Get Mystery Box with random crypto!

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™
የሰርጥ አድራሻ: @mentalcounsel
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.06K
የሰርጥ መግለጫ

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-06-10 07:30:03
2.1K views04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 22:09:47 Live stream finished (1 hour)
19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 22:06:07 #LIVE_PODCAST እንዴት ነበር?
ሃሳብ አስተያየት ፃፉልን።
2.6K views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 21:00:48 Live stream started
18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 20:14:37 ምንድነው የምትሰጠው?
፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨
እንደ አንድ ጥሩ ሰው፣ እንደ አንድ ብርቱ ለሰው አዛኝ ሰው፣ እንደ አንድ ቅንና የዋህ ሰው ይበልጥ የሚያስጨንቅህ ነገር ምንድነው? የምትሰጠው ወይስ የምትቀበለው? የምታደርገው ወይስ የሚደረግልህ? የምታስገኘው ወይስ የምታገኘው? የምታስጨምረው ወይስ የሚጨመርልህ? ለየትኛው ይበልጥ ትኩረት ትሰጣለህ? ልብህ ለየትኛው ያደላል። መቀበል የለመደ ሰው ደስታው ሁሌም የሚሰጠውን ነገር በማሰብ የሚያገኘው ነው። መስጠትን የለመደ ደግሞ ሲሰጥ ብቻ የሚያገኘውን ደስታ በሚገባ ያውቀዋል። አዲስ ነገር ሲደረግልህ እንደምትደሰተው ሁሉ አዲስ ነገር ለሰዎች ማድረግም ደስታን ሊሰጥህ ይገባል። የጠበከው ነገር ሲከናወንልህ ልብህ ሃሴት ያደርጋል፤ ብዙዎች የሚጠብቁትም ባንተ በኩል ሲደረግላቸው ያንተን ስሜት አዳምጥ።

አዎ! ጀግናዬ..! ምንድነው የምትሰጠው? እንደ ማንኛውም ሰው "ምን አለኝና" አትበል። ምንም ባይኖርህ መስጠት እንደምትችል መለማመድ ይኖርብሃል። ነገር ግን ማንም ምንም ሳይኖረው፣ ምንም ሳይሰጠው፣ ምንም የሚያካፍለው ሳይታደለው የተፈጠረ ሰው የለም። ትኩረታችን ሁሉ ሰዎች ላይ ሆኖ ያለንን ነገር ግን ማስተዋል ያልቻልን ብዙዎች ነን። ባለው ነገር የሚመካ፣ በተሰጠው ነገር ደረቱን የሚነፋ ሰው ቢኖር አለኝ የሚለው ነገር ሲጠፋ ተሽመድምዶ እንደሚቀመጥ ምንም ጥርጥር የለውም። ኩራትህ በተሰጠህ፣ ባገኘሀው ወይም በታደልከው ሳይሆን በምትሰጠው፣ በምታጋራውና በምታካፍለው ይሁን። የሚያኮራህ ነገር አንተ ጋር ያለ ነገር ሳይሆን ካንተ የሚወጣ ነገር ይሁን።

አዎ! ሌላው ባይኖርህ ተስፋ አለህ፣ ብርታት አለህ፣ ቅንነት አለህ፣ ደግነት፣ መልካምነት፣ የዋህነት አለህ። ሰዎችን ከዚህ በላይ ለረጅም ጊዜ የሚጠቅማቸው ነገር የለም። የምትሰጣቸው ገንዘበ ለጊዜው ችግራቸውን ይፈታል፤ የምታጋረቸው ንብረት ለተወሰነ ጊዜ የተሻለ ህይወት ያሳያቸዋል፤ በየጊዜው የምትመግባቸው የተስፋ ቃል፣ እንደ ቀላል ጆሮ ሰተህ የምታዳምጣቸው፣ ሲፈልጉህ አለሁላችሁ የምትላቸው፣ ብርታትን የምታካፍላቸው ነገር ግን ከምታስበው በላይ ዋጋህን ይጨምራል። ሁሌም ቢሆን ከምትቀበለው የምትሰጠውን አስበልጥ፤ ከሚደረግልህ ለሰዎች የምታደርገውና የምታካፍለው ነገር ላይ አተኩር፤ መስጠትን፣ ማጋራትን ልመድ፤ ውስጥህንም በመትረፍረፍ ሙላው።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.3K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 11:51:45
ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦች!
ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት በሳምንታዊ #LIVE_ምክረአዕምሮ_PODCAST እንገናኛለን።

ዘወትር አርብ ምሽት ከ3:00 - 4:00 በዚሁ ቴሌግራም ቻናል ላይ እንዳያመልጣችሁ።
ምክረ-አዕምሮ PODCAST on TELEGRAM
EPISODE 01: Today Night
@MentalCounsel @MentalCounsel @MentalCounsel  @MentalCounsel
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.3K viewsedited  08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 07:34:39 እራስህን ተመልከት!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
የትኛውም ግንኙነት ውስጥ ከመግባትህ በፊት እራስህን ተመልከት፤ ወዴትም በጭፍን ከመጓዝህ አስቀድሞ እራስህን መዝን። እራሱን የማይወድ ሰው ሁሌም ፍቅርን ከሰው እየጠበቀ የሚሰቃይ ሰው እንደሆነ አስታውስ። ግንኙነት ድርሰቶች ላይ እንዳለው ፍፁም እንከን አልባ አይደለም፤ የተለያዩ የፍቅር ፊልም ላይ እንደሚገለፀው ሙሉ ማንነትህን የሚቀማህም አይደለም። ድርሰት ከእውነታው ይልቅ የሰውን ትኩረት ለመሳብ የሚደረግ ነገር ይበዛዋል። ደራሲው በፈለገው መልኩ ሊማርክህ ይችላል፣ ተዋንያኖቹም እንዲሁ ያደርጋሉ። ትክክለኛው ያንተ ህይወት እውነታ ግን ከዚህ የወጣ ነው። እራስህን ሳትመለከት፣ ደረጃህን ሳትረዳ፣ ማንነትህን ሳታውቅ፣ መስጠት የምትችለውን ሳትገነዘብ፣ የምትቀበለውን ብቻ እያሰብክ በጭፍን የምትገባበት የትኛውም ግንኙነት አንደኛው የውድቀትህ ምክንያት ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! እራስህን ተመልከት! እራስህን በጥልቀት ጠይቀው። ሌላ ተጨማሪ ሰው ወደ ህይወትህ ከማስገባትህ በፊት ለእራስህ ያለህን ቦታ ገምግም፤ ከሌላ ሰው ጋር ከመወዳጀትህ በፊት ከእራስህ ጋር ያለህ ወዳጅነት ምን እንደሚመስል እወቅ። ለእራሳችን የማንሰጠውን ክብር፣ ቦታና እንክብካቤ በተወሰነ ጊዜያት ለምናውቀው ሰው እየሰጠን መጨረሻችን ህመምና ስቃይ ሆኖ የሚገኝበት ጊዜ ጥቂት አይደለም። አንተ ጨክነህ እራስህን አሳልፈህ ከሰጠህ ቦሃል ማንም አንተን የማዳን ግዴታ የለበትም። እውነተኛ ግንኙነትና የድርሰቱ አለም በብዙ መልኩ እንደሚለያይ ካልተረዳህ እራስህን ከፉ ወጥመድ ውስጥ እያስገባህ ነው። ከማንም ከምንም በፊት ቀዳሚው ለእራስህ የምትሰጠው ፍቅር፣ ክብርና ቦታ ነው። ሌላው የማጋራት ደረጃው ላይ ብቻ ስትደርስ የምታደርገው ነገር ነው።

አዎ! ጀግኒት..! አንቺ ያልወደድሽውንና ያልተቀበልሽውን ማንነትሽን ሌላው እንዲወደውና እንዲቀበለው አትታገይ። እራስሽን መጠገን፣ ተፈላጊ ሰው መሆንሽን ማስመስከር፣ ለምትፈልጊው ነገር ብቁ እንደሆንሽ ማረጋገጥ የእራስሽ ድርሻ ነው። እራስሽን ደካማ የሚመጣውን ጠንካራ፣ እራስሽን ተረጂ የሚመጣውን ሰው ረጂና ደጋፊ አድርጎ መሳል አቁሚ። እራስሽን ካላጠነከርሽ ማንም ቢመጣ ሊያጠነክርሽ አይችልም፤ እራስሽን ካልረዳሽ ማንም እስከመጨረሻው የሚረዳሽ የለም። ለእራስሽ መወገን ካልቻልሽ ወገን እንደሌለሽ ቁጠሪው፤ ምክንያቱም አንድ ቀን ብቻሽን መቅረትሽ አይቀርምና ነው። ህይወትን ልክ እንደ ድርሰት ሳይሆን እንድ እራሱ እንደ ትክክለኛ ህይወት መኖር ጀምሪ። ያየሽውን ሁሉ ለማድረግ ሳይሆን የሚገባሽንና የሚጠቅምሽን ለማድረግ እራስሽን አዘጋጂ።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.0K views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 07:33:53
2.5K views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 20:52:40 እብድ ተባል!
፨፨፨////፨፨፨
እብድ አትሁን ነገር ግን በሚያዩህ እብድ ተባል፤ የለየለት አለሌ አትሁን ነገር ግን ለሚከታተሉህ አለሌ ሁን፤ ብቸኛ አትሁን ነገር ግን ለሰዎች ብቸኛ ሰው አልባ ሁን። ትክክለኛው ማንነትህ አንተ ለእራስህ የሆነከው እንጂ ለሰዎች ሆነህ የምትታየው አይደለም። የእብደት መለኪያ ብዙ ቢኖርም የተለየ መንገድ ስለመረጥክና እራስህን እንደ ጀግና ስለተመለከትክ እንደ እብድ ብትቆጠር ለእራስህ ትክክለኛው መንገድ ላይ እስከሆንክ ድረስ ግድ አይስጥህ፣ ብዙ አትጨነቅ። በማይመለከትህ ጉዳይ ከሰዎች ባለማውራትህ፣ ወሬያቸውን ባለማዳመቅህ፣ ከማይመጥንህ ስፍራ በመራቅህ፣ የብቻኝነት ደሴትህን በመውደድህ ዝምተኛ፣ ብቸኛና ሰው እንደማትወድ ልትቆጠር ትችላለህ፤ ነገር ግን ከእራስህና ከአምላክህ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እስካለህ ድረስ ብቸኛ ልትሆን አትችልም።

አዎ! ጀግናዬ..! የተባልከውን አይደለህምና እብድ ተባል፤ የሆንከውን ነህና የማይሆን ስም ይውጣልህ፤ እራስህን ታውቃለህና ትቺት ይቅረብብህ፤ በፍፁም አትጨነቅ። ባለን አጭር የመኖር ጊዜ ስለምንባለው፣ ስለሚወራብን ጉዳይ ተጨንቀን ህይወታችንን ይባስ ልናሳጥራት አይገባም። እራስህን ስታውቅ በኩራት መኖር ትጀምራለህ፤ የት መድረስ እንደምትችል፣ ደረጃህ ምን እንደሆነ ስታውቅ የልብህ ሙላት የአሰናካዮችህን አይን ያርቅልሃል። ቀላልም ይሁን ከባድ እራስህን ሆነህ ለእራስህ መታገል የግድ ነው። አሉታዊ ንግግርን መዝራት የለመደች ምላስ ለማንም አትመለስምና አስቀድሞ መንፈስን ማጠንከር፣ እራስህን ማበርታት ያስፈልጋል።

አዎ! ምንም ስታደርግ የማይጥማቸው ሰዎች ካሉ፣ አንድ ነገር በከወንክ ቁጥር ለተቃውሞ የሚንደረደሩ ሰዎች ካጋጠሙህ፣ ቀላሉን "በርታ" ማለት ከብዷቸው ከባዱን "አትችልም ይቅርብህ" ለማለት የሚሯሯጡ ሰዎች ወደ ህይወትህ ቢመጡ ማዳመጥ ሳይሆን ለአፍታም ጊዜ መስጠት አያስፈልግህም። የሚለጠፍብህ ስም፣ የሚወራብህ ወሬ፣ የሚነገርብህ ጉዳይ አንተን እንደማይገልፅህ በተግባር አሳይ። "እሱ እብድ ነው፤ የሚያደርገውን አያውቅም፤ የሚመክረው ሰው የለውም፤ ዝም ብሎ ይለፋል።" መባል የእንቅስቃሴህ ማሳያ ነው። ምክንያቱም የተለየ ተግባር ላይ ያልተሰማራ፣ ባልተለመደ አቅጣጫ የማይጓዝ፣ በመደበኛው መንገድ የሚመላለስ ሰው እንዴትም እብድ ሊባል አይችልምና ነው። የምትባለውን ተወት አድርገህ ፈልገህ የሆንከው ላይ አተኩር፤ ከተሰጠህ ስም በላይ ያለህበት ስፍራ ያሳስብህ፤ በእራስህ መንገድ መዳረሻህን እራስህ ወስን።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.3K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 07:08:22 መነቃቃትህን እርሳው!
፨፨፨፨///////////፨፨፨፨
አዎ! መነቃቃትህን እርሳው ለእራስህ የገባሀው ቃል ላይ አተኩር፤ ለስሜትህ መገዛት አቁም ማድረግ የሚገባህን በጊዜው አድርግ፤ በምታየው፣ በምትሰማው መማረክህን አቁም፣ አይንና ጆሮህ ግብህ ላይ ይሁን። መነቃቃት ጊዜያዊ ነውና እርሱን መጠበቅ ከጀመርክ ተግባርህም ጊዜያዊ እንደሚሆን አትጠራጠር፤ እንድ ዲም ላይት (dem light) ስትነቃቃ የምታደርገው ሲደብርህ የምታቆመው ተግባር የት ሊያደርስህ ይችላል? ወዴትስ ይወስድሃል? ወዴትም። በድግግሞሽ ስሜት፣ በተደጋገመ ውጤት ያደክምሃል፤ የጠበከውን ሳይሆን የሆንከውን ያሳይሃል፤ የምትፈልገውን ሳይሆን ያደረከውን ፍሬ ያመላክትሃል። ከሁሉም በላይ ዲሲፕሊን (discipline)፣ እራስን መግዛት፣ እራስን መገሰፅ፣ ላወጣሃቸው የእራስ ደረጃዎች መታምን፣ ማንም ባያየንም፣ ማንም ቃላችንን ባይሰማም ለእራሳችን ለገባነው ቃል መታመን ይኖርብናል።

አዎ! ጀግናዬ...! መነቃቃትህን እርሳው! ዲሲፕሊንን አስቀድም፤ ከስሜት በላይ መሆንን ተላመድ፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ውስጥ ትርጉም ማግኘትን አዳብር። ሲመችህ ብቻ በምትሰራው እንቅስቃሴ የሰውነት አቋምህ አይቀየርም፤ ሲደላህ ብቻ በምታስበው ሃሳብ እራስህን አታሻሽልም፤ የፈለከው ሁሉ ተሟልቶ በምታደርገው ተግባር ብቻ ወደፊት መጓዝ አትችልም። አንዳንድ ሁኔታዎች ልፋት እንጂ ቶሎ ውጤት አይኖራቸውም፤ ያደክሙሃል እንጂ የሚታይ ነገር አትመለከትባቸውም፤ እለት እለት ስትደክም ትመለከታለህ እንጂ በፍፁም ጠብ የሚል ነገር አታገኝባቸውም። የአሁን ድካምህን ሳይሆን የወደፊት ውጤትህን አስበህ ትታገላለህ፤ የአሁን መረበሽህን ረስተህ የመጪው መረጋጋትህ ላይ ታተኩራለህ። ቢዘገይም የምትናፍቃትን ብረሃን ትመለከታለህ፤ ቢቆይም ተስፋ ያደረከው ደረጃ ላይ እራስህን ታገኘዋለህ፤ ቢያደክምህም የለፋህበት ዋጋ ይገፈልሃል።

አዎ! ዲሲፕሊን ቀላል አይደለም፤ ዋጋ መክፈል፣ ወዶ መሰቃየት፣ ውጤት ሳይኖር መድከም፣ በማይታይ ትግል መጠመድ፣ እለት እለት ከእራስ ጋር መሟገት፣ ውጪ የምታየው ሌላ ውስጥህ የምታየው ሌላ ሲሆን የስሜትህን መቀያየር መቆጣጠር ከባድ ነው። በዚህ ሁሉ ውጣውረድ ውስጥ ለእራስህ መታመን ካልቻልክ ይባስ ነገሮችን ታከብዳቸዋለህ። የሚሰራ ሰው፣ ለምን የሚሰራውን ስራ ከብዙዎች መርጦ እንደሚሰራው ካላወቀ በስሜቱና በጉልበቱ እየተጫወተ ነው። ገንዘብ ለማግኘት፣ ህይወትን ለማሸነፍ፣ ሌሎችን ለመርዳት፣ ህልሙን ለመኖር ሊሆን ይችላል። ምክንያቱን በማነቃቂያው ቦታ የሚያስቀምጥ ከሆነ ዲሲፕሊንን የማያዳብርበት፣ እራሱ ላይ የማያተኩርበት፣ በምክንያቱ የማይገዛበትን አጋጣሚ አይኖረውም። ለተግባርህ ጠንካራ ምክንያት ይኑርህ፣ ለምታደርገው ነገር ዋጋ የሚያስከፍል ፅኑ ፍላጎት ይኑርህ፤ በመነቃቃት ሳይሆን በምክንያትህ ተመራ፤ ለምክንያትህ ብለህ እራስህን ግዛ።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.7K views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ