Get Mystery Box with random crypto!

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™
የሰርጥ አድራሻ: @mentalcounsel
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.06K
የሰርጥ መግለጫ

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-08 07:07:45
3.0K views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 20:55:31 ዋጋህን ጨምር!
፨፨፨///////፨፨፨
ያመለጡህን እድሎች እርሳቸው፤ የሳትከውን ታርጌት እርሳው፤ ያመለጠህን አጋጣሚ ደጋግመህ ማሰብ አቁም። አንድ የገባህ ነገር ካለ እርሱን ይዘህ እስከመጨረሻ መጓዝ ተለማመድ። በየመሃሉ የሚያጋጥሙህን እንቅፋቶች ብዙ ትኩረት አትስጣቸው፤ ውስጥህ ከተሳለው ትልቅ ነገር የአንድ ቀን አሉታዊ ንግግር ወይም ያልተገባ ተቃውሞ አንዲረብሽህ አትፍቀድ። ማናችንም ስለ ውሎአችን ማሰብ ካልቻልን፣ ለአካባቢያችን ካልተጠነቀቅን፣ የምንሰማውን ካልመረጥን፣ ለምናየው ካልተጠነቀቅን ስብራታችን ማብቂያ አይኖረውም፤ ዘወትር ጀምሮ ማቆማችን ይቀጥላል፤ በየመሃሉ በሚመጣው ድካም ዋጋ መክፈላችን አይቀርም። አቅደህ በምትኖረው ህይወት፣ ግብህን ባስቀመጥክለት፣ እራስህን በሰጠህለት፣ በጥንቃቄ ለምትመራው ህይወት አጋጣሚ የተባለ ነገር እቅድህን እንዲያበላሽና መንገድህን እንዲያስትህ መፍቀድ አይኖርብህም።

አዎ! ጀግናዬ..! በአስተሳሰብህ፣ በእይታህ፣ በተግባርህና በዉሎህ ዋጋህን ጨምር፤ እሴት ያለው ህይወት መኖር ጀምር። ሰዎችን መጥቀም ስትፈልግ በልበሙሉነት አድርገው፤ ውስጥህ ለመልካም ነገር ሲጓጓ ሄደህ ከውነው፤ ሰላም እንደሚሰጥህ የተሰማህ ነገር ካለ አጥብቀህ ግፋበት። ንቃትህ ለጊዜው ቢሆንምከ ፍላጎትህ ግን ሁሌም እንዲገፋህና እንዲያበረታህ አድርግ። በቅድሚያ ያንተን ምርጫ ምታከብረው አንተ እንጂ ሌላው አይደለም፤ ማንም የሚበጅህን የሚያውቅልህ አካል የለም። ለእራስህ እራስህ እንደምታውቅ፣ ለእራስህም ብቁ እንደሆንክ ማሳየቱ ያንተ ድርሻ ነው። በተወሳሰበ ስብዕና፣ ባልተገለጠ ማንነት፣ በተሸፈነ አስተሳሰብ ሳይሆን ቀላል፣ ግልፅና ብርቱ በሆነ ማንነት እራስህን አሳይ።

አዎ! እራሱን ያወቀ ዋጋውን ያውቃል፤ የሚገባው ስፍራ የት እንደሆነ በሚገባ ይረዳል። ዋጋህን ስትጨምር ውሎህ ይቀየራል፤ እሳቤህ፣ እርምጃዎችህና ንግግርህ ሁሉ የተለየ ይሆናል። ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አላስፈላጊ ጊዜህን አታባክን፤ በሚወረወሩብህ ጥቃቅን ጠጠሮች ማንነትህን አትገምት፤ በሚሰጡህ አሉታዊ ስያሜዎች ስሜትህን አትረብሽ። ማንም ያንተን መንገድ መሔድ እንደማይችል አስታውስ። ይብዛም ይነስም በልክህ ብዙ ውጣውረድ አልፈሃል፤ ተፈትነሃል፤ ዋጋም ከፍለሃል። ይህን በማድረግህም በየጊዜው ዋጋህን እየጨመርክ ትመጣለህና በእራስህ ለመኩራት ምንም አይነት ውጫዊ ማረጋገጫ አትፈልግም። በእራስህ ምርጫ ማደግህን ቀጥል፤ ዋጋህንም በየእለቱ ጨምር።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.6K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 11:03:44 እራሳችሁን ይቅር በማለት ወደፊት ለመጓዝ የተቸገራችሁ ይህን ቪድዮ ተመልከቱ! ሃሳብም ስጡበት! 

ለእራሳችሁ ማዘን ጀምሩ
እራሳችሁን ከልብ ይቅር በሉ
የሚጠብቃችሁን ወደፊት ብሩህና አስደሳች ለማድረግ ተዘጋጁ

የእናንተ LIKE COMMENT SUBSCRIBE SHARE ለቪድዮ እይታ ትልቅ ቦታ አለውና ማድረጋችሁን እንዳትረሱ።




3.6K viewsedited  08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 07:22:09 ፍቃድ አትጠብቅ!
፨፨፨/////////፨፨፨
ምርጡ፣ ወሳኚ፣ ምቹውና ትክክለኛው ጊዜ መቼ ነው? ህይወት ቀያሪው፣ ከፍታን ፈጣሪው፣ ስኬትን አቅራቢው፣ ልዕልናውን የሚያፈጥነው ትክክለኛ ጊዜ መቼ ነው? ትናንት? ዛሬ? ነገ ወይስ አሁን? ትክክለኛው ጊዜ ነገም፣ ዛሬም፣ ትናንትም አይደለም። እናም አሁንና አሁን ብቻ ነው። ትክክለኛና እንከን አልባ ነገር ለመስራት ለአመታት ልትጠብቅ ትችላለህ፣ እስክትማር፣ እስክትአውቅ፣ ብቁ ነኝ ብለህ እስክታስብ፣ ሰዎች ትችላለህ ጀምር እስኪሉህ ልትጠብቅ ትችላለህ። በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ከዚህ ሁሉ ጥበቃ ቦሃላ እንኳን ስህተት መስራትህ አይቀርም፤ ማጥፋትህ አይቀርም፤ ውድቀትህም እንደዛው። ቦሃላም መለስ ብለህ እራስህን ትጠይቃለህ "ይህን ሁሉ ጊዜ የጠበኩት ለመሳሳት ነውን? ይህን ሁሉ ጊዜ እራሴን የገደብኩት፣ በፍረሃቴ የተሸነፍኩት፣ ፍላጎቴን ያዳፈንኩት ውድቀቴ ለማይቀር ነገር ነውን?" ትላለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ፍቃድ አትጠብቅ! የሆነ ሰው ወደ ህይወትህ መጥቶ መሆን የምትፈልገውን ሰው እንድትሆን እንዲፈቅድልህ አትጠብቅ፤ መንግስት "ላንተ የሚመችህ ይህ ነው፤ ይህን አድርግ፣ እንደዚህ ስራ" እስኪልህ አትጠብቅ፤ የፈለከው ገንዘብ መጥቶ፣ የተመኘው እቃ ተሟልቶ አንተ ስራውን እንድትጀመር የምትጠራበትን ጊዜ አትጠብቅ። መጀመሩ ብቻ ሳይሆን እስከ ጅማሬህ የሚወስድህን የፅናት፣ የትእግስትና የድፍረት ጉዞም መጓዝ ያለብህ አንተው እራስህ ነህ። ፍራትህን በማስታመም ስህተትህን አታጠፋም፤ ስጋትህን በመጠየፍ ከውድቀት አታመልጥም፤ ፍፁምነትን እየተመኘህ እንከን አልባ ስራ አትሰራም። ስህተትህን አትጠብቅ፤ መሳሳት ካለብህ አሁን አድርገህ ተሳሳት።

አዎ! የመጠው ቢመጣም፣ ስህተቱ ቢፈጠርም፣ ውድቀቱ ቢከሰትም፣ ትቺቱ ቢያጋጥምህም አሁን ጀምረህ ተሳሳት፤ አሁን ጀምረህ ውደቅ፤ አሁን ተነስተህ ተተች። ቦሃላ፣ ነገ፣ የሚቀጥለው አመት ማለት የህልምህ ጠላት እንደሆነ እወቅ። ጊዜውን ከማዘግየቱም በላይ፣ በሂደት በስንፍና ሃይል ከህልምህ ይለይሃል፤ ከራዕይህ ይነጥልሃል፤ መኖር ከሚገባህ ህይወት ያስቀርሃል። ማንም ያልተሳሳተ፣ ማንም ያልወደቀ፣ ማንም ትቺት ያልቀረበበት፣ ሰው መጥፎ አስተያየት ያልሰጠው ሰው ቢኖር ያልጀመረና ባለበት የቆመ ሰው ብቻ ነው። ስህተትህ ጅማሬህን ያመላክትሃል፤ ውድቀትህ ጥረትህን ይገልፃል፤ የሰው አይን ውስጥ መግባትህ ጉዞ መጀመርህን ያሳያል። በፍረሃት የምትሸረሽረው፣ በፍፁምነት እሳቤ የምትቀናንሰው ረጅም ጊዜ ያለህ እንዳይመስልህ። ጉልበትህ ውሱን ነው፤ ንቃትህ የተገደበ ነው፤ ሁሉም በጊዜው ልክ እየሔደና እየወረደ ይመጣል። ብርታትህን በፍጥነት ተጠቀም፤ ንቃትህን በጊዜ ስራ ላይ አውለው፤ ጥንካሬህን በጠዋቱ ለፍሬ አብቃው።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.6K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 07:20:58
3.0K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 20:53:08 ፍቅርን በሙላት ኑሪ!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
አዎ! ፍቅርን በሙላት ኑሪ፣ ህይወትሽን ስሜት ስጪው፤ ውብ አስደሳች ማራኪ አድርጊው። ጊዜ እንደሌለሽ አስቢ፤ የሚወዱሽን እንደ ውዶችሽ ተመለከቺ፤ ለሚያስቡልሽ ጊዜ ስጪ፤ ለሚያዝኑልሽ ማዘን ጀምሪ፤ ለሚንከባከቡሽ እንክካቤን ለግሺ። ህይወት አጭር ነች በተስፋሽ አስረዝሚያት፤ ህይወት ጉድለት አይጠፋትም በፅናትሽ ሙሉ አድርጊያት፤ ህይወት እንቅፋቶች ይኖሯታል በብርታትሽ ተሻገሪያቸው። ስለእራስሽ ብቻ ማሰብ አቁሚ፤ ባንቺ መኖር የሚያተርፍ፣ ባንቺ ከጎኑ መቆም የሚደሰት ሰው እንዳለ አስቢ። ሰው የለኝም ከማለትሽ በፊት ሰው ለሌላቸው ሰው ሆኖ መገኘትን ተለማመጂ፤ በእርግጥም ከልብሽ ሰዎች እንዲሆኑልሽ የምትፈልጊውን ሰው ለሰዎች ለመሆን ሞክሪ። ውስጥሽ የሌለ ማንነት ስለፈለግሽው ብቻ እንደማይመጣ አስታውሺ።

አዎ! ጀግኒት..! የሆንሽውን ከጎንሽ ታገኚዋለሽና፤ ውስጥሸ ያለው ወዳንቺ ይመጣልና ፍቅርን በሙላት ኑሪ፤ ለምኞትሽ ሁሉ ልባዊ ጥሩ ስሜት ይኑርሽ። አንዳንዴ ፍላጎታችን ሌላ፣ እኛ የሆነው ሰው ሌላ ሆኖ ይገኛል። መልካም ሰው ወደ ህይወቱ እንዲገባ የሚፈልግና የሚጠብቅ ሰው፣ ከጥበቃው በፊት የእርሱን መልካምነት፣ የእርሱን ለዛ ለሚመጣ ሰው ተገቢ መሆን በሚገባ ማረጋገጥ ይኖርበታል። ከእራስሽ ጋር በፍቅር ከወደቅሽ አንቺን የሚያፈቅርና የሚያከብር አይጠፋም። ህይወትን መኖር በስስት ነው፤ ዛሬን ማሳለፍ በሙላት ነው። ምክንያቱም ከአንድ ጀምበር ኋላ የምትመጣው ከቀድሞው የተለየችና አዲስ ቀን፣ አዲስ ህይወት ነችና ነው። በህይወት እያለሽ ማሳካት የምትፈልጊውን ነገር በጥልቀት መርምሪው፤ መመስረት የምትመኚውን የቤተሰብ ሁኔታ፣ እንዲኖርሽ የምትፈልጊውን ስፍራ፣ መርዳት የምትመኚውን ሰው ደጋግመሽ አስቢ። ዛሬ ያለሽበትን ስፍራ ተመልከቺ፣ ጉዞሽን አስተውይ፣ ምንያክል ለምኞትና ፍላጎቶችሽ ብቁ እንደሆንሽ እራስሽን ጠይቂ።

አዎ! ጀግናዬ..! ማምጣት የምትፈልገውን ተዓምር የምታመጣው በውስጥህ ፈጥረሀው ከጨረስክ ቦሃላ ነው። ያንተ እንደሆነ ያመንከው ነገር ያንተ ነው፤ ያንተ በመሆኑ የሚሰማህን ስሜት ማጣጣም ስትጀምር በእውን ያላችሁ ርቀት እየጠበበ ይመጣል። በምኞት አለም ለመኖር ጊዜ እንደሌለህ አስብ፤ ዘወትር የምትፈልገውን እያሰብክ ለመዝለቅ ሁኔታዎች እንደማይፈቀዱ አስተውል። የልብህ መሻት እውን ይሆን ዘንድ የፍቅርን ሃይል በሚገባ ልትጠቀመው ይገባል። ደስታን የሚሰጥህን ነገር ለመውደድ ገደብ አታስቀምጥ፤ በሚያረጋጋህ ነገር ለመረጋጋት እራስህን አታቅብ፤ ውስጥህ ሃሴት የሚፈጥርልህን ነገር ከማጣጣም ወደኋላ አትበል። በዙሪያህ በጣም ብዙ ህይወት ኖሯቸው ህይወት የሚዘሩብህ፣ ምሉዕ የሚያደርጉህ ነገሮች አሉ። ፍቅርን ከልብህ መኖር ስትጀምር፣ ለተፈጥሮ ያለህ ስሜት ከውስጥህ ሲወጣ፣ በከባቢህ ስትማረክ ካሰብከው በላይ የህይወት ምርጫና ፍላጎት በአንድ አቅጣጫ ሲዋሃዱ ትመለከታለህ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.8K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 07:39:49 ከዚህ ይበልጣል!
፨፨፨/////////፨፨፨
አንዳንድ ሃሳቦች ሃሳብ ብቻ ናቸው፤ አንዳንዶችም ቅዠት ሊሆኑ ይችላሉ። ደጋግመህ ታስበዋለህ ነገር ግን ልታደርገው አትሞክርም፤ ደጋግሞ ይታይሃል፣ ይመጣብሃል ነገር ግን በእውን ልታየው አልቻልክም። ጀርባህ ብዙ ታሪክ፣ ኋላህ ብዙ እንቆቅልሽ፣ ብዙ ሸክም ይኖራል። በምንም ተዓምር በእንቆቅልሽ ማንነት፣ ባልተፈታ ታሪክ ታጅበህ ወደፊት መጓዝ፣ ሃሳብህን መኖር፣ እቅድህን መፈፀም፣ ህልምህን መኖር ሊቀልህ አይችልም። ምንም እንኳን መጠኑና አይነቱ ቢለያይም ሁሉም ሰው በህይወት አጋጣሚ በህመም ውስጥ ያልፋል፤ በስቃይ ይፈተናል፤ በግል አጣብቂኝ ውስጥ ይወድቃል፤ ደፋ ቀና ይላል፣ ይታገላል። የተደላደለ ህይወት ለማግኘት ብዙ ርቀት መጓዝ ይኖርበታል፤ ብዙ መሰናክሎችን ማለፍ ይጠበቅበታል፤ መወጣት የማይፈልገውን ሃላፊነት መወጣት ይጠበቅበታል።

አዎ! ጀግናዬ..! ሃላፊነትህ ቢልቅም፣ ተጠያቂነትህ ቢበዛም፣ ችግሮችህ ቢወሳሰቡም ህይወትህ ግን ከዚህ ይበልጣል፤ መቆየትህ ከዚህ ሁሉ ይልቃል። የሚሆኑ የማይመስሉ ታሪኮች ሊከሰቱ ይችላሉ፣ አጣብቂኞቹ ሊደራረቡ ይችላሉ፣ ፍላጎትና አሁናዊው አቅምህ ሊለያዩ ይችላሉ፣ ምኞትህና የጀመርከው መንገድም ሊራራቁ ይችላሉ። ነገር ግን በዚህ መሃልም ቢሆን መዳረሻህ አንድና አንድ ነው፤ በአዎንታዊነት ዘርፍ ከፍ ማለት፤ ጠቃሚ፣ ችግር ፈቺና አንተ የመጣህበት ከባድ መንገድ ላይ ያሉ ሰዎችን ማብቃት፣ መደገፍና አቅጣጫውን መጠቆም። የሆነው ቢሆንም የሚበልጠው ላይ ማተኮር ይኖርብሃል፤ እውነታውን ተቀብሎ መቆም ሳይሆን ወደፊት መጓዝ፣ መሰናክሎችን ተሻግሮ የተሻለውን ህይወት መፍጠር ይጠበቅብሃል።

አዎ! በጊዜ ብዛት የተገለጡ፣ ጊዜ ወዳንተ ያመጣቸው ጉዳዮች ፈቺው ጊዜያቸው ነው፤ የሚያቀላቸው እራሱ አምጪው አምላክ ነው። ፅናትህ እስከ ጥግ ሲሆን እንቆቅልሾችህ ይፈታሉ፤ ትዕግስትህ ሲበዛ የላቀውን ብለሃት ትጎናፀፋለህ። በደረሰብህ ጉዳይ ፈጥነህ ብይን አትስጥ፤ እራስህ ላይ ለመፍረድ፣ ማንነትህን ለመተቸት፣ መንገድህን ለማንቋሸሽ አትቸኩል። ሁሉም ሰው የተመረጠለት መንገድ በእርሱ በመራጩ በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክልና እንከን አልባ ነው። ሁኔታህን መቃወም፣ ገጠመኞችህን መተቸት፣ በመጣህበት መንገድ ማፈር ከአምላክህ መቃረን፣ ፈጣሪህን መተቸትና በስራው ማፈር እንደሆነ እወቅ። መሰራት ባለብህ መንገድ ትሰራለህ፤ ብቁ መሆን በሚገባህ አቅጣጫ ብቁ ትሆናለህ። ዋናው ስቃይና ውድቀትህ ሳይሆን ዳግም መነሳትና የፈለክበት ስፍራ መድረስህ ነው።
ግሩም ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
4.2K views04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 22:00:31 እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ

አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ

JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማረኛ ይማሩ


የቻናሉ Link

@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
505 views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 20:15:49 ዝም ብለህ እደግ!
፨፨፨//////////፨፨፨
አንዳንዴ ካንተ ጋር የማይሔዱ፣ ከሃሳብህ የማይስማሙ፣ ህልምህ የማያሳምናቸው፣ ተስፋህ የማይታያቸውን ሰዎችን መራቅ፣ መነጠል፣ መለየትና እነርሱን መግፋት ላያስፈልግህ ይችላል። እግረመንገድህን ህይወትህን ለመቀየር፣ እራስህን ለማሻሻል፣ ማንነትህን ለማሳየት፣ በልክህ ለመኖር በምታደርገው ጥረት በሁኔታዎች መሃል ዙሪያህን እየቀየርክ፣ ውሎህን እያስተካከልክ፣ አመለካከትህን እያሳደክ ትመጣለህ። ይህም ተግባርህ ምንም ቢያደርጉህ፣ ምንም ቢያደርጉብህ ዝም ብለህ ማደግህ ብቻ እነርሱን ወደኋላ ያስቀራቸዋል፤ ፍጥነትህ ከእነርሱ ይነጥልሃል፤ ውሎህ በብዙ ርቀት እንድትቀድማቸው ያደርግሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! ዝም ብለህ እደግ፤ ዝም ብለህ ተመደግ፤ ድምፅህን አጥፍተህ እራስህ ላይ ስራ፤ ጠንክረህ መለወጥህን ቀጥል። ሊተውህ ወይም ልትተዋቸው ያልቻልካቸው የቅርብ ሰዎች ቢኖሩና በእርግጥ የሚገቡህ፣ የሚያስቡልህና የሚጠቅሙህ ከሆኑ በኑሮህ መቀየርህ፣ በህይወትህ ከፍ ማለትህ፣ በብዙ ዘርፍ ማደግህ ሊጎረብጣቸውና ግንኙነታችሁን ሊያበላሸው አይችልም። ነገር ግን ዝቅ ስላልክ፣ ደረጃህን ስላሳነስክ፣ ወርደህ አቀርቅረህ ስለሰራህ ከሰው በታች የሚያዩህ፣ እራስህን በመሆንህ፣ ትክክለኛ ማንነትህን በመግለጥህ፣ በምርጫህ በማደግህ አይናቸው የሚቀላ፣ የሚቀኑብህና የሚናደዱብህ ከሆኑ ለእራስህ በመታመን የለውጥ ጉዞህን መቀጠሉ ብቸኛው አማራጭህ ነው።

አዎ! ወዳጅ ቢሔድ ወዳጅ ይተካል፤ በህይወትህ የሚገጥሙህ ሰዎች በሙሉ የእድሜ ልክ አይደሉም። አላማህን ከያዝክ ካንተ ጋር የሚስማሙ፣ የሚጠቅሙህ፣ አንተም ደስ ብሎህ የምትጠቅማቸው ሰዎች ይመጣሉ። በክፉ ቀን ከደረሱልህ፣ ስትወድቅ ካነሱህ፣ ስትፈልጋቸው ከሚደርሱልህ ሰዎች የትኛውም እድገትህ ላይለይህ ይችላል። ከሚያሴሩብህና በጀርባህ ከሚወጉህ ሰዎች ግን እድገትህ በሚገባ ይነጥልሃል፤ እለት እለት መቀየርህ መንገዳችሁን ይለየዋል። አንድ ቀን ትቺት የማትሰማበት፣ ለነቀፋ ጆሮ የማትሰጥበት፣ ለተቃውሞ የማትመለስበት ጊዜ ይመጣል። ያም ሰዓት በእርግጥም በእራስህ የምትተማመንበት፣ በእድገትህ የምትኮራበትና የእራስህን አቅጣጫ የያዝክበት ሰዓት ነው። ዝም ብለህ እደግ፣ ዝም ብለህ ተቀየር፣ ማራገፍ ያለብህን ሸክምም በሂደት እያራገፍክ ተጓዝ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
1.4K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 08:22:31 ተለቀቀ!

በተረጋጋ መንፈስ
በሰከነ አዕምሮ
በሚዛናዊ እይታ ህወታችሁን ለመምራት አዳምጡት!

LIKE COMMENT SUBSCRIBE SHARE



2.4K views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ