Get Mystery Box with random crypto!

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mentalcounsel — Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™
የሰርጥ አድራሻ: @mentalcounsel
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.06K
የሰርጥ መግለጫ

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-16 07:52:15 የምትኖረውን ስራ!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
አዎ! ስራህን ኑረው ወይም የምትኖረውን ስራ። እያማረርክና እየተናደድክ የምትጨርሰው ረጅም ጊዜ ያለህ እንዳይመስልህ። እያንዳንዱ ሰዓትህ ተመላሽ አይደለም፤ እያንዳንዱ ጊዜህ በምንም ቢያልፍ ውድና አይተኬ ነው። እንዳለመታደል ሆኖ የምትሰራውን ላትወደው ትችላለህ ነገር ግን ወደድክም ጠላህም እየኖርክ ያለሀው እርሱን እየሰራህ ነው። "ኑሮ እንዴት ነው?" ብትባል ቀድሞ የሚመጣልህ አሁን የምትሰራው ስራ ነው። ስራህን እንደ መዝናኛ መመልከት ብትችል ህይወትህን ማቅለል ትችላለህ፤ ከስራህ ጋር ብትዋሃድና ከልብህ ብትሰራው ማንም ባያይህም በብዙ እጥፍ ጥራትና ውጤትን ትጨምራለህ። መስራትህ ካልቀረ ከልበህ ስራው። እስከ መቼ እራስህንም ስራውንም እየበደልክ ትኖራለህ? የያዝከው ህይወት እንጂ ነገ የምትደግመው ጫወታ አይደለም። አንድ ስራህን እያማረርክ ህይወትህን ደስታ ቢስ ታደርገዋለህ፤ ሁለት ካንተ በማይጠበቅ ሁኔታ ስራውን ትበድላለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከሁለት አንዱን ካላደረክ ምንም አትቀይርም። የተሰጠህን አጭር እድሜ ጠዓም ለመስጠት አንድም ስራህን ኑረው ወይም የምትኖረውን ስራ። ስራህን ስትኖረው ከማንነትህ ጋር ይዋሃዳል፤ ስራ ሳይሆን ጫወታ ወይም መዝናኛ ይሆንሃል፤ ሁሌም ስታደርገው ደስተኛነትህ በእጥፍ ይጨምራል፤ ጊዜህን ቢወስድ፣ ቢፈትንህና ቢያደክምህ ላንተ ምንም አይደለም። የምትኖረውን ስትሰራም እንዲሁ መርጠሀው፣ ወደሀው፣ ፈልገሀው ትጀምረዋለህና ስሜቱ የተለየ ነው፤ ያለማንም ግፊት፣ ያለምንም ጫና በእራስህ ስለጀመርከው ብቻ ውስጥህ በሃሴት ይሞላል፤ ህይወትህ በእርሱ ትርጉም ያገኛል፤ በእርሱ ታርፋለህ፤ በእርሱ ትታደሳለህ፤ በእርሱ ትረጋጋለህ። ህይወታችንን በምንም ብናሳልፍ ማለፉ አይቀርም። ተደሰትን አዘንን፣ ተቆጨን አመሰገንን፣ አማረርን በስራችን ረካን ጊዜው ይሔዳል፤ ወቅቱ ይቀየራል፤ ነገሮች ይለዋወጣሉ።

አዎ! ምርጫ እንደሌለህ ካሰብክ ምንም ቢሆን ምርጫህ ተረጋግቶ፣ ተደስቶና ሰላም አግኝቶ ህይወትን ማጣጣም ነው። ለዚህም ሁነኛው መንገድ ስራህን መኖር፣ በውስጡ ህይወትን ማግኘት፣ ደስታን መፍጠር። ካልሆነም የምትኖረውን፣ የሚያኖርህን፣ እለት እለት የምትታደስበትን፣ ላንተ ትርጉም የሚሰጥህን እያደረጉ መኖር ነው። ምኑንም እንደነገሩ ሰርተሃል፣ ይህንንም ያንንም እየጀመርክ ትተሃል፣ ማንንም ስትከተል ከርመሃል ነገር ግን ዛሬም እዛው ነህ፤ ህይወትህ ለውጥ የለውም፤ በእራስህ ላይ ምንም አልጨመርክም። ጉዳዩ የገንዘብ፣ የንብረት ወይም የስምና የእውቅና ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩ የእሴት (Value) ጉዳይ ነው። በህይወትህ ትርጉም የምታገኘው እሴት መጨመር ስትችል ነው። በምሬትና በለቅሶ፣ በሰበብና በቁጪት ደግሞ እንኳን እሴት መረጋጋትም ሊመጣ አይችልም። ህይወት ነገ እንደማትኖር እያሰብክ በሚገባ ኑራት፤ መቼ እንደምትቀማ አታውቅምና ባለህ አመስግንባት፤ እንዲኖርህ ለምትፈልገውም እንዳለህ አድርገህ አመስግን። በህይወት መሰንበትህ ውዷ ስጦታህ ናትና በስራህ ሙሉና አስደሳች አድርጋት።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.5K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 20:52:22 ስብራትሽ ያበቃል!
፨፨፨/////////፨፨፨
ለእራስሽ ማሰብ ስትጀምሪ፣ ጨከን ስትዪ፣ እራስሽን ስትደግፊ፣ ዙሪያሽን ስትመለከቺ፣ አማራጮችን ስትቃኚ ሲያስጨንቅሽ የነበረው ነገር ሁሉ ተኖ ይጠፋል። ማንም የለሽም ብለው ችላ ቢሉሽ ተያቸው፤ ዋጋ የለሽም ብለው ቢርቁሽ ተያቸው፤ አታስፈልጊንም ብለው ቢያገሉሽ ተያቸው። ዳግም እንዲጎዱሽ አትፍቀጂ። ለእራስሽ ዋጋ ሲኖርሽ በሰዎችም ፊት ዋጋ ይኖርሻል። በወሬ ቢተቹሽ በስራ ብለጪያቸው፤ ስም በማጥፋት ሊጥሉሽ ቢሞክሩ እራስሽ ላይ በመስራት ተሽለሽ ተገኚ። ወደ ፊት ወደ ኋላ ማለት አያስፈልግም። አንዴ ሲገፉሽ የነበሩ ሁሉ ሊወዳጁሽ ቢጥሩ አትደነቂ። እራስሽን ስትጠብቂ፣ እራስሽን ስትወጂ፣ እራስሽን ስትንከባከቢ የማይመለከትሽ ሰው አይኖርም። ነገር ግን ለእራስሽ ተገን የምትሆኚው፣ ዋጋ የምትሰጪው በሰዎች ተቀባይነት እንድታገኚ፣ ሰዎች እንዲወዱሽ አይደለም። ለእራስ መወገን፣ እራስን መጠበቅ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እንደሆነ ስለምታውቂ ነው።

አዎ! ጀግኒት.! እራስሽን ስታውቂ፤ ማንነትሽ ሲገባሽ፣ አንቺነትሽን ስትረጂ፣ ዋጋሽ ሲገለጥልሽ፣ ደረጃሽን ስትለዪ ስብራትሽ ያበቃል፤ እንባሽ ይታበሳል፤ ሃዘንሽ ይቆማል። ነገሮች በምክንያት እንደሚሆኑ ስታምኚ ያለ ጥፋትሽ ለበደለሽ፣ ክዶሽ ጥሎሽ ለሔደ ማዘን ትጀምሪያለሽ፤ በእርሱም ምክንያት ወደ እራስሽ በመምጣትሽ ታመሰግኚዋለሽ። "አንቺ እራስሽን ካልረዳሽ ማንም አይረዳሽም" የሚለው ንግግር ንግግር ብቻ አይደለም። ሁሉም ችግሮችሽ መፍትሔ የሚያገኙት ከማንም በላይ አንቺ እራስሽን ስትረጂና እራስሽን ስትረጂ ብቻ ነው። ጠንካራ ሴት መሆን ምርጫ ሳይሆን ግዴታሽ ነው። በጣም ብዙ ሃላፊነቶች እንደሚጠብቁሽ አስቢ፤ ከጊዜያዊ ችግሮችሽ በላይ የሙሉ ህይወትሽ ቁልፍ በእጅሽ እንደሆነ ተገንዘቢ። ከእንድ ሰው ጫወታ ሜዳ ብትወጪ የእራስሽ የግል መጫወቻ ሜዳ እንዳለሽ አስታውሺ። ከምንም በፊት እራስሽን ጠግኚ፤ እራስሽን አበርቺ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሰው (High Value Man) ስትሆን ውድና ተፈላጊ ሰው ትሆናለህ። እንደ በፊቱ የፈለገህ ሁሉ አያገኝህም፤ ያልተፈለክበት ቦታም አትገኝም፤ እንደ ቀድሞው ሲጠሩህ አቤት ሲልኩህ ወዴት አትልም። ዛሬ ትጠይቃላህ፣ ታመዛዝናለህ፤ የምትላክበት ስፍራ ካንተ አላማ ጋር መሔዱን ታገናዝባለህ። የመሸወድ፣ የመታለል፣ የመበላት ጊዜ አብቅቷል። ጥለውህ ስለሔዱ፣ ስለካዱህና የማይሆን ስም ስለሰጡህ ጥግ ይዘህ የምታለቅስ ወይም የማይሆን ሱስ ውስጥ የምትገባ አይደለህም። ዋጋህን ከፍ በማድረግ፤ ጥራትህን በመጨመር፤ ደረጃህን በማስተካከል ማንነትህን ታሳያለህ። ሲጫወቱበት ነበሩት ሰው ሁሌም መጫወቻ ሆኖ አይቀጥልም፤ ሲቀለድበት የነበረ ሰው ሁሌም መቀለጃ ሆኖ አይቀርም። ማንም ደጋግሞ ቢጥልህ ደጋግመህ እራስህን የማንሳት ግዴታ አለብህ። ለእራስህ ማድላትን፣ ለእራስህ መወገንን ምርጫ አታድርገው። ካንተ ቦሃላ የሚመጡትን ነገሮች አቆያቸው፤ አስቀድመህ እራስህን ታደግ፤ እራስህን አጠንክር።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
2.7K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 07:12:41 ድጋሜ ሞክረው!
፨፨፨/////////፨፨፨
ምንም ያክል ዋጋ ያስከፍልህ ድጋሜ ሞክረው፤ ያስወጣህን ያስወጣህ አሁንም ደግመህ አድርገው። እስኪያኮራህ፣ አንገትህን ቀና እስኪያደርግ፣ ልብህን እስኪያስደነድን በፍፁም ከማድረግ እንዳትቦዝን። ሙከራህ ዋጋ አለው፤ የማይቋረጥ ጥረትህ ይቆጠራል፤ በስተመጨረሻም ይከፍልሃል። ከምትባለው በላይ ነህ፤ ከሚወራብህ ትናንሽ ነገር ትበልጣለህ። ሀ ብለህ ስትጀምር ሃላፊነት መውሰድ እንዳለብህ ታውቃለህ፤ መርጠህ፣ ፈልገህ፣ ወስነህ መጀመርህ ደግሞ ሃላፊነት እንዲሰማህና ይበልጥ እንድትጠነክር ያደርግሃል። የምትችለው ወድቆ መቅረት አይደለም፤ የሚመጥንህ በመሃል ማቋረጥ አይደለም፤ የሚገልፅህ የጅምሮች ብዛት አይደለም። የጀመርከውን የመፈፀም ሃላፊነት አለብህ፤ ምቾት ማጣትን መላመድ አለብህ፤ ትቺትና ጫናውን መቻል ይኖርብሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! ድጋሜ ሞክረው! ተስፋ መቁረጥ፣ ወደኋላ መመልከት፣ መሰናክሎችን መቁጠር፣ ችግሮችን ማጋነን፣ ሁኔታዎችን ማወሳሰብ አቁም። ካልደጋገምክ የትም እንደማትደርስ እወቀው። አንዴ ሞክሮ በማቆምና ደጋግሞ እስኪሰለችህ መሞከር መሃል ጥልቅ ፍላጎት የተሰኘው ልዩነት ፈጣሪ ነገር አለ። ካልፈለከው አትገደድም፤ ከፈለከው ግን የምታቆመው ስታሳካው ብቻ ነው። አንተ ቢደክምህ ውስጥህ አይደክመውም፤ አንተ ብትሰበር ውስጥህ አይሰበርም፤ አንተ ብትሰለች ውስጥህ አይሰለችም። እችላለሁ ከምትለው በላይ እንደምትችል የሚያረጋግጥልህ ማንም ሳይሆን የማያቋርጠው ጥረትህ ነው፤ እልህ አስጨራሹ ትጋትህ ነው። የትም ብትሔድ ድጋሜ እንድትሞክር የሚገፋህ ሃይል ውስጥህ አለ፤ ከየትኞቹም ብርታትና አነቃቂዎች በተሻለ እርሱ ያበረታሃል፤ እርሱ ያነቃቃሃል።

አዎ! በጫና፣ በግፊት፣ በሰዎች አበረታችነት አንዴ ልትሞክር ትችላለህ፤ ለእራስህ፣ በእራስህ ፈልገህ መርጠህና ወደህ ከጀመርክ ግን የመደጋገሙ ጥያቄ አያሳስብህም። ከጅማሬህ ማግስት ረጅም ርቀት እንዳለ ልብህ ያውቀዋል፤ በአጭሩ የትም እንዳማትደርስ ውስጥህ ያውቃል። በሙከራህ ሂደት እዚህ ደርሰሃል። ወደኋላ ብትመለከት፣ ለአፍታ እራስህን ብትቃኝ ከዛሬው ማንነትህ ፍፁም የተለየውን አንተን ትመለከታለህ። በሙከራህ ውስጥ አድገሃል፤ በጥረትህ ትክክለኛውን ማንነትህን ተገንዝበሃል፤ ያንተ የሆነውን የሚያስደስትህንና የሚገልፅህን አውቀሃል። መቼ ታቁም አታቁም ባታውቅም መቀጠል እንዳለብህ ግን ውስጥህ ይነግርሃል። ለመጀመር ረጅም ጊዜ ወስደሃል፤ ለማቆምም ይህንኑ ታደርጋለህ። ያንተ ያልሆነን ነገር መደጋገም ላይጠበቅብህ ይችላል፤ ያንተ የሆነውን ግን መተው አትችልም። በጫና ውስጥ ብትሆንም ሙከራህን ቀጥል፤ ብዙ ያልተመቸህ ነገር ቢኖርም ለውስጥ ፍላጎትህ፣ ለልብ መሻትህና ለማያቋርጠው ፅኑ ምኞትህ ብለህ ጥረትህን ቀጥል፤ ህይወትህን አሸንፍ።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.1K views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 07:12:16
2.6K views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 20:33:31 ብቻህን ተመሰጥ!
፨፨፨//////////፨፨፨
አለምን ተመልከት፤ እረፍት የላትም፤ እለት እለት አጀንዳ አታጣም፤ አዲስ ነገር የሚያመጣ ሰው አይጠፋትም፤ የሚረብሽና ሰላም የሚነሳ ክስተት አይለያትም። አንዱ አጥፊ ሲሔድ ሌላው ይተካል፤ አንዱ በዳይ ሲያልፍ ሌላው በተራው ይመጣል። አለም መቼም የሚወራ አጀንዳ አጥታ አታውቅም፤ መቼም የሰውን የሚያስጨንቅ፣ ፋታ የሚነሳ ነገር ተለይቷት አያውቅም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ብቻህን ልትሆን ትችላለህ? ብቻህን የሆንክ ይመስልሃል ነገር ግን አይደለህም። ስለ ወቅታዊው ጉዳይ የማታውቀው ነገር የለም። ዜናው አያመልጥህም፤ የሰፈሩን ወሬ አትዘለም፤ መሃበራዊ ድህረገፁ አይቀርህም። ሁሉም በእጅህ ነውና የሚሆነውን ታያለህ፤ የምትፈልገውን ትመለከታለህ፤ የተመቸህን ሰው ታወራለህ ነገር ግን በዚህ ሁሉ የተጣረሰ ምህዳር ውስጥ ተቀምጠህ ብቻህን እንደሆንክ ትብሰለሰላለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ብቻህን ተመሰጥ! በፍፁም ለእራስህ ነፃነት ለመስጠት ጊዜ አታባክን። የሚረብሹህን ነገሮች አያንዳንዳቸውን አጥፋቸው፤ ጥቅም ከሌላቸው ተግባሮች ተነጠል፤ እራስህን ከጫጫታ ዞር አድርግ። በምንም አይነት ሁኔታ መረጃ የማትሰማበትን ሁኔታ ፍጠር፤ ለእራስህ ብለህ እራስህን ዝም ፀጥ አሰኘው። "ብቻዬን ነኝ" እያልክ የምታለቅስበት ጊዜ አብቅቷል። ብቸኝነትህ እጅግ በጣም ውዱ ነገር ነው። ብቻህን ስትሆን የምትርቀው ከሰው ብቻ አይደለም፤ ከአምላክህ በቀር ከምንም ውጫዊ ነገር ጋር አትገናኝም። ውስጥህን በጥለቀት ትመረምራለህ፤ ትኩረትህን እራስህ ላይ ብቻ ታደርጋለህ፤ ስብራትህን ትጠግናለህ፤ ህመምህን ትፈውሳለህ፤ ውስጥህን ታጠራለህ፤ ምንያክል ለእራስህ አለኝታ መሆን እንደምትችል ታስመሰክራለህ።

አዎ! አንዳንዴ ከሰው ጋር ሆነህ ብቸኝነት ሊሰማህ ይችላል፤ የከበበህ ጫጫታ ውስጣዊ ብቸኝነትህን ላያጠፋው ይችላል። ምንም ቢሆን እራስህን ለማደስ ከብቸኝነት የተሻለ ሁኔታ አታገኝም። ጠንካራው ሰው ብቸኝነቱን እራሱን ለመጠገን የሚጠቀመው ሰው ነው። ብቻህን መወጣት ያለብህን የቤት ስራ ከማንም ጋር ልትወጣው አትችልም። ያንተ ጉዳይ ላንተ ብቻ የሚተው ነው። "ሰው የለኝም፤ ብቻዬን ቀረሁ፤ የሚረዳኝ የለም" እያላክ እራስህን በብቸኝነት አለንጋ አትግረፈው። በቻህን እንደሆንክ ይሰማሃል? ማንም እንደሌለህ ታስባለህ? እንግዲያውስ ለእራስህ አንተ አንዳለህ አረጋግጥ፤ እራስህን መታደግ እንደምትችል አሳይ። ማብቂያ በሌለው የአለም ጫጫታ አትታበይ። ውዱን ጊዜህን ለእራስህ ስጥ፤ እራሰህ ላይ ለመስራት ምንም ቅድመሁኔታ አታስቀምጥ፤ በቻልከው መጠን በብቸኝነትህ ውስጥ ተመሰጥ፤ በሚገባው ልክ ለእራስህ ተገን ሆነህ ተገኝ።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.0K views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 17:23:08
ሰላም ሰላም ውድ የሰውኛ ጥበብ ቤተሰቦች እንዲሁም ውድ ተወዳዳሪዎች እንዴት ናችሁ?

ባጋጠሙን አንዳንድ ምክንያቶች ወድድሩን በፍጥነት ባለመጀመራችን ከልብ ይቅርታ እየጠየቅን በዚህ ሳምንት የስነ-ግጥም ውድድሩን የመጀመሪያ ዙር ወደናንተ የምናደርስ መሆኑን በአክብሮት ልንገልፅላችሁ እንወዳለን።

የውደድሩን አቀራረበ በተመለከተ አጠር ያለውን ማብራሪያ እንዲሁም የተወዳዳሪዎችን የመወዳደሪያ መለያ ቁጥር (Code)ና ስራቸው ለእይታ የሚበቃበትን ቀን ነገ (ሰኞ) ምሽት 12:00 ሰዓት በሰውኛ ጥበብ: Sewgna Tibeb ዩትዩብና ቴሌግራም ቻናላችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
ለትዕግስታችሁ ከልብ እናመሰግናለን!

ሰውኛ ጥበብ እራስን ማወቅ ነው፤ ባወቁት ልክም ተገልጦ መታየት ነው።

ለጥያቄና ለአስተያየት፡ @iifam @iifam  ይጠቀሙ!

@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb
@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb
2.8K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 13:08:12
እናትነት ፀጋ ነው፤
እናትነት ክብር ነው፤
እናትነት መመረጥ ነው።

ለእናትነት ክብር የበቃችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለእናቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ።
ካደረጉልን ነገር አንፃር እጅጉን ያነሰና ኢምንት ቢሆንም ከሌላው ቀን በተለየ ዛሬ ለሁሉም እናቶች ያለንን ክብር፣ ፍቅርና መልካም ምኞት በተለየ ሁኔታ እንግለፅላቸው።

መልካም የእናቶች ቀን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.0K views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 07:33:38 ምግብህ ቃሉ ነው!
፨፨፨///////////፨፨፨
ስጋዊ ምግብ ስጋን ያበረታል፤ ጉልበት ይሆናል፤ ሃይልን ይሰጣል። የአምላክ ቃል ግን ከእርሱ በላይ ነው፤ ስጋን ያበረታል መንፈስን ያድሳል፤ ነፍስን ያነፃል፤ ውስጥን ያረጋጋል፤ ብርታት፣ ጥንካሬ ይሆናል። እራሱን ለማበርታት የሚፈልግ፣ በማያልቀው በረከቱ መታነፅ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መንፈሳዊ ህይወቱ ላይ መስራት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው። ከስጋ በላይ በነፍስ ፍቃድ መመራት እጅግ ደስ ያሰኛል፤ ሰላምም አለው። የነፍስን ፍቃድ መፈፀም ከምንም በላይ የህይወት ጠዓምን ይቀይራል፤ ወደ አምላክ ያቀርባል፤ እውነተኛውን ውስጣዊ እርጋታ ያጎናፅፋል፤ የአለምን ጫጫታ ዝም ያሰኛል፤ ማንነትን በበረከት ይቃኛል። አለም ምን አለው? ከአለም ምን ይገኛል? ገንዘብ፣ ንብረት፣ ዝና። ከመንፈሳዊ ህይወትስ? ከአምላክ በረከትስ ምን ይገኝ ይሆን? እርጋታ፣ ፍፁም ደስታ፣ የአምላክ በረከት፣ የማያልቀው ምህረቱ፣ የሚያረጋጋው ቃሉ፣ ህያው ማዳኑ፣ የማያልቀው ይቅርታው።

አዎ! ጀግናዬ..! ምግብህ ቃሉ ነው! ወጣህ ወረድክ፣ ብዙ ደከምክ፣ ከልብህ ለፋህ፣ ታተርክ ውስጥህ ግን የሚፈልገውን እረፍት አላገኘም፤ የተጠማውን እርካታ አላገኘም። ከማይቋረጠው ጥረትህ በላይ እለት አለት የምታቀርበው ምስጋና፣ ከሚያደክምህ እረፍት አልባ ሩጫ በላይ በቆሸሸው ልብህም ቢሆን የምታደርሰው ፀሎት የላቀ ዋጋ አለው፤ የተሻለ ውጤትም ያመጣልሃል። አማኝ ስለሚደረግለት ነገር፤ ስለሚደመጠው ፀሎት፣ ወደፊት ስለሚሰጠው በረከት፣ ስለሚመለስለት ጥያቄ ቀድሞ ያመሰግናል፤ ቀድሞ ይደሰትበታል፤ አስቀድሞ በሚፈልገው ውስጣዊ መሻት በፍቅር ይሞላል፤ ፍቅሩም እምነቱን ከልቡ ያፀናዋል፤ ከአምላኩ ጋር ያስተሳስረዋል።

አዎ! ዝምታህ መበቀል ስለማትችል አይደለም፤ መልስ የማትሰጠው ምላሽ አጥተህ አይደለም፤ ለበደልህ አፀፋ የማትሰጠው አቅም አነሰሶህ አይደለም። ፈሪሃ እግዚአብሔር ውስጥህ አለ፤ አምላክ ሁሉን እንደሚያይ ታውቃለህ፤ ፈጣሪ የልብህን እንደሚያውቅ ታውቃለህ። ክፉ ያደረገብህ ክፉ እንዲደርስበት አትፈልግም፤ የበደለህ እንዲበደል፣ ያሳጣህም እንዲያጣ አትፈልግም። ቢቻል የሆነው መጥፎ ነገር ሁሉ ባንተ ላይ እንዲቆም ታደርጋለህ፤ ነገሮችን ካንተ የግላዊ ጉዳት ከፍ አድርገህ ትመለከታለህ፤ የመልካምነትህ ዋጋ በአምላክ መልስ እንደሚያገኝ ታምናለህ፤ ውስጣዊ መረጋጋትህ በበቀል ወይም ያልተገባ መልስ በመስጠት እንደማይመጣ ታውቃለህ። ቃሉን ተመገብ፤ ነፍስህን አረስርስበት፤ እራስህን አንፃበት፤ አስተማሪና ተምሳሌት ህይወትን ፍጠርበት። ብትችል በማደሪያው፣ ባትችልም በማደሪያህ ጊዜ ሰጥተህ አድምጠው፤ ልብህን በማረጋጋት እንዲሰራብህ ፍቀድ።
ብሩክ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.3K views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 20:50:07 ይሄው ነው!
፨፨//////፨፨
እውነት ነው፤ ያለምንም ጥርጥር ከቆይታ ቦሃላ የተሻልክ ሰው ትሆናለህ፤ መጀመር ስለምታስበው ነገር ብዙ ትማራለህ፤ ብዙ ታውቃለህ፤ በተሻለ ደረጃም ትገኛለህ። አንተ ባትፈልግም የህይወት ግፊት፣ የሰዎች ጫና፣ የሁኔታዎች ከባድ መሆን በትንሹም ቢሆን ይበልጥ እንድትሰራና ለተሻለ ስፍራ እንድትበቃ ያደርግሃል። ነገር ግን በዚህ መንገድ ከመደበኛው ለውጥ የተለየ ነገር አታደርግም። ምኞትህ ልባዊ ሆኖ ተግባር ባይኖረው እንደማንኛውም ሃሳብና ምኞት እንዳለው ሰው ከመደበኛው የህይወት መዓቀፍ አትወጣም። ልዩ ነው የምትለው መርህ በውስጥህ ቢመላለስና ለመተግበር ድፍረቱ ባይኖርህ ዛሬም በነበርክበት ትቀጥላለህ። ዞሮ ዞሮ እዛው መገኘት ምንም የተለየ ጠዓም አይኖረውም።

አዎ! ጀግናዬ..! ከተግባር በቀር አትለወጥም፤ ካላደረከው ምንም አታመጣም፤ ካልጀመርክ አንዳች ነገር አትመለከትም። የትም ብትሔድ ፍረሃት አለ፤ ምንም አዲስ ነገር ለማድረግ ብታስብ መስጋትህ አይቀርም። ምክንያቱም ከለመድከው የሃሳብ እርከን ትወጣለህና፤ ምክንያቱም አድርገህ የማታውቀውን ነገር ለማድረግ ተዘጋጅተሃልና። በህይወትህ ተጨባጭ ለውጥ ማየት ከፈለክ የለውጥ ሃሳብህን አድርጎ መገኘት ምርጫ የሌለው አማራጭ ነው። ያስቀመጥካቸው ቅደመሁኔታዎች እስኪሟሉ ጊዜ ቆሞ አይጠብቅህም። የአለምን የለውጥ ፍጥነት ተመልከት፤ አንተ ግን ዛሬም በይሉኝታ ታስረህ ትጨነቃለህ። ሃሳብህ ምንም ይሁን አዎንታዊ ከሆነና ካንተ ጀምሮ የሰዎችን ህይወት የተሻለ የሚያደርግ ከሆነ ማንም ምንም ቢል ጉዳይህ ሊሆን አይገባም። ሃሳብህ መስረቅ አይደለም፤ ሃሳብህ ወንጀል መስራት አይደለም፤ ምኞትህ ሰዎችን መጉዳት አይደለም። ስለዚህ መጀመሩን ለምን ፈራሀው? ለምንስ በሰዎች አሉታዊ ቃላት ተሸበብክ?

አዎ! እርሱ ሳይመጣ አንተ ሂድለት፤ ሳያስገድድህ በውዴታ ጀምረው። ኑሮ ከብዷል፤ ሰው ክፉ ሆኗል፤ ፈተና ተደራርቧል፤ ችግር ላይ የወደቀ ሰው በዝቷል። ከዚህ በላይ ሃሳብህን መሬታ ላይ እንድታወርድ የሚያደርግህ ሁኔታ ምን ሊሆን ይችላል? አንዳንዴ የነገሮች ዋጋቸው መናር አይቀሬ ቢሆንም የእኛ በነበርንበት ስፍራ መሰንበት ደግሞ ንረቱን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል። የዛሬ አምት አመት በሚከፈልህ ደሞዝ እንዴት የዛሬውን ኑሮህን በሚገባ ተቋቁመህ ማለፍን ታስባለህ? የነገሮች ዋጋ ሲጨምር ያንተም ዋጋ በትንሹም ቢሆን መጨመር ይኖርበታል። ጊዜው ትልቅ ሃሳብ ታቅፎ ለሚያባብል ሰው አይሆንም፤ ጊዜው ምኞትን እየተመገበ ለሚኖር ሰው አይሆንም። ሁሌም ቢሆን እራስን አዘጋጅቶ መጀመር፣ ወደ ተግባር መግባት መስራት፣ መስራት ብቻ። አትፍራ፤ ለሚያድገው ህልምህ ዛሬ መሰረቱን ጣል፣ በየጊዜው በሙሉ አቅምህ ስራበት፤ በዚህ ሁኔታ በፍፁም ያለማደግ ምርጫ ሊኖረው አይችልም። ይሄው ነው፤ በርታ!
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
3.5K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 20:12:16 Mental Counsel ETH: ምክረ-አዕምሮ pinned a photo
17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ