Get Mystery Box with random crypto!

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™
የሰርጥ አድራሻ: @mentalcounsel
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.06K
የሰርጥ መግለጫ

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-02 20:53:48 የማይቻለውን አትችልም!
፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨
አንዳንዴ አንዳንድ እውነታዎችን ለህሊና ሰላምና ለውስጣዊ መረጋጋት በጥንቃቄ መቀበል እጅግ አስፈላጊ ነው። የማይቻውን ነገር እድሜ ልክ እየታገሉ ለመቻል መውተርተር አስፈላጊ አይደለም። ጠቢብ የሚያዋጣውን ያውቃል፤ አስተዋይም የሚችለውን ልቡ ይነግረዋል። ሁሉንም ሰው ማስደሰት አይቻልምና ሙከራችሁን አቁሙ፤ ዘወትር በአስመሳይ ማንነት መቀጠል አይቻልምና ከድካማችሁ ተመለሱ፤ ሁሌም ችግርን መተንተን አያዋጣምና ተውት። ሁሉም ይቻላል ማለት የማይቻል አንዳች ነገር የለም ማለት አይደለም። ሁሉም ሰው በማንነቱ ልክ የሚችለው አለ፤ የማይችለውም እንዲሁ ይኖራል። የሰው ልጅ በጠቅላላ የማይችለውና ከአቅሙ በላይ የሆነ ነገርም አለ። ደስታን ፍለጋ ደጋግሞ የሚዋሽ ሰው ደስታውን ማግኘት አይችልም፤ አዎንታዊነት የሌለው ሰው ለውስጣዊ ሰላሙ ዋስትና የለውም፤ በጭፍን ጥላቻ የታወረ ሰው ርህራሔን አያውቀውም።

አዎ! ጀግናዬ..! የማትችለውን አትችልም፤ የማታውቀውን አታውቅም፤ የማይመለከትህ አይመለከትህም። እውነታውን ማመን ቢያጠነክርህ እንጂ ደካማና ዋጋ ቢስ አያደርግህም። የማይሆን ነገር እንደማይሆን ካወክ ከእርሱ ጋር ጊዜህን የምታጠፋበት ምክንያት አይኖርም። አንተ የሁሉም ሰው መሆን አትችልምና ሁሉም ሰውም ያንተ ሊሆን አይችልም። አንተ በሁሉም ሰው ሃሳብ ልትስማማ አትችልምና እንዲሁ ሁሉም ሰው ባንተ ሃሳብ ሊስማማና አስተምሮህን ሊቀበል አይችልም። መሆን የምትችለው እራስህንና እራስህን ብቻ ነው። እዚም እዛም እየተገኘህ መሃላ ሰፋሪነትህ የትም አያደርስህም። ተቃውሞን ማብዛት በእራስ መጨከን ነው፤ ችሎታን መግደል አቅምን ማኮሰሰ ነው። የአዕምሮህ ንቃት ቀጥተኛውን መንገድ ይጠቁምሃል፤ አስተውሎትህ የትኩረትህ ዋንኛ ግበዓት ነው።

አዎ! እንደምትችለው ከሚነገርህ በላይ ልብህ እንደምትችለው የሚያውቀውና ውስጥህ በፅኑ የሚያምንበት ነገር እጅጉን የተሻለና አመርቂ ውጤት ሊያመጣ ይችላል። ልብህን መቃወም አትችልም፤ ውስጣዊ መሻትህን እስከ ወዲያኛው አፍነህ ማስቀረት አትችልም። ለዚህም ነው መሆን ያለብህን ትሆን ዘንድ እራስህን መልቀቅና ለፍላጎትህ እድል መስጠት ያለብህ። በተመሳሳይ እውቀት፣ በቋሚ አመለካከት፣ በታጠረና ነገሮችን በየአቅጣጫው በማይመለከት፣ ለፍረጃ በሚጣደፍ ማንነት ከፍ ማለትም ሆነ፣ እራስን ማብቃት አይቻልም። ህይወትን ለማቅለል የሚመርጥ ሰው ከእራሱ ፍላጎትና አመለካከት ጋር በማይገናኝ ትግል ውስጥ ዘው ብሎ አይገባም። ያንተ የሆነውን እንደምትችል እወቅ፤ ያንተ ያልሆነውን ግን ለባለቤቱ ስጥ። በአላስፈላጊ ብክነት የምታጠፋው ጊዜ እንደሌለህ አስታውስ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.9K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 19:48:35
ሰላም ውድ ቤተሰቦች እንዴት አመሻችሁ?

እራስህን ሁን! በእራስህ አትፈር። በማንነትህ ኩራ፤ ሌሎች የሚመለከቱህ መንገድ አያስጨንቅህ።
Be Yourself. Never be ashamed of yourself. Be proud of who you are and don't worry about how others see you.
- Unknown

ነገ (ሰኞ) ጠዋት በተለመደው 2:00 ሰዓት ሃፍረታችሁን ለመግፈፍ በሚጠቅማችሁ አዲስ ቪድዮ እንገናኝ።

"አትሸማቀቅ!"
"DON'T BE SHY !"

እንደምታተርፉበት ተስፋ እናደርጋለን።
የነገ ሰው ይበለን!

ከወዲሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ቻናላችንን
SUBSCRIBE በማድረግና
የደውል ምልክቱን በማብራት ይጠብቁን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube LINK!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.7K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 13:54:21 #ሁሉንም ጠይቅ - ሶቅራጠስ

ለሶቅራጥስ “አለማወቅን ማወቅ” የፍልስፍና መጀመሪያ ነው፡፡ አለማወቃችንን ሳናውቅ የእውቀትን መንገድ መጀመር አንችልም፡፡

በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ “አላውቅም” ማለት የመሃይም ምልክት ሆኖ ቆይቷል። ልክ ኃጢአትን እንደሰራ ሰውም ትቆጠራለህ፤ ችግር እንዳለብህም ይታሰባል። መድኃኒትን ፍለጋም ወደ መምህራን ወይም አዋቂ ወደተባሉ ሰዎች እንድትሄድ ይነገርሃል።

ለሶቅራጥስ ሁለት አይነት አላዋቂነቶች አሉ።

1.አለማወቅን_አለማወቅ።
ይህ በሕይወትህ ላይ ምን እንደማታውቅ ሳታውቅ መኖር ማለት ነው። እነዚህ ራሳቸውን አይጠይቁም አውቃለሁ አላውቅም ብለውም አይመረምሩም፡፡ ሕይወታቸውንም በእንቅልፍ ውስጥ እንዳለ ሰው፣ ሁሉንም አውቃለሁ እያሉ ይኖራሉ፡፡ ሃሳባቸውን ለመመርመር ቆም ብለው አያስቡም፡፡

2.ሶቅራጥሳዊ አለማወቅ ።
ይህ ከእንቅልፋችን ነቅተን እና አይናችንን ገልጠን መጠየቅ ስንጀምር ያለውን ጊዜ ያመለክታል። የምናውቀውን ሁሉ እንጠረጥራለን::

ሁለተኛውን አለማወቅ ሶቅራጥስ የተቀደሰ አለማወቅ ይለዋል፡፡ የምናውቃት ጥቂት ናት፤ ከምናውቀውም የሆነ ጊዜ፣ የሆነ ቦታ ላይ ስህተት መኖሩን እንረዳለን፡፡
ሶቅራጥስ በዚህ አባባሉ ይታወቃል፤ “Unexamined life is not worth living' (ያልተመረመር ሕይወት ሊኖሩት ያልተገባ ነው።)

ምንጭ :- ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ

THANK YOU FOR READING.
ELODIA READING
ኤሎድያ ንባብ

   #share and join for more

@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
2.9K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 07:40:48 ነፍሴን ቀድሳት!
፨፨፨///////፨፨፨
ደጉ አባት ቅዱስ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይናገረናል። ንግግሩም ከባህሪው ሲቀዳ "በፍቅር ትመላለሱ ዘንድ፣ እኔንም ታስደስቱ ዘንድ የፍቅር ልብ ይኑራችሁ፤ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ፤ ድጋፍን ፈልጉ፣ ለወገናችሁም ድጋፍ ሁኑ።" የዘወትር አሸናፊዎች በነፍሳቸው ላይ የሰለጠኑ፣ እራሳቸውን የገዙ፣ ማንነታቸውን የዋጁ፣ እግዚአብሔር አምላካቸውን የወደዱና ከልባቸው የተቀበሉ ናቸው። ፍቅርን ከኢየሱስ ክርስቶስ በበለጠ ያስተማረ የለም። አምላክ ሆኖ በፍቅሩ ብዛት የሞተው ለእኛ ለልጆቹ ነው። የእኛ በፍቅር መመላለስ ግን የሚፈልገው ሞት ሳይሆን ንፁ ልብ፣ አዎንታዊ አስተሳሰብና ቅንነት ነው። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ የፍቅሩ መገለጫም እኛው ድንቅ ልጆቹ፣ የእጆቹ ስራ፣ ግሩም ትሩፋቶቹ ነን። ወዶ፣ ፈቅዶ፣ መርጦ እኛን ፈጠረ፣ ወደዚህ ምድርም አመጣን። ከፈጣሪያችን እግዚአብሔር በቀር ማን ስለእኛ ያውቃል፤ ማንስ እርሱ እያወቀን ዝም ብሎ ፃድቅ ነኝ በይ ሊከሰን ይነሳል።

አዎ! ጀግናዬ..! እግዚአብሔር መንገድህ ነው፤ አምላክህ መዳረሻህ ነው፤ ህይወትህ የእርሱ መንግስት ነው፤ ፅድቅህ ፍቃዱ ነው፤ ምርጫው ነው፤ ትዕዛዙ ነው። የምታውቀውን ለመኖር ጥበብ ያሻሃል፤ ትልቁ ጥበብ ደግሞ እግዚአብሔርን መፍራት ነው። ከጠቢቡ ሰለሞን በላይ ጥበብን የሚያውቅ፣ ምንነቱን የተረዳ፣ ምንጩንም የተገነዘበ ሌላ ማን ይኖራል? ማንም። ጥበብን የሚሻ የአምላክ ባለሟል ነው፤ የአምላኩ የእግዚአብሔር ተገዢም፣ ታዛዥም ነው። ልፋ ያለው ይለፋል፤ ድከም ያለው ይደክማል፤ አምላክህን እወቅ ያለው ግን በእውቀቱ ያርፋል፤ በጥበቡ ህይወቱን ይመላል። መርጋት በእግዚአብሔር እጆች ላይ ነው፤ ሰላም ማግኘት በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነው፤ መባረክ በቃሉ መውዛት ነው፤ መመረጥ መንገዱን መከተል ነው።

አዎ! ካንተ በለይ የምታመልከው አምላክ፣ የታመንክበት ጌታ፣ የምትማፀነው ፈጣሪ መመኪያህ ነው፤ ዙፋንህ ነው፤ ዘወድህ፣ ክብርህ፣ ጌጥህ ነው። ብቻህን አለምን ብታካልል ነፍስህ እረፍት አይኖራትም፤ ምድራዊውን እውቀት ጨርሰህ ብትይዘው ውስጥህ ሃሴት አያደርግም፤ የአለም ጭብጨባና ዝና ቢጎርፍልህ መንፈስህን አያድስም፤ ውስጥህን አያክምም። እረፍትህ፣ ሰላምህ፣ ሃሴትህና እድሳትህ ሁሉ ምንጫቸው እግዚአብሔር አምላክህ ነው፤ መገኛቸው ጌታህ፣ ገዢህና አባትህ ነው። ቅዱሳት ነፍሳት የሚመኩት፣ የሚኮሩት የሚታመኑት በአምላካቸው በእግዚአብሔር ነው ነውና ከዘወትር ፀሎትህ መጀመሪያ፣ ከዘወትር ፀሎትህ መደምደሚያ ይህችን የልባዊ ተማፅኖ ቃል እንዳትረሳ "ነፍሴን ቀድሳት!" ።
ብሩክ ቅዱስ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.3K views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 07:40:08
2.7K views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 20:22:36 እንዳይረፍድብህ!
፨፨፨//////////፨፨፨
እንዳይረፍድብህ ዛሬ አሁን ወደ እርምጃ ግባ። ሃሳቦችህን ሰብስብ፣ እቅድ አውጣ፣ ግብህን ቅረፅ፣ ወደፊት ተመልከት። ጊዜው ለለቅሶ፣ ለዋይታና ለወቀሳ ቦታ የለውም። ነገሮች ቢወደዱብህ አንተ ከእነርሱ በላይ ውድ እንደሆንክ ማሰብ ጀምር። የሚገዛህ ወርቅ፣ እምነበረድ ወይም ገንዘብ የለም። ዋጋህ ሰማያዊ ፀጋ ነው፤ ዋጋህ የአምላክህ ሰጦታ ነው፤ መገለጫህ ሰውነትህ ነው። አዳዲስ ነገሮችን ለመከወን እራስህን ማዘጋጀት ያንተ ድርሻ ነው። ሲያልፍ የሚያልፍን ጊዜ በሚያስወቅስህ ተግባር አታሳልፈው። አርፋጅ ከሚቀር፣ ከማይሞክር፣ ከማይጀምር ይሻላል፤ ነገር ግን ውድድርህ ካልጀመሩ፣ ቁጭ ብለው ከሚያማርሩና ምክንያት ከሚደረድሩት ጋር አይደለም። ውደድርህ ከፈሪው አንተ ጋር ነው፤ ውድድርህ ይሉኝታ ካለበት ማንነትህ ጋር ነው፤ ውድድርህ ፍፁም ነገርን ከሚጠብቀው አንተነትህ ጋር ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! እንዳይረፍድብህ! ህፃን እስካልሆንክ እንደ ህፃን መጫወት፣ መቦረቅ አትችልም። አስተዋይ ካልሆንክ እንደ አስተዋይ መኖር አትችልም። የትኛውንም ማንነት ለመገንባት ግን ጊዜ አለው። በወጣትነህ እንደ ህፃን መኖር አትችልም፤ ፈሪ ሆነህ የደፋርን ስብዕና መላበስ አትችልም። መሆን ያለብህን በጊዜው ስትሆን የሚገለፅብህ ማንነትና ስብዕና ይኖርሃል። እየቻልክ እንደማትችል፣ እያወክ እንዳላወቂ፣ ጥበብ እያለህ ጥበብና ማስተዋል እንደጎደለው መኖር አልሰለቸህም? ዘወትር ከእራስህ የምትጠብቀውን ነገር አንዴም ሳታገኘው መቅረት አያሳስብህም? ድርሻህ መጀመር ሆኖ ስትጠብቅ ልትገኝ ትችላለህ፤ ሃላፊነትህ መወሰን ሆኖ ስታወላውል ልትገኝ ትችላለህ፤ በጊዜው መገኘት ኖሮብህ አርፋጅም ልትሆን ትችላለህ። ነገር ግን ዋናው ጉዳይ ሁሌም አርፋጅ፣ ሁሌም እራስን ወቃሽ ሆኖ አለመገኘት ነው።

አዎ! ተመልሶ የማይገኝ እድሜ ይዘህ ማርፈድ እራስን ለቁጪት መዳረግ ነው፤ የምትፈልገውን ነገር ለመጀመር ዛሬ ነገ ማለት በጊዜህ መፍረድ ነው። አንዳንዶቹ የምታጣቸው ነገሮች ሃላፊነትህን በሚገባው ልክ ሳትወጣ ስትቀር የሚፈጠሩ ናቸው። በሚያልፍ ጊዜ ውስጥ ሁሌም አንድ አይነት ምክንያት እየደረደሩ ወደኋላ መቅረት፣ እራስ ላይ ሸክም ማብዛትና ዘወትር እራስን እየወቀሱ መኖር እጅግ አድካሚና የህይወትን ለዛ የሚያበላሽ ነው። እስከመቼ ዛሬን እየሸሸህ በነገ እየታመንክ ትኖራለህ? እስከመቼ እውነታውን እየገፋህ በምኞት ለመኖር ትዘጋጃለህ? እስከመቼስ የተገብር ሳይሆን የቀጠሮ ሰው ብቻ ትሆናለህ? ዛሬ የሚጠበቅብህ ሃላፊነት ጊዜው በጨመረ ቁጥር ያንተም ድክመትና ስንፍና እየጨመረ ይመጣል። የነገውን ቀላል ህይወት ከፈለክ ዛሬ ከባድ ሁኔታ ውስጥ እራስህን አስገባ፤ በማርፈድህ ከምትቆጭ ዛሬውኑ ቀድመህ ተገኝ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.5K views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 07:46:30 ትረዱ ዘንድ ፍቀዱ!
፨፨፨፨///////፨፨፨፨
ሊረዳቹ ለሚፈልግ ሰው ቀላል ሁኑ፤ ግልፅ ሁኑ። በሩ እስካልተከፈተ ድረስ በተዘጋ ቤት መግባት አይቻልም። የሰዎችን እርዳታ የሚፈልግ ሰውም እራሱን ግልፅ ካላደረገ፣ ችግሮቹን በሚገባ ካላስረዳ፣ እንዲረዱት በሩን ካልከፈተ ማንም ሊያግዘው አይችልም። በማንኛውም ጊዜ የሰው እርዳታ የሚያስፈልጋችሁ አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል። ነገር ግን እራሳችሁን ግልፅ ካላደረጋችሁና ችግራችሁን በቅርበት ማስረዳት ካልቻላችሁ ማንም ሊረዳችሁ እንደማይችል እወቁ። እግዚአብሔርም ቢሆን ስትፈቅዱለት፣ ስትፈልጉት፣ ስትቀርቡት በእናንተ ላይ ይሰራል እንጂ በፍፁም እናንተን ብቻ መርጦ አይሰራላችሁም፤ ቁጭ ብላቹም ያሻችሁን እንድታገኙ አያደርግም። ለምንም ነገር የእናንተ ፍቃደኝነት እጅግ ወሳኝ ነው። እግዚአብሔር ፍቃደችሁን የሚሻ ከሆነ የሰው ልጅ እንዴት ፍቃዳችሁን ላይፈልግ እንደሚችል ተረዱ።

አዎ! ጀግናዬ..! የተሾመብህ ሌላ ሰው ሳይሆን እራስህ ነህ፤ ለእርዳታም እራስህን የምታዘጋጀው አንተው እራስህ ነህ። ከባለቤቱ በላይ ለባለቤቱ የሚያውቅ የለም። ለእራስህ አንተ ታውቃለህ፤ ስለእራስህ መረዳቱ ያለህ አንተ ነህ። ከሁሉ የሚልቅ ማንነትን የምትገነባው እራስህን ባወክና በተረዳህ መጠን ነው። የሚያግዙህ፣ የሚያበረታቱህና የሚደግፉህ ሰዎች ወደ ህይወትህ ይመጡ ዘንድ ምርጫውም ውሳኔውም የእራስህ ነው። ባንተ ህይወት ማንም አይወስንም፤ አንተም በሌላው ላይ መወሰን አትችልም። የአንድ ሰው ነፃ ፍቃድ የሚሰራው እራሱ ላይ ብቻ ነው። በምንም መንገድ ነፃ ፍቃዱን ተጠቅሞ የሌሎችን መብት መንካት፣ ነፃነታቸውን መግፈፍና በህይወታቸው ገብቶ መወሰን አይችልም። የሚያግዝህ ሰው የሚያስፈልግህ ከሆነ ወደ ቤትህ ገብቶ ያግዝህ ዘንድ በርህን ክፈትለት።

አዎ! ችግር ስላጋጠማችሁ ብቻ ችግራችሁን ላገኛችሁት ሰው በሙሉ አታስረዱም፤ መፍትሔ ማምጣት ስላልቻላችሁ ብቻ ካገኛችሁት ሰው ሁሉ መፍትሔ አትፈልጉም። ትረዱ ዘንድ ፍቀዱ፤ ፍቃዳችሁን ግን ሊረዳችሁ ፍቃደኛ ለሆነ፣ አቅሙና እውቀቱ ላለው ሰው ስጡ። አብዛኛው በእናንተ ላይ የሚሆን ነገር የእናንተን ፍቃድ ይፈልጋል። ለእርሱም ሃላፊነትን መውሰድ ስትጀምሩ ጠንቃቃና የመፍትሔ ሰው መሆን ትጀምራላችሁ። ለብቻችሁ የምትታገሉት ትግል ካደከማችሁ አጋዥ፣ አበርታች፣ አይዞህ ባይ ለማግኘት ፍቃደኛ ሁኑ፤ ድፍረቱም ይኑራችሁ። እራችሁን ብቻ የእራሳችሁ ሚስጥረኛ አድርጋችሁ ሸክማችሁ ካልቀለለ በትንሹም ቢሆን ሚስጥራቹን የምታካፍሉት፣ ሸክማችሁንም የሚያቀልላችሁ ሰው ፈልጉ።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.8K views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 07:45:44
3.3K views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 21:42:09 በ "EXCUSE / ሰበብ ዙሪያ የነበረን #LIVE_PODCAST እንዴት ነበር?
ሃሳብ አስተያየት ፃፉልን።
3.5K views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 20:46:04 የአምላክህ ልጅ ነህ!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
በእራስህ እንደምታፍር ይሰማሃል? ቀና ማለት ትልቅ ሸክም ሆኖብሃል? ውስጥህ ተረብሿል? ብርታት አጥተሃል? ዋጋህን ለመጨመር ተቸግረሃል? እራስህ ላይ ለመሰልጠን፣ እራስህን ለመግዛት አቅም አንሶሃል? እንግዲያውስ ይህን ንግግር ከልብህ አንስተህ በቃልህ ደጋግመህ ለእራስህ ንገረው፦ "ልበ ብርቱ መንፈሰ ጠንካራ፣ ለአለም ፈተና የማልበገር በእግዚአብሔር የምታመን፣ በአምላኬ መፅናትን የተማርኩኝ፣ በሙላት መፈጠሬ የማያጠራጥረኝ፣ በአሁን ስቃዬ እራሴን የማልለካ፣ አቅሜን የማልገድብ፣ መማር፣ ማወቅን፣ መንቃትን የማላቆም፣ ከእራሴ የሚልቅ፣ ከከባቢዬ የገዘፈ ለሀገር፣ ለአህጉርና ለአለም የሚበቃ ብሩህ ተስፋ ያለኝ፣ እምነቴን ዋና ስንቄ፣ የአምላኬን መንፈስ ጋሻዬ አድርጌ የምጓዝ፣ ስብራቴን ለማከም ማንንም የማልጠብቅ፣ በአምላካዊ ፍቅር በታደለኝ ጥበብ እራሴን የማድን እኔ ብርቱ የአምላኬ ልጅ ነኝ።" ብለህ ለእራስህ ደጋግመህ ተናገር።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ የአምላክህ ልጅ ነህ! የደጉ አባትህ፣ ፍቅር የሆነው፣ በፍቅር የሚያኖርህ፣ ፍቅሩን በየቀኑ የሚገልፅልህ፣ ውሎህን የሚያሳምርልህ፣ መንገድህን የሚጠርግልህ፣ መዓትህን የሚያርቅልህ አዎ! የእርሱ የህያው አምላክህ ልጅ ነህ። አለምን አትፍራ፣ ህይወትህን ከልክ በላይ አታግዝፋት፤ በምድራዊ ዱብዳ፣ በጊዜያዊ ችግር፣ በጊዜያዊ እጦት አትሸማቀቅ። በተለዋዋጭ አለም ፍፁም የማይለዋወጥ በፊትም፣ ዛሬም፣ ነገም ያው ፍቅር የሆነ አምላክ እንዳለህ አስታውስ። በእርግጥ አለም ውስጥ ብዙ አይንን የሚስቡ፣ ለጆሮ የሚጥሙ፣ ስሜትን የሚገዙ፣ ለማድረግ፣ ለመስራት ብሎም የእራስ ለማድረግ የሚያስጎመዡ አያሌ ነገሮች ይኖራሉ። ነገር ግን እንደሚጠበቁት ጥምን አይቆርጡም፤ አምሮትን አያወጡም፤ ስሜትን አያረኩም፤ ውስጣዊ ሰላምን አይሰጡም።

አዎ! ከድካምህ ለማረፍ መንፈስህን ጠግን፣ ከሩጫህ ፋታ ለመውሰድ በእግዚአብሔር መንገድ ተመላለስ፤ ህይወትህን እንደ አዲስ ለማነፅ የአምላክህን ድንቅ ስራ፣ የፈጣሪህን የስነ-ፍጥረት ጥበብ አስተውል። ጨለማን እንዲሁ በዝምታ በአርምሞ ፈጠረ ጨለማም ሆነ፤ ብረሃንንም በቃሉ በነቢበ ብረሃን ይሁን አለ ብረሃንም ሆነ። በዝምታ ረቂቁን ጨለማ የፈጠረ፣ በቃሉ ብቻ አስደናቂውን ብረሃን ወደ ምድር ያመጣ አምላክ ላንተ ህይወት ብረሃን መስጠት፣ ጨለማህን መግፈፍ ምንያክል ቀለሉ እንደሆነ አስብ። ነገር ግን በእርሱ ላይ ያለህን እምነት ይፈልጋል፤ ፅናትህን፣ ፍፁም እርሱን ማስቀደምህን፣ ከውስኗ ሰውኛ አቅምህ በተሻለ ስልጣኑን ለእርሱ እንድትሰጥ ይፈልጋል። አምላክህን አስቀድም ህይወትህንም አንተ ቅደም፣ አንተ አሸንፋት።
የሰላም ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
1.5K views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ