳጣህና ዋጋ እንደሌለህ አታስብ። ያንተን ጉዳይ ለእራስህ እንዲተዉት አድርግ። የእራሱን የማያልቅ ችግር ይዞ ያንተን ጉዳይ አጉልቶ ለመተንተን የሚሞክርን ሰው አትስማ። ሁሌም ቢሆን ያንተ ጉዳይ የሚፈታው ባንተና ባንተ ብቻ እንደሆነ ተረዳ።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.1K views04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ